>

ስለ አንዳርጋቸው ሳስብ [ሄኖክ የሺጥላ]

ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ ሳስብ ዛሬ መተኛት አልቻልኩም። ከእንቅልፌ ተነሳሁ፣ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፣ ተመልሼ በማልቀሴ ተናደድኩ።HENOK YESHITILA & ANDARGACHEW TSGIEለማን ነው የማለቅሰው፣ ለአንዳርጋቸው ወይስ ና ተከተለኝ ሲለኝ ላልተከተልኩት እኔ ? ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሰአታት በፊት የተናገሩት ነገር ትዝ አለኝ ።”ይሄ የአንዳርጋቸው ጽጌ ለወያኔ ተላልፎ መሰጠት አንገት አያሰብርም ያሉት” ከዚያ ደሞ “Don’t get mad get evil ” ያሉት። እኔ ግን ሁሉንም መሆን ነው የምፈልገው። ቀጥዬም አንዳርጋቸውን እኔ መተካት አልችልምን ስል ራሴን ጠየቅኩ ( ልብ ዓርጉ መሆን አላልኩም መተካት ነው ያልኩት ፣ በግብር ማለት ነው ) ። ውስጤም መለሰለኝ ” ትችላለህ አታመንታ እንጂ አለኝ ” ልጄን ከመኝታ ቤቱዋ ሄጄ ተመለከትኩዋት፣ ኩርትም ብላ ተኝታለች ( እንደዚህ ተኝታ አይቼያት አላውቅም ፣ ምናልባት የማስበው ነገር ይሁን አስተኘቱዋን፣ መኮራተሙዋን ያጎላብኝ ? አላውቅም !) ልዩ ሄኖክ ገና ሁለት አመቱዋ ነው ፣ የአባት ፍቅር አልጠገበችም፣ በእርግጠኝነት ትፈልገኛለች፣ አብሬያት ብሆን ደስ ይለኛል፣ ግን ሀገር ፣ ክብር፣ ወገን ፣ዘመድ የሌለው ልጅ እንደወለኩ ሳውቅ የልጄን ትንሽነት ፣ የልጄን ልጅነት ረሳሁት ፣ ይልቅስ ምን ባደርግ ለልጄ ሆነኛ አባት ልሆን እችላለሁ አልኩ ፣ መልሱ አንድ እና አንድ ብቻ ነበር ፣ የአንዳርጋቸው ጽጌን ፈለግ መከተል፣ አንዳርጋቸው ጽጌ የጀመረውን መቀጠል ፣ ሌላ አንዳርጋቸው መሆን ፣ ሌላ እምቢተኛ መሆን ። ወደ-ማይቀረው ትግል ለመቀላቀል ፣ መሬት ቆንጥጦ ይሄን የዘመን ችንካር ለመጋፈት ወሰንኩ። ከዚያ ደሞ ቀጠልኩ

ኢትዮጵያ አሁን ግን ከእስከ አሁኑም በላይ በቃኝ

ህቅ አለኝ ግፍ መረረኝ
በቃላት ወይ በስሜት
በእንባና በምሬት
የማልገልጸው የማልለው
የማልናገውረው ነገር ይሰማኛል
ጥርሴ ይፋጫል
ድብን እርር ኩምትር
እንደ እሳት የሚለበልብ
ቃር የተሞላበት ትንፋሽ
ጸጉር መንጨት
ደሞ እንቅልፍ ማጣት
መሃል ላይ የልጅ አይነት ለቅሶ
በዚያ ላይ ከንፈር ተነክሶ ።
ሕይወት ይሄ ከሆነ ከሞት በምን ተሻለ ?
መኖር ከተባለ ይሄ
መሞት ምን ነበር ወገኔ ?
ደሞ ተናደድ
ከፈለክ ያርግህ እንደ እብድ
እበድና ሜዳ ውረድ
ሜዳ ወርደህ ፍሪዳህን እንዳባትህ በሰይፍ እረድ

አልኩት ልቤን ….

Filed in: Amharic