>

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦ•ነ•ግ) መንገድ መርተሻል የተባለችው ድምፃዊት!!! (ተወልደ (ተቦርነ) በየነ) 

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦ•ነ•ግ) መንገድ መርተሻል የተባለችው ድምፃዊት!!!
ተወልደ (ተቦርነ) በየነ 
ተወልዳ ያደገችው አዳማ ነው።በ1952 ዓም ለሙዚቃ በነበራት ስሜትና ፍቅር የመጀመሪያውን አባሳደር ቲያትርን ባቋቋመው ተሰፋዬ ለማ አማካኝነት ተመልምላ ከፀሀዬ ዮሀንስ ፣መሀመድ አወል ፣ሻምበል በላይነህ ፣ኤልያስ ተባበል ፣ንዋይ ደበበ ፣ኪሮስ አለማየሁ ፣አብተው ከበደ ፣ጋር በመሆን የራስ ቲያትርን ከመሰረቱት ድምጻውያን አንዷ ነች ።ድምጻዊት አበበች ደራራ ከህዝብ ካስተዋወቋት በወቅቱ አጠራር አብዮታዊ ዜማዎች መካከል ተጠንቀቅ ዋ፣ያኒ ያጭቁርፈምቱ ጥቂቶቹ ናቸው።
    “የኮሚቴው አባላት አምቦ ቤተ መንግስት ተሰብስበው አምቦ ላይ  ማን ይገደል? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ ።በእጩነት ሶስት የአምቦ ከተማ አንጋፋ ኦሮሞዎች ቀርበው ነበር ።እነርሱም የድምፃዊት አበበች ደራራ አባት ደራራ ከፈኔ ፣ዳቃ ሙለታ እና ደንደና የተባሉ ነበሩ።በህዝብ ተቀባይነቱና በኦ•ነ•ግ ተጠርጣሪነቱ በድምፅ ብልጫ ደራራ ከፈኔ አሸነፈ ።ዝርዝር እቅድ ከተነደፈ በሁዋላም ደራራ እለት ፣ሰአትና ቦታ ተወስኖ ስብሰባው አበቃ ።”(የጋዜጠኛው ማስታወሻ) ከተስፋዬ ገብረአብ ገፅ 336 የተወሰደ
ጊዜው ከዛሬ 32 ዓመት በፊት የ3 ድምጻውያን ሥራ ያካተተ የጋራ አልበም በለገሀር ሙዚቃቤት አማካኝነት ይታተማል። በዚህ አልበም ውስጥ ተካተው ተወዳጅነትን ካተረፋ ሙዚቃዎች አንዱ የአበበች ደራራ” በሉ እንጅ” ነበር።በዚህ ሥራ የተካተተው አንዱ ስንኝ ድምፃዊ አበበች ደራራን ለኦ•ነ•ግ መንገገድ መርተሻል በሚል በወቅቱ ካድሬዎች ለከፍተኛ እንግልት እንደዳረጋትን ባንድ ወቅት አውግታኝ ነበር ።
አበበችን ያስጠየቃት የግጥም ስንኝ ቀጣዩ ነበር።
          ቄጠማዬ ሰመመኔ በናዝሬት አድርገህ ግባ ሻሸመኔ
        ጽጌረዳ የኔ አበባ በናዝሬት አድርገህ ግባ አዲስ አበባ
   በጣም የሚገርመው አበበችን ያስጠየቀዉ ይህ ሥራ በደራሲው የአሳዬ ዘገዬ የግል ታሪክ ዙሪያ የተሠራ  እንጅ እወደድ ባይ የወቅቱ ካድሬዎች እንዳሉት ኦነግን መንገድ ለመምራት የተሰራ  አልነበረም ።ዛሬ ይህን ታሪክ ያስታወስኩት በቅርቡ በሀገራችን የተፈጠረውን የለዉጥ ሂደት ተከትለው ወደ ሀገርቤት እዬገቡ ካሉ ድርጅቶች ኦነግ አንዱ በመሆኑ ነው። ከቀድምዎቹ የድርጅቱ አመራር ከነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ ፣አቶ ዳውድ ኢብሳ ፣ጀኔራል ከማል ገልቹ ፣ጀኔራል ኃይሉ ጎንፋን ጨምሮ ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ መግባት ጀምረዋል። በቅርቡም አቶ ገላሳ ዲልቦ እንደሚገቡ እየሰማን ነው ። “ኦነግ እንደ ሊሞዚን ይሄን ያህል ረጅም ነው እንዴ ገብቶ የማያልቀው?”እየተባለ ነዉ
Filed in: Amharic