>
5:13 pm - Tuesday April 19, 7261

"የትዳር ቀለበቴን ሲቀሙኝ "ምን ያደርግልሃል? አትወልድ!" ነበር ያሉኝ!!! ዮናስ ጋሻው

“የትዳር ቀለበቴን ሲቀሙኝ “ምን ያደርግልሃል? አትወልድ!” ነበር ያሉኝ!!! ዮናስ ጋሻው 
* ገ/ እግዚአብሔር  “ህግ ባይኖር እኔ ነበርኩ የምገድልህ”  ዛሬም ቢሆን ፈታንህ ማለት ከእኛ ቁጥጥር ውጭ ነህ ማለት አይደለም” ነበር ያለው
ጸሃፊ: የበላይ ናሁሰናይ
 ዮናስ የተያዘው አዲስ አበባ ነው። እንደተያዘ ወደ ኮተቤው የደህንነት ቢሮ ይወስዱታል። ጨካኙ ተክላይ መብርሃቱ እየበረረ በለሊት ይደርሳል። ከለሊቱ 9 ሰዓት ላይ ሊገድለው ሲል የያዙት ደህንነቶች “ኧረ እህቱ አይታናለች” በማለታቸው ያደገው ፀጉሩ ላይ ይተኩስበታል። እህቱ ባታየው ገድለውት ነበር። ከኮተቤ ማሰቃያ ወደ ጦር ሀይሎቹ ሌላኛው ድብቅ እስር ቤት ይወስዱታል። ዮናስ የደረሰበት ሰቅጣጭ ተግባር እንዲህ ሲል ይናነራል…
.
“…ማታ 2 ሰዓት ሰቅለውኝ ሌሊት 6 ሰዓት ላይ  ያወርዱት ነበር በምርመራ ወቅት ከሚደረገው ደብደባ በላይ በማንነቱ ላይ የሚፈፀመው ዘለፋ  ጥላቻና ብቀትን ያዘለ መሆኑ ቅስም ሰባሪ ነበር ይላል።
.
ብልቱ ላይ ሁለት ሊትር ውሃ፣ እንዲሁም ፍሬዎቹ ላይ ሁለት ሊትር አንጠልጥለውበታል። በአንዴ አራት ሊትር ማለት ነው። በዚህ ምክንያት ፍሬዎቹ ፈሰዋል። ዘቅዝቀው እንደሰቀሉትም ይናገራል። ከተሰቀለበት መሬት ላይ ሲጥሉት ወገቡን ተመትቷል። በዚህ ምክንያት ነርቭ ጉዳት ደርሶበታል።
.
ከዛም ወደማዕከላዊ! ገና ከመነሻው ደህንነቶቹ ዮናስን ሲይዙት የትዳር ቀለበቱንም ቀምተውታል። ሲቀሙት “ምን ያደርግልሃል? አትወልድ!” ነበር ያሉት። ምን እንደሚደርጉት ያውቃሉና። ወደማዕከላዊ ከተዛወረ በኋላ ባሉት መሰረት እንዳይወልድ አድርገውታል።
.
“አንድ ቀን ከአስከሬን ጋር አሳድረውኛል ግፉ ግን በዚህ አያበቃም አንዲት ሴት መርማሪ ፊቴ ላይ ትሸናብኝ ነበር እኔም ለእርሷ አፍር ነበር ብቻ ያላደረጉት ነገር የለም። መርማሪዎች ብቻ ሳይሆን የቂሊንጦ ኃላፊዎችም ቢገድሉኝ በወደዱ ነበር።  የሚለው ዮናስ ከእስር ሲፈታ ገብረእግዚ የተባለ ሀላፊ “ህግ ባይኖር እኔ ነበርኩ የምገድልህ” ዛሬም ቢሆን “ፈታንህ ማለት ከእኛ ቁጥጥር ውጭ ነህ ማለት አይደለም” ነበር ያለው።
.
የዮናስ ስቃይ የከሳሾችን ስሜት እንኳ ይፈታተናል። ለምሳሌ የ19ኛ ችሎት ዳኞችን አንገት አስደፍቷል።
“መናገር አትችልም” ሲሉት ሱሪውን አውልቆ ጉዳቱን ሲያሳይ ፀጥ ብለው አስጨርሰውታል። በከሳሽነቱ ለታወቀው አቃቤ ሕጉ ምክትል ብርሃኑ ወልደሰማያት ሱሪውን አውልቆ ሲያሳየው ያ ጨካኝ ብርሃኑ አልቅሷል።
Filed in: Amharic