>

እድለኞቹ የወንበዴ እስረኞች!!! (ቹቹ አለባቸው) 

እድለኞቹ የወንበዴ እስረኞች!!!
ቹቹ አለባቸው 
 
* እኒህ የተከዜ ማዶ ሰወች ስለ ህግ የበላይነት ስለ ሰብአዊ መብት ማዉራት መጀመራቸው ታላቅ ፌዝ ነው። አማራው ኦሮሞው ደቡቡ ሱማሌው ሌላውም በህወሀት ወንበዴ ቡድን በዘራቸዉ ከእነርሱ አለመሆኑ ወንጀል ሆኖ ሲታሰሩ፣ ቶርች ሲደረጉ ፣ ሲኮላሹ … የት ነበሩ???
እናንተ የተከዜ ማዶ ወንድም/እህቶቻችን  ኖሮን ልመዷት።  በዚህ ሁለት ቀን ዉስጥ የተወሰኑ እና  ቀጫጭኖቹ የሜቴክና የሰዉ በላዉ የቀድሞዉ ደህንነት መዋቅር አንዳንድ አጋሰሶች ተለቃቅመዉ ወደ ከርቸሌ ተወርዉረዋል የሚለዉን ዜና ተከትሎ: አንዳንድ የወዲያ ማዶ ሰወች ጩኸት ተበራክቷል አሉ። ለነገሩ ሰወቹ እንኳን የሚያስጮህ ነገር አግተዉ ከድሮዉም ጨኸት ይወዳሉ።  
 
ለሁሉም አሁን አሁን “አትፍረድ ይፈረድብሀል” የሚባለዉ አባባል  እየደረሰ መሰለኝ: ፈራጆቹ ሊ ፈረድባቸዉ ነዉ።  
 
ሰሞኑን ታሰሩ የሚባሉት ግለሰቦች እኮ: ቀላል ወንበዴወች አይደሉም: እነዚህ አካላት: ይችን አገር ና ዜጎቿን አጥንታቸዉን ያስቀሩ ዘራፊ:ገራፊና ገዳይ ግለሰቦች ናቸዉ ተብለዉ የሚጠረጠሩ አረመኔወች  ናቸዉ።ይሁን እንጅ  አንዳንድ የተከዜ ማዶ ሰወች: መንግስት በነዚህ ወንበዴወች ላይ እየወሰደ ያለዉን ህግ የማስከበር እርምጃ: በበጎ አልተመለከቱትም: እንዲያዉም ሆን ተብሎ የተከፈተ ጥቃትና ህግና ስርአትን ያልተከተለ: ሰብአዊ መብትንም የሚጋፋ ነዉ ሲሉ ሰማናቸዉ።
 
ወይ ጊዜ! የተከዜ ማዶ ሰወች: ስለ ህግ የበላይነት: ሰለ ሰብአዊ መብት ማዉራት? አማራና ኦሮሞ በህወሀት ወንበዴ ቡድን በዘራቸዉ ሲታሩረ:ቶርች ሲደረጉ:ሲኮላሹ ወዘተ እነዚህ ተከዜ ማዶወች የት ነበሩ? ለሁሉም “ጅብ በማያዉቁት አገር ሂዶ ጀንዲ/አጎዛ አንጥፉልኝ አለ” ነዉ ነገሩ። እንጅማ እንዴት ብሎ:የተከዜ ማዶ ሰዉ: ስለ ሰብአዊ መብትና ህጋዊ እስራት ያወራል? በምን ሞራሉ? እየተዋወቅን? ስለሆነም እናንተ የማዶወቹ: ለማያዉቅሽ…..
 
 ለሁሉም እንግዲህ እነዚህ ወንበዴ ወገኖች: ተለቃቅመዉ : ሰዉ ሲያስሩበትና ሲገርፉበት ወደከረሙበት ቤት ገብተዋል። ሰወቹ እድለኛ ናቸዉ: ዛሬ እነሱ ሲያደርጉት እንደከረሙት ሁሉ: ገራፊ የለባቸዉ:ሰብአዊ መብታቸዉን የሚገፍ የለ: ብቻ በጥሩ ወቅት የታስሩ  ወንበዴወች ናቸዉ። አሳዛኙ ነገር ግን: እነዚህ ወገኖች : እንኳን በዚህ ወቅት ለመታሰር አበቃኸን ብለዉ ፈጣሪያቸዉን እንደማመስገን: ያልሆነ አርቲ-ቡርቲ ጩኸት ሲያሰሙ መደመጣቸዉ ነዉ።
 
በነገራችን ላይ: እነዚህ ወገኖች እንዲህ የሚጮሁት  እኮ ገና ግንዶቹ ወንበዴወች ሳይያዙ ነዉ እንዲህ የሚንጨረጨሩት።  ነገ ግንዶቹ ሲታሰሩ ምን ሊሉ ነዉ? የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመብን ነዉ ብለዉ የተለመደዉን የቀበሌ መሰል መግለጫ ያወጡ ይሆን? መግለጫ ማዉጣት ይወዳሉ ብየ ነዉ። 
 
ብቻ ምክራችን ልመዱት ነዉ!
 
መዉጫ:- 
 
ትኩረታችንን ከወንበዴወቹ እስራት ዜና ማሰራጨት: ወደ ቅማንትና የአማራ ህዝብ አብሮነት: እንዲሁም: ራያ: ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ላይ እናድርግ።  ሁሌም ቢሆን  የቅድምያ ትኩረታችን ለዉስጥ ጉዳያችን ይሁን!!!
Filed in: Amharic