አባተ ደግአረገ
ምንም እንኳ ሙሉ በሙሉም ባይባል የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግሮች ቀስ በቀስ እየተቀረፉ ይመስላል ።
ህዝባዊ እምቢተኝነቱ አሼንፎ የለውጥ ኃይላትን ወደ ስልጣን ካመጣ ወዲህ የዶ/ር አቢይ መንግስት የሚከተሉትን ችግሮች ሙሉ በሙሉ አሊያም በአብዛኛው ቀርፏል ብየ አምናለሁ ።
1ኛ) ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመደመሪያ ጊዜ ጋዜጠኞች እስር ቤት ውስጥ የማይገኝባት ሃገር እንድትሆን ተደርጓል ።
2ኛ) ተዘግተው የነበሩ ድህረ ገፆች ዜጎች በነፃነት እንዲነብቡ ተደርጓል ።
3ኛ) ዜጎች በነፃነት የፈለጉትን ሃሳብ በሰላማዊ ሰልፍና በጽሁፍ እንዲገልጹ ተደርጓል ።
4ኛ) የመከላከያ ሰራዊቱና የመንግስት ተቋማት የአንድ ዘር መገልገያ ከመሆን እንዲፀዱ ተደርጓል ።
5ኛ) ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሰሚነት እንዲጨምር ተደርጓል ።
6ኛ) ኤምባሲዎች የአንድ ዘር መፈንጫ ከመሆን ፀድተው የህዝብ መገልገያ እንዲሆኑ ተደርጓል ።
7ኛ) በአንድ ክልል ሌቦች ተይዞ የቆዩ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን የህዝብ ልሳን እንዲሆኑ የማስተካከያ ስራ ተሰርቷል ።
8ኛ) የህወኃት አከርካሬ ተሰብሮአል ። ህወኃት ጨርሶ አልጠፋም ግን እጅና እግሮቹ ተሰባብረው ምላሱ ብቻ ቀርቷል ።
9ኛ) ሃገርን የዘረፉ ሌቦችና ወንጄል የሰሩ ባለ ስልጣናትን ወደ ፍትህ የማምጣቱ ስራ በከፊል ተጄምሯል ።
10ኛ) በውጭ የሚገኙ ዜጎች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሃገር እንደፈለጉ እንዲገቡና እንዲወጡ ተደርጓል ።
11ኛ) የምርጫ ሂደቱን ለሁሉም ተፎካካሪ ኃይሎች ምቹ ለማድረግ እርምጃ በመወሰድ ላይ ነው ።
12ኛ) የማህበረሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶች የቢሮ ስራዎችን እንዲሰሩ ሹመት ተሰጥቷቸዋል ።
13ኛ) የፍትህ ስርዓቱ ላይ ማስተካከያ በማድረግ ፍ/ቤቶችን በአዲስ መልክ የማዋቀር ስራ ተሰርቷል ።
14ኛ) ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ተፈትተዋል ።
15ኛ) አንዳንድ የመንግስት የንግድ ሴክተሮች ወደ ግል እንዲዘዋወሩ ተደርጓል ።
16ኛ) ለዘመናት የታፈኑ የዲያስፖራ ድምጾች በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲደመጡ ተደርጓል ።
17ኛ) እንደ አብዲ ኢሌ አይነት ፀረ ህዝብ አመራሮች ከስልጣን ወርደው ወደ ህግ እንዲቀርቡ ተደርጓል ።
18ኛ) በሙስና ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነትነ እንዲከፈት ተደርጓል ።
19ኛ) በባዕድ ሃገር በተለይም በግብጽ ፣ በሱዳንና በሳኡዲ የታሰሩ ዜጎች እንዲለቀቁ ተደርጓል ።
20ኛ) ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በነፃ እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል ።
ቀሪ የቤት ስራዎች ….
21ኛ) ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ያልተያዙ ወንጀለኞች በህግ ቁጥጥር ስር ሊውሉ ይገባል ።
22ኛ) በሌቦች ተመዝብሮ በውጭ የተቀመጠ የህዝብ ንብረት ወደ ሃገር እንዲመለስ መደረግ ይኖርበታል ።
23ኛ) የህወኃት ድርጅት በሃገር አቀፍ ደረጃና ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ ናዚ ፓርቲ በሽብር መዝገብ እንዲሰፍርና እንዲታገድ ሊደረግ ይገባል ።
24ኛ) ነፃ ታማአኒና ፍትህአዊ ምርጫ በአስቸኳይ ሊደረግ ይገባል ።
25ኛ) በውጭ የሚኖረው ዲያስፖራ ጣምራ ዜግነት እንዲያገኝና በሃገሩ ሃብት ንብረቱን እንደፈለገ እንዲያንቀሳቅስ ሊፈቀድለት ይገባል ።
26ኛ) ህዝብን የሚያፈናቅሉ ሁሉ በአስቸኳይ ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ይገባል ።
27ኛ) የኢንጅነር ስመኘው እውነተኛ ገዳዮችን በማፈላለግ ለህግ ማቅረብ ይገባል ።
28ኛ) የኤፈርት ንብረት የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት በመሆኑ ወደ ኢትዮጵያ ካዝና ሊገባ ይገባል።
ስለ ለውጡ የዶ/ር አቢይን መንግስት እናመሰግናለን ።