>

ኦዴፓ ወዴት እየሄደ ነው ? (ሀብታሙ አያሌው)

ኦዴፓ ወዴት እየሄደ ነው ?
ሀብታሙ አያሌው
 
 ”ከኦዴፓና ኦፌኮ በቀር በዚህ አካባቢ ማንም አይንቀሳቀስም!” ብለዋል ከንቲባዋ።
 
ኦዴፓ “ጊዜው የኛነው”  በሚሉ አክራሪ ብሔርተኞች እየተዋጠ ነው፤ እነዚህ አክራሪ ኃይሎች የለውጥ አመራር የሆነውን የዶክተር አብይ አስተዳደር (ቲም ለማን) በተፅኗቸው ስር በማድረግ በፊደራል መንግስቱን ወሳኝ የፓለቲካ፤ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ተቋማት በአንድ ብሔረሰብ ቀጥጥር ስር እንዲወድቅ ከሚያደርጉት ትግል ባሻገር የኦሮሚያን ክልል የፀረ ዴሞክራሲያዊ ባህሪያቸው ግልፅ ማሳያ እያደረጉት ነው።
 በተደራጀ ሁኔታ ተራ የሽፍታነት ስራ የሚሰሩ ጥቂት ቡድኖች ከኦሮሞ ህዝብ ባህል እምነትና ፍላጎት ውጪ ግላዊና ቡድናዊ ፍላጎታቸውን የመንግስትን ስልጣን በያዙ አጋሮቻቸው ጭምር ማስፈፀማቸውን ቀጥለውበታል።  በአርሲና አሰላና በአካባቢው ባሉ አካባቢዎች ያለው ሁኔታ የሚያሳየው ይህንን ሁኔታ ነው።
 መሬት ላይ ያለውን እውነት ማሳያ
 “በአርሲ አሰላና በአቅራቢያው በሚገኙ አካባቢዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዛችኋል የተባሉ ሰዎች እስከ ሁለት ዓመት ከሶስት ወራት እስራት መቀጣታቸው ተገለጸ። በአሰላ ከተማ ከንቲባ አማካኝነት በተለይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ደጋፊዎች እየታደኑ ሲሆን የስብሰባ አደራጅ ኮሚቴ አባላት ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ከ200 በላይ ሰዎች ታስረው የተለቀቁ ሲሆን 60 ሞተር ሳይክሎች በፖሊስት ተይዘዋል። ”ከኦዴፓና ኦፌኮ በቀር በዚህ አከባቢ ማንም አይንቀሳቀስም” ብለዋል ከንቲባዋ።”
Filed in: Amharic