>
5:13 pm - Wednesday April 19, 3741

"በማንነቴ ምክንያት....!!!"  (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

“በማንነቴ ምክንያት….!!!” 
ብርሀኑ ተክለያሬድ
* ዛሬ ዛሬማ በሀገራችን አዋጪው ንግድ “ማንነት” ይባላል አልሸጥ ያለ ስብእና አልሸጥ ያለ መስዋእትነት ብጤ ካለህ “ማንነት” በሚል መጠቅለያ ጠቅልለው ያኔ ትንሽም ቢሆን ዋጋ ያወጣልሀል!
በሰላሌ ጠንቋዩ ታምራት ገለታ(እያንጓለለ)
ለጅዋር መሀመድ ሰላሌ በሄደበት ወቅት አንድ ወይፈን እና ጋሻና ጦር በስጦታ አበርክቶለታል።
 “የታሰርኩት ኦሮሞ ስለሆንሁ ነው” ብሎ የሠራውን ወንጀል በብሔሩ ተደብቆ ለማለፍ ሲሞክር ታይቷል!! ይህ በእውነቱ የጊዜው ፋሽን  ሁኗል ማለት ይቻላል ወንጀል እየሰሩ በብሔር መደበቅ።በሰዓቱ ጀዋር ስጦታውን ተቀብሎ ለአካባቢው ፖሊስ መልሶ እንዳስረከበው ታውቋል።ሀቁ ይህ ሁኖ ሳለ የስቱን ቤት ያፈረሰው የታዋቂ ሰዎችን ጭምር ታምራት(እያንጓለለ) በኦሮሞነቴ ነው የታሰርሁት ሲል ተከትለን የሌባ ጠበቃ መሆናችን ያሳፍራል።
ዛሬ ዛሬማ በሀገራችን አዋጪው ንግድ “ማንነት” ይባላል አልሸጥ ያለ ስብእና አልሸጥ ያለ መስዋእትነት ብጤ ካለህ “ማንነት” በሚል መጠቅለያ ጠቅልለው ያኔ ትንሽም ቢሆን ዋጋ ያወጣልሀል  አንዳንዴ ግለሰቦች አሳፋሪ ታሪካቸውን በማንነት ጠቅልለው ሲያቀርቡት ስመለከት የሀቀኞቹ የማንነት ጠያቂዎች ጉዞ ያሳዝነኛል በአንድ ወቅት በማጭበርበር ወንጀል ተከሰው እስር ቤት የገቡት (በምርጫ ክርክር ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ብለህ ድምፅህን ስጠን እንጂ ፖሊሲም ስትራቴጂም የለንም ብለው በሳቅ የገደሉን) አቶ ሰኢድ ሚኒሻው ከድምፃችን ይሰማ ወጣቶች ጋር ሆነን ለምን እንደታሰሩ ስንጠይቃቸው “የታሰርኩት በሀይማኖቴ ምክንያት ነው እንጂ ሁሉም የፓርቲ መሪ ሌባ ነው” ብለው አስገርመውናል በቅርቡ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘሁት ፍራሀን የተባለ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነርም “እኔና አብዲሌ የታሰርነው በማንነታችን ምክንያት ነው”ብሎ  እኔና መኩን ስንስቅ እንድንውል ተባብሮናል
 ዛሬ ደግሞ በማጭበርበር ችሎታው ወደር የማይገኝለትና በነፍስ ግድያ ሳይቀር ተፈርዶበት  በእስር ቤት ሆኖ እንኳን ተፈቅዶለት ሲያጭበረብር የነበረው ታምራት ገለታ የታሰርኩት ኦሮሞ በመሆኔ ነው እያለ አስገድዶ  እያሳቀን ነው ከሁሉ በላይ አስገራሚው ደሞ ታምራት ይህን ያለው የኦሮሞ ነፃነት ትግል አዋላጅ ነኝ ባዩ ጃዋር መሀመድ በተገኘበት መድረክ መሆኑ ነው  ስጦታ ቢጤም ለጃዋር አበርክቶለታል አሉ (በሀገሪቷ የይቅርታ አዋጅ መሰረት በነፍስ ግድያ ወንጀል የታሰረ ሰው የእርቅ ወረቀት ካላመጣ በስተቀር በይቅርታ እንደማይፈታ ተደንግጎ እያለ በይቅርታ መፈታቱስ  በማንነቱ ምክንያት ያገኘው በረከት ይሆን?) የደብረ ፅዮንን “እነ ክንፈ የታሰሩት በማንነታቸው ነው” ያሉትን የድፍረት ንግግር ያወገዙ ፖለቲከኞች ዛሬ ለጠንቋዩ ንግግር እየሳቁ ሲያጨበጭቡ ታይተዋል ምናልባትም ነገ በየከተማው ለሚከፍተው ቢሮ እገዛ ያደርጉለት ይሆናል እኛም ይህን አሳፋሪ ጉድ በህይወት እያለን ሰማን እውነተኞቹ የማንነት ፖለቲካ አራማጆች ትግላቸውን ከሌቦችና ወሮበሎች መጠቀሚያ አርቀው እስካልሰቀሉ ድረስ ገና ብዙ ጉድ እናያለን ህፃናት  ደፋሪዎቹም ሆኑ ማጅራት መቺዎቹ የዚህኛው ብሄር አባል ስለሆንኩ ማለታቸው አይቀርም በስንቱ እንፈር? ይህስ ጨዋውን ኦሮሞ ህዝብ ማሳነስ አይሆንም?  ሙሉጌታ ሉሌ እንዲህ አይነት በህዝብ የሚቀልድ ባለጌ ሲገጥመው “መትፋት ያስነውራል” ይል ነበር ሌቦች ከንፁሀኑ ህዝብ ራቅ በሉ!!!
Filed in: Amharic