>
5:13 pm - Monday April 18, 8811

ህወሓት መሬት እንቅጥቅጥ ሰልፍ መቀሌ ላይ አደርጋለሁ ብሎ እየፎከረ ነው!!! (ወዲ ሻምበል)

ህወሓት መሬት እንቅጥቅጥ ሰልፍ መቀሌ ላይ አደርጋለሁ ብሎ እየፎከረ ነው!!!
ወዲ ሻምበል
ዛሬ በዋዜማው ሽርጉድ እያለ ነው። ኢትዮጵያውያን ይታያችሁ እንግዲህ አልባሳቱ እንደባለፈው አዲስ አበባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ህዝቡ ያለውን ድጋፍ ለመግለፅ በግል ገንዘቡ እየገዛ እንደለበሰ ይታወቃል። መቀሌ ግን ህዝቡ በእራሱ አነሳሽነት እንደማይለብስ የታወቀ ስለሆነ ሙሉ ወጪው ህወሓት ነው የሸፈነው ስለዚህ አፋችን ሞልተን የህዝብ ሰልፍ ሳይሆን ህወሐት በወንጀል መጠየቅ የለብኝም ብሎ ያስተባበረው ሰልፍ ነው እንላለን።
ህወሓት እንደ ኮርያ የመጨረሻ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጋ ወደ መቃብሯ ልትሸኝ ይሆን?!?
ናት ኤል አስመላሽ
ነገ በትግራይ ዋና ከተማ መቀለ አቦይ ስብሓት፣ ጌታቸው አሰፋ ፣ አባይ ጻሃየ ፣ ስዩም መስፍን ………
ሰልፍ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፣ የትግራዩ ሃይለማርያም ደሳለኝ ደብረጽዮን፣ የተጻፈለትን ያነባል፣ እንበታተናለን ይላል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢፈርት ካምባኒ የሆነው አልመዳ ጨርቃጨርቅ ኮፍያዎች ቲሸርቶች አምርቶ ሰልፉን ይቀላቀላል፣ መቀሌ ውስጥ የሚገኙ የኢፈርት ካምፓኒ ሰራተኞች ስራ አቁመው ሰልፉን በግድ ይቀላቀላሉ፣ ካልተቀላቀሉ ከስራ እንደሚባረሩ ተነግሮዋቸዋል፣ በከተማዋ የሚገኙ የኢፈርት ካምፓኒ መኪኖች ስራ አቁመው ሰልፉን ያደምቃሉ። ህወሓት እንደ ኮርያ የመጨረሻ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጋ ወደ መቃብርዋ የምት ሸኝበት ጊዜ ይሆንላታል። አፋር እጁን ሰጥተዋል፣ ቀጣዩ ደግሞ የትግራይ ክልል ነው።
ማሳሰብያ ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ
ነገ በሚደረገው ሰልፍ፣ ህዝቡ ተገዶ መውጣቱ አይቀርም፣ ህዝብ ያለው አማራጭ መታዘዝ ብቻ ነው፣ ነገ ህወሓት ሲወድቅ የትግራይ ህዝብ ምን እንደሚል ሳይፈታ የታለመ ነገር ነው፣ ስለሆነም የትግራይ ህዝብ ሰልፍ የወጣ የሚመስላቹ ካላቹ ተሳስታችዋል፣ ነገ ህገመንግስት ይከበር ብለው ሰልፍ የሚወጡ፣ እነ ስብሓት ነጋ ጌታቸው አሰፋ እና ቤተሰቦቻቸው ናቸው። አፋር ላይ የተገኘው ድል ትግራይ ውስጥም በቅርቡ ይገኛል።
NB—ተገደህ ሰልፍ የምትወጣ የትግራይ ህዝብ ሆይ፣ ስቃይህ ይገባናል፣ በቅርቡ ከ 40 አመታት የህወሓት የጭቆና ቀንበር በቅርቡ ነጻ ትወጣለህ። ድል ለትግራይ ህዝብ ሞት ለህወሓት አመራሮች።
Filed in: Amharic