>

ለህግ ልዕልና ዋጋ የከፈሉትን ለሹመት በሚያበቃ መሪ ተስፋ አለማድረግ አይቻልም!!! (መሳይ መኮንን)

ለህግ ልዕልና ዋጋ የከፈሉትን ለሹመት በሚያበቃ መሪ ተስፋ አለማድረግ አይቻልም!!!
መሳይ መኮንን
”ይሄን ተስፋ አይቶ መሞትም አንድ ነገር ነው” ይህን የተናገሩት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው። እውነት ነው። የሰብዓዊ መብት ሻምፒዮን ዳንዔል በቀለን ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽነርነት፡ ለህግ ልዕልና መስዋዕትነትን የከፈለችን ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ለምርጫ ቦርድ ሃላፊነት የሚሾም መሪ በሚሾፍራት ሀገር ላይ ተስፋ አለማድረግ አይቻልም። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ስልጣንን በፖለቲካ ወገንተኝነት አጥር ውስጥ ሆነው የሚያከፋፍሉ አለመሆናቸውን እያስመሰከሩ ቀጥለዋል።
 በዚህ አካሄዳቸው የካቢኔአቸውን መዋቅር ተመሳሳይ መንገድ እንዲከተል የሚያደርጉ ይመስለኛል። በውስጣዊ መሳሳብና ፖለቲካዊ ውጥረት የተነሳ ካቢኔው በኮታ መስፈርት የተዋቀረ መሆኑን እሳቸውም ነግረውናል። ወደፊት የጀመሩትን ሪፎርም መሬት ካሲያዙ በኋላ እውቀትና ልምድ ዋናው የስልጣን መለኪያ እንደሚሆኑ እንጠብቃለን። የብርቱካንና የዳንዔል ሹመት የሚነግረንም ይሀው ነው። ይሄም ተስፋ ነው።
የሚሆነውን ማመን ነው ያቃተኝ!!!
መሀመድ አሊ መሀመድ
እነዚህ ለኢትዮጵያ እንቁዎች ናቸው። ቁምነገሩ ግን እንቁ መሆናቸውን አውቆ መቀበሉ ነው። እነዚህ የሀገሬ ወድ ሀብቶች እንጅ ከቶም ስጋቶች ተደርገው መታዬት አልነበረባቸውም።
ዐብይ አህመድ ግን ዐይናማ ነው። አላህ ከክፉ ዐይን ይጠብቀው። አሁንማ መልካም ነገሮችን በላይ በላዩ እየደራረበ ለማድነቅም ትንፋሽ እያሳጣኝ ነው። ኧረ እንዳውም የሚሆነውን ማመን እያቃተኝ; ህልም ሁሉ እየመሰለኝ ነው።
ብርቱካን ሚዴቅሳ የኢ/ብ/ምርጫ ቦርድን; እንዲሁም ዳንኤል በቀለ የኢ/ሰበኣዊ መብት ኮሚሽንን ሊመሩ ነው ማለትን ሰምቼ ነፍሴ በሀሴት ተሞልታለች።
ሀገሬ እስቲ ቀን ይውጣልሽ!!!
Filed in: Amharic