>

የወያኔ ሚሊሺያዎች ወይስ የኢትዮጵያ ጀነራሎች!!! (አዳነ አጣ ነው)

የወያኔ ሚሊሺያዎች ወይስ የኢትዮጵያ ጀነራሎች!!!
አዳነ አጣ ነው
የወያኔ ነገር ሁሉን ነገር ማርከስ/ዋጋ ማሳጣት ነው፡፡ ደንቆሮዎች ናችሁ ሲባሉ ሁሉም በተልኮ Open University Dr ተብለናል ብለው ማታውን ሁሉም ዶክተር ነን አሉ፡፡የትምህርት ጥራትን ዝቅ እንዲል የግል ዩኒቨርሲቲዎች እና ትምህርት ቤቶችን በስፋስት ያለ መስፈርት በመክፈት ትምህርት ክብር እንድያጣ አደረጉ፡፡
የሀሰት የትምህርት ማስረጃ, የሀሰት የመንጃ ፈቃድ, ፓስፖርት, ዜጋን ወደ ውጭ አገር መላክ , ውሸትን እንደ ክብር መውሰድ ወዘተ ሁሉን የወረደ ነገር በጎሳ ተደራጅተው አስፋፉት፡፡ጉቦ በደርግ ጊዜ ጣሪያው $199 ብር ነበር ወያኔዎች በቢልዮን መዝረፍ ጅመሩ፡፡ ሁሉን ነገር ዋጋ ማሳጣት የወያኔ ዋነኛ ስራ ልዩ ምልክት ሆነ፡፡
ደርጉ በኢትዮጵያ ህዝብ ተጋድሎ, ከምእራቡ አለም ጥላቻ እና ተጋድሎ ብሎም ከአለም የፖለቲካ ለውጥ ሂደት አልጣጣም ብሎ  በራሱ ክብደት በተፍረከረከ ወያኔዎች በአጉል ውሸት በብቸኝነት ደርጉን ለመጣል እንደቻሉ አድርገው እራሳቸውን አሳምነው ወደ አልኾነ ባዶ አልበገርነት  እራሳቸውን ሰይመው በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ ተሰርቶ የማይታወቅ አስነዋሪ ነገሮችን ሁሉ ፈጸሙ፡፡
ከነውረኛ ነውረኛ ሆነው ዜጋን አስረው ግብረሰዶም ፈጸሙ፡፡
ወያኔ የኢትዮጵያን ሰራዊት አፍርሶ ያለምንም መስፈርት የሀገረን ሰራዊት በራሱ ጎሳዊ ሚሊሺያ ተካ፡፡ያለምንም ብቃት  በገፍ ጀነራሎችን በመሾም የወታደራዊ ማእርግ እዲረክስ አደረገ፡፡ ታዲያ አሁን በለየለት ምዝበራ የሀገርን ሀብት ሲዘርፉ ተራ ሌባን ጀነራል እያሉ መጥራቱ አሳፋሪ ነገር ሆነ፡፡
 ያለ ወታደራዊ ዝግጅት እና ብቃት በጅምላ በጎሳቸው መስፈርት ምክኒያት ተመርጠው ጀነራል የተባሉ ዘራፊዎችን በወታደራዊ ማእርግ መጥራቱ ተገቢነት የለውም፡፡ሊሆን የሚገባው በትክክለኛ በሚወክሉት መደብ እና ማእርግ “ሚሊሺያ ጀነራል ወይም ወያኔ ጅነራል ብሎ በትክክለኛ ማእርጋቸው መጥራት አግባብነት አለው፡፡
ለወደፊቱ አገሪቱ ለምታፈራው እውነተኛ የሀገር ጀነራሎች ስም እንዳይረክስ ከወዲሁ ሊታስብበት ይገባል፡፡
Filed in: Amharic