>

በወያኔ ኢህኣዲግ እስር ቤት ውስጥ የሚገኘው፤ መምህርና ጦማሪ ዘላለም ክብረት በ''ስራው ላይ ባለመገኘቱ'' ከስራ ተሰናበተ

Zelalem Kibret (Sinbet debdabe) ከ72 ቀን በላይ በወያኔ ኢህኣዲግ እስር ቤት ውስጥ ያስቆጠረው መምህርና ጦማሪ ዘላለም ክብረት በስራ ገበታው ላይ ባለመገኘቱ ከስራ ተሰናበተ። ”ተደጋጋሚ ጥሪ ተደርጎልዎት ከስራ ገበታዎ ላይ ባለመገኘትዎ ከስራ የተሰናበቱ መሆኑን እንገልጻለን ” የሚለው ደብዳቤ  የተለጠፈው በኣምቦ ዩንቨርስቲ ቦርድ ላይ ሲሆን፣ እንደ ደብዳቤው ኣገላለጽ፤ መምህር ዘላለም በዩንቨርስቲው ባለመገኘቱ ነው ከስራ እንዲባረር የተወሰነበት። ይህ የስንብት ደብዳቤ የተፈረመው በ ዶክተር  ላቀው ወንድሙ አባጫሪ Laqew Wendimu & Zelalem Kibretበተባሉ በኣምቦ ዩንቨርስቲ  ኣካዳሚና ምርምር ም/ፕሬዚዳንት ሲሆን፣ ጦማሪ ዘላለም  ክብረት  በእስር ቤት  ሆኖ ፤  ሃገርና ዓለም እንዲፈቱ በሚወተውቱበት ጊዜ  ደብዳቤው መጻፉም ሆነ፣ በ”ዶክተሩ” መፈረሙ  ኣነጋጋሪ ኣድርጎታል።

በዚህ ደብዳቤ የተማረሩ ኢትዮጵያውያኖች ”መምህርና ጦማሪ ዘላለም ክብረት የመጻፍና የመናገር መብቱን በማወቁ፤ ዕጣው እስር ሆኖ በባለጊዜዎች የተሸበበበት  ቢሆንም፣ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ኣንድ ቀን ነጻ እንደሚወጣ ኣስምረው፤ የተማሩበትንና የተመደቡበትን ሞያ ለሆዳቸው በለወጡ፤ በነ ዶክተር ላቀው ወንድሙ አባጫሪ ዓይነቱ የጊዜው ጠንቆች ቁጣቸውን በማህበራዊ ድረ-ገጾች (ትዊተርና ፌስ-ቡክ) እየገለጹ ነው። እንደሚታወቀው ዘላለም ክብረት ከኣፕሪል 25  ጀምሮ ከሌሎች 8 ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች ጋር  የሚጽፍበት እጆቹ ካቴና ጠልቀውበት፣ የሚናገርበት ኣፎቹ  ታግደው ክስም ሳይመሰረትበት  ከ72 ቀን በላይ በእስር ላይ መሆኑ ኣይዘነጋም።

 

 

Filed in: Amharic