>

የግፍ ጽዋ!  (መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ)

የግፍ ጽዋ! 
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
በዓለም ላይ ብዙ ጨካኝ ሰዎች ተነስተዋል የመጀመሪያው ጨካኝ ቃኤል ነው ቃኤል ወንድሙ አቤልን በደንጋይ ቀጥቅጦ ራሱን ገምሶ ደሙን አፍሶ ገድሎታል ቃኤል በዚህ ጭካኔው የመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ ተብሎ በታሪክ ተመዝግቧል የገደለበት ምክንያት የአቤል ሚስት ሉድ ለኔ ካልሆነች በማለት ነው የእናቱ ልጅ አቤልን አታሎ ውሃ እንጠጣ ብሎ ወደ ጫካ ወስዶ ውሃ ተጎንብሶ ሲጠጣ በደንጋይ አናቱን ብሎ ገድሎታል የሚገርመው ወንድሙን በደንጋይ እንደገደለ እሱም በደንጋይ ነው የሞተው።
ቃኤል ተቅበዝባዝ ሁኖ ከኖረ በሇላ አንድ ቀን ዝናም ሲዘንም ከድንጋይ ካብ ተጠግቶ ሳለ ካቡ ተንዶ አናቱን ገምሶ በዚያው ሙቷል ለሰው ጉድጓድ የቆፈረ ራሱ ይቀበርበታል ቃኤል ወንድሙን በድንጋይ ቢገልም እሱም በደንጋይ ሙቷል።
✔ የናቡቴን ደም ያፈሰሰው አክአብ የእሱም ደም ፈሶ ውሾች ልሰውታል አክአብ ናቡቴን ርስትህን ካልወሰድኩ ብሎ  ከሚስቱ መክሮ የደሐውን ደም በከንቱ አፈሰሰ ግፍ አይቀርምና የአክአብ ደምም ፈሶ ውሾች ልሰውታል
✔ጨካኙ ፈርኦን የእስራኤልን ልጆች በዘረኝነት ተነሳስቶ ገና ሲወለዱ ወንድ ወንዶችን  እያነቀ ባህረ ኤርትራ ያሰጥማቸው ነበር የእስራኤል ልጆች በኤርትራ ባህር ተቀብረው አልቀሩም የግፉ ጽዋ ሲሞላ ፈርኦን ህጻናትን ባሰጠመበት ባህር መልሶ ሰጥሞበታል  ፈታሂ በርትዕ ኮናኒ በጽድቅ የሆነው እግዚአብሔር ፈርኦንንም አሰጠመው።
✔ ዮሐንስን ያስገደለው ሄሮድስ የገንዛ ሰውነቱን እየበላ ተልቶ ሙቷል።
 ✔መቶ አርባ አራት ሽ ህጻናትን የጨረሰው ርጉሙ ሄሮድስ ያለእድሜው መልአኩ ቀስፎታል
 ከዚህ የምንረዳው በሰው ላይ ግፍ የሰሩ መጨረሻቸው አያምርም ሲገድሉበት በነበሩበት መንገድ እነሱም ይገደላሉ በዘመናችንም የምናየው ይሄው ነው።
ሰውን ሲያስሩ ፣ ሲዘርፉ ፣ ሲከፋፍሉ ፣ ሲገድሉ  በጨለማ ቤት ውስጥ ሲያሰቃዩ  ፣ ሀብቱን ንብረቱን ሲወርሱ  ፣ ሞራሉን ሲገድሉ  ፣ ብልቱን ሲሰልቡ  እናትንና ልጅን ባልና ሚስትን አባትና ልጅን ሲለያዩ የጫካ ህግ አምጥተው ሰውን ጫካ ሲጥሉ የአውሬነት ጭካኔ ይዘው ሰውን ከአውሬ ጋር ሲያስሩ የሰዶማዊ ተልኮ ይዘው  ግብረ ሰዶም ሲፈጽሙ የጨለማው ሰይጣንን ተልኮ ይዘው ሰውን ጨለማ ውስጥ ሲገድሉ፣ ዓይን ሲያጠፉ ህጉ ጨለማ ፈጻሚዎቹ የጨለማው ታዛዥ ሲሆኑ ሰውን ብቻ ሳይሆን ሀገርንም ራቁት ያስቀሩ ሰዎች የፈጸሙት የግፍ ጽዋ ሞልቶ እነሱ ሊጠጡት ተሰልፈዋል።
Filed in: Amharic