>

ጨቅላ "ፖለቲከኛ ነን" ባዮች ወያኔ የወደቀው መንገድ በመዝጋት ና መኪና በማቀጥል ብቻ ይመስላቸዋል!!! (ወንድማገኝ ለማ)

ጨቅላ “ፖለቲከኛ ነን” ባዮች ወያኔ የወደቀው መንገድ በመዝጋት ና መኪና በማቀጥል ብቻ ይመስላቸዋል!!!
ወንድማገኝ ለማ
* ወያኔን ከማንም በላይ ተፋልመው መሰረቱን የናዱበት በጋዜጣ ፣ በመፅሔት ና በመፅሐፍ የስርዓቱን ብልሹነት ያጋለጡት ፣ የሚዲያ ተቋማትን ከፍተው ህዝብ እንዲያምፅ የቆሰቆሱት ጋዜጠኞች…
 
እየኖርክ ያለኸው ድኩማን ሐገር ላይ ነው ፣ ዛሬ ያንተን ቋንቋ መናገር የማይችሉትን ብታፈናቅልም በገዛ መሬትህ ላይ መሪዎቻችን ለሀያላኑ ሀገራት እስካላፈነደዱ ድረስ የመኖር መብት የለህም! ሀገርህ ከልመና ሳትወጣ ነፃ ወጣሁ ብሎ ነገር የለም! መጀመሪያ ለማኝ ሐገር ላይ የምትኖር ተመፅዋች ህዝብ መሆንህን እመን! ዛሬም በበሬ ብቻ እየታረሰ ነው የምትበላው ፣ ዛሬም ሱዳንና ሊቢያ ለመሰደድ የምትቋምጥ ነህ ፣ ዛሬም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ቻይናውያን የሰሩልህን ልብስ ነው የምትለብሰው ፣ አሁን እንኳን ይሄንን ፁሁፍ የምታነብበት ስልክ እንኳን በሀገርህ ልጆች የተሰራ አይደለም! ታዲያ ከምን ነፃ ወጥተህ ነው ነፃ አወጣኋችሁ የምትለን????
ጥቂቶች የ6 ወራት ጨቅላ ቦጠሊቃኛ ነን ባዮች ወያኔ የወደቀው (ወድቋል ብለን ካሰብን) መንገድ በመዝጋት ና መኪና በማቀጥል ብቻ ይመስላቸዋል። ወያኔን ከማንም በላይ ተፋልመው መሰረቱን የናዱበት በጋዜጣ ፣ በመፅሔት ና በመፅሐፍ የስርዓቱን ብልሹነት ያጋለጡበት ፣ የሚዲያ ተቋማትን ከፍተው ህዝብ እንዲያምፅ የቆሰቆሱት ጋዜጠኞች፣ ማህበራዊ ሚዲያውን ከፎቶ መለበጃነት አላቀው ወደ ታላቅ የፖለቲካ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የቀየሩት አክቲቪስቶች ና ወደድንም ጠላንም የአሜሪካና የወዳጆቿ መልካም ፈቃድ ነው።
.
 ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ የወያኔ ስርዓት አንገቱ እንደታረደ ዶሮ በመንደፋደፍ ላይ ነበር። ባለፉት 3 ዓመታት በተከታታይ የተካሄደው ተቃውሞ ባንድ ጊዜ የፈነዳ አይደለም። ለብዙ ጊዜያት ተለፍቶበታል። ብዙዎች ቀድመውን ተሰውተዋል ፣ ታስረዋል ፣ አካላቸው ጎድሏል። የተነቃነቀውን ስርዓት ለመገንደስ በተለየ መልኩ በየክፍለሀገሩ ያሉ ወጣቶች ለዓመታት ተዳፍኖ የተቀመጠውን እሳት አቀጣጥለውታል። ለዚህ ምስጋና ይገባቸዋል። በተለየ ለህዝብ ነው የታገልነው ብለው በሰበብ ባስባቡ አመስግኑኝ ካሉ ግን አደባባይ የወጡት ለራሳቸው ችግር ብቻ ነው ብለን እናስባለን።  ከዋነኞቻችን ውስጥ አንዱ ደግሞ ብርቱው እስክንድር ነጋ ነው! ይሄንን ታላቅ ጀግና ማንም ነፃ አላወጣውም! እንኳን እሱን ቀርቶ ራሱንም ነፃ ያወጣ የለም! እኔ ነኝ ነፃ አውጪህ እያልክ የምትኩራራ ሁላ ያንተ እኩዮች ምዕራባውያን የደረሱበት የአስተሳሰብ ደረጃ ደርሰህ ለማህበረሰብህ የሚጠቅምን ነገር አበርክት! ያኔ ነፃ አውጥቻችኋለሁ ሳትለን #ነፃ_እንደወጣህ እንመሰክርልሃለን!
ሺናሻ ላለው ህዝብ ፣ ሐመር ለሚገኙት ወገኖቻችን ፣ ስለሱርማ ህዝቦች…ድምፃቸውን ያሰሙ ጥቂቶች ናቸው። ጫፍ ና ጫፍ ያለው ሕዝብ ለአንዲት ሰከንድም ትዝ ብሎህ ሳያውቅ #የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እኛ ብቻ ነን አትበል!
እስኬው እንኳን ተወለድክልን! 
Filed in: Amharic