>
5:13 pm - Thursday April 19, 4621

ሄሎሎ… ዛሬስ ህመማችን ተሰማችሁ!  (ስዩም ተሾመ)

ሄሎሎ… ዛሬስ ህመማችን ተሰማችሁ! 
ስዩም ተሾመ
ወንድ ልጅ መናገር አቅቶት ስሜቱን በእምባው ሲገልፅ ተመለከታችሁ? ያደረሳችሁብን ስቃይና ሰቆቃ ከቃላትና ፊደላት በላይ ሆኖ በእምባ እየታጠበ ሲፈስ አያችሁ? እምባችን የሚፈሰው እንድትራሩልን አስበን ሳይሆን የደረሰብንን ስቃይና መከራ በቃላትና ፊደላት የማይገለፅ ሆኖብን ነው፡፡
ማደንዘዣ ወግተው ሶስት ግዜ እግሬን ቆራረጡት፣ ወያኔ ሰለተቃወሙ አባት፥ ወንድሜንና እናቴን ለሞትና መከራ ዳረጉብኝ ለማለት የሚስችል ቃልና ሀረግ ስላጣን ነው፡፡ የሚናገረት ቃላትና የሚፅፉት ፊደል ቢኖር እንኳን የደረሰብንን መከራ፤ ያለፍንበትን መከራ ለመግለፅ ብቁ አይደሉም፡፡ ካደረጋችሁብን ነገር ሁሉ በጣም የሚያመው ስቃይና መከራችንን ስንነግራችሁ መልሳችሁ ስላቅና ማንጏጠጥ መሆኑ ነው፡፡ ይሄን ሁሉ መከራና ግፍ የፈፀመብን ወያኔ/ህወሓት ነው፡፡ “ከህወሓት/ወያኔ ጋር አንድ ነኝ!” የሚል አውሬ ከመጣ በእሱ ልክ ጨካኝ አውሬ ነው፡፡ በተግባር አውሬ ለሆነ እና በሃሳብ አውሬ መሆን ለሚሻ ይቅርታ የለኝም፡፡
ህወሓት/ወያኔ መውደቅ ብቻ ሳይሆን መቃብር ይገባል፡፡ ይቅርታ ከህውሓት/ወያኔ ጋር “አንድ ነኝ” የሚል ካለ እሱም አብሮት መቀመቅ ይገባል፡፡ ምክንያቱም እኛ ሰዎች ነን!! በመሆኑም ሰው ሆነን እንደ አውሬ፣ ጨካኝ አውሬ ሆነን እንደ ሰው መኖር አንችልም፡፡
በሌላ በኩል አውሬን ሰው፣ ሰውን አውሬ ለማድረግ አንሞክርም፡፡ በሰው ልጅ ላይ ይሄን ሁሉ ግፍ የሚፈፀም በሙሉ ጭራ የሌለው አውሬ እንጂ ሰው አይደለም፡፡ ከዚህ አውሬ ጋርና አንድና ተመሳሳይ ነኝ የሚል የአውሬው መንጋ ነው፡፡
Filed in: Amharic