>
5:13 pm - Thursday April 19, 0379

አጼ ቴዎድሮስ ንግስናቸውን ያወጁባት ደረስጌ ማርያም!!! (ታደለ ጥበቡ)

አጼ ቴዎድሮስ ንግስናቸውን ያወጁባት ደረስጌ ማርያም!!!
ታደለ ጥበቡ
ደጃዝማች ውቤ ሲማረኩ ዐፄ ቴዎድሮስ ሀብትዎን ያምጡ አሏቸው፡፡ ደጃች ውቤም «ይህንን ሁሉ ገንዘቤን ለእግዝትነ ማርያም መስጠቴ የምድር እና የሰማይ መከራ እንዳታሳየኝ ነበር፤ አሁን እንዴት ላድርግ ከእርሷ ይቀበሉ እንጂ፡፡» አሏቸው፡፡ የደጃች ውቤ ሠራዊትም እየሸሸ ደረስጌ ገብቶ ደወለ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም «ስለ እግዝትነ ማርያም ብዬ ምሬዋለሁ» ብለው ዐዋጅ ነገሩ!!!
 
ደረሰጌ ማርያም ዙርያዋ በኖራ በተመረገ የድንጋይ ግንብ በታጥረ ኮረብታ ላይ ትገኛለች፡፡ የመግቢያ በሩ  ሰቀላ ሲሆን  ቤተ መቅደሱ ክብ ሆኖ አናቱ ላይ የወርቅ ጉልላት አለው፡፡በሮቹ እስከ ሦስት ሜትር በሚደርሱ ግዙፍ ግንዲላዎች የተሠሩ ናቸው፡፡ የመቅደሱ ወለል ከቅርቀሃ እና ከጠፈር በተሠራ አቴና የተሞላ ነው፡፡
ደረስጌ ጽርሐ ጽዮን ማርያም ትክሏ በአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን መሆንዋን የደብሩ ሽማግሌዎች ይገልጣሉ፡፡ በአጼ ሰርጸ ድንግል የተተከለች ናት የሚል ታሪክ አላት፤ በአድያም ሰገድ ኢያሱ ተሰራች የሚለውና የለም በ12ኛው ክፍለ ዘመን ነው የታነጸችው የሚለው የደረስጌ ታሪክም ገናናነቷን የሚያሳይ ነው።ነገር ግን አሁን ያለውን ቤተ መቅደስ አሠርተው የደበሯት እና ዛሬ ያላትን ክብር የሰጧት በ1810 ዓም ደጃዝማች ውቤ ናቸው።
ደጃዝማች ውቤ ትግራይን እና ስሜንን ሲገዙ ዋና መናኸርያቸውን ደረስጌ ላይ አድርገው ነበር፡፡ በዚያ ቦታ ላይ ቤተ መንግሥት እና የመሣርያ ግምጃ ቤት ነበራቸው፡ ቤተ ክርስቲያንዋን ለማሠራት ከሀገር ውስጥ እና ከባሕር ማዶ ዕውቅ መሐንዲሶችን አሰባስበው ነበር፡፡ ከውጭ ከመጡት መካከል ጀርመናዊው ዶክተር ዊልሔለም ሺምበር ይጠቀሳል፡፡
 የደብሩ ክልል ሦስት ጋሻ መሬት ሲሆን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ በሁለት ቅጽር እና በዐጸድ የተከበበ ነው፡፡ የመጀመርያው ቅጽር በጎንደር ከተማ እንደሚገኘው የዐፄ ዮሐንስ ቤተ መንግሥት በዕንቁላል ከፎቁ አናት ደውል ቤቱ ይታያል፡፡ህንጻው ደጃች ውቤ ሊነገሱበት ያስገነቡት መናገሻ ነበር፡፡ ዶክተር ዊልያምን አስጨንቆ የተገኘ የኪነ ህንጻ ጥበብ ነው፡፡  ከላዩ የሚገኘው 5 የፈረስ ጉልበት የሚመዝን ደውል ወገራ ድረስ ይሰማል የሚባለው 50 ኪሎ ሜትር የሚሰማ ግዙፍ ደውል ነው፡፡ የሰሜንና የኤርትራ ገዢ ሆነው አርባ ዓመታትን ያክል የገዙት መስፍን፣ በወቅቱ ገናና ነን ከሚሉ የዓለም ሀገራት ጋር ማህበር የገቡት ደጃች ውቤ ከደረስጌ ማርያም ተነጥለው የማይታዩ ሰው ነበሩ፡፡
ወደ ቤተ መቅደሱ ስትዘልቁ ደጃዝማች ውቤ ያስሳሉትን ሥዕል ታገኛላችሁ፡፡ የቤተ መቅደሱ በር እና መስኮት ለእያንዳንዱ እንጨት ተፈልፍሎ ጌጥ እየወጣለት የተሠራ ነው፡፡ ከበሩ ግራ እና ቀኝ ሁለት ነጋሪቶች አሉ፡፡በዚያ ዘመን የተሠራው ለማኅሌት እና ቅዳሴ ጊዜ መብራት ይሰጥ የነበረው የዘይት መቅረዝ ዛሬም ለታሪክ ይገኛል፡
ከበስተ ጀርባ ራሱን በቻለ ጠባብ ክፍል የደጃዝማች ውቤ መቃብር ቤት ይገኛል፡፡ የደጃዝማች ውቤ  ዐፅም በሳጥን ሆኖ  መጎናፀፊያ ለብሶ ይታያል፡፡የመቃብር ቤቱ ግድግዳው እና ጣራው በታሪካዊ ሥዕሎች የተሞላ ነው፡፡
ደጃዝማች ውቤ ቤተ ክርስቲያኗን ያሠሩት ከኖራ፣ ከድንጋይ እና ከጭቃ ነው፡፡ ኖራው ሰባት ዓመት ይቀበራል፡፡ በየጊዜውም ውኃ ይጠጣል፡፡ በሰባት ዓመቱ ይወጣና ከጭቃው ጋር እየሆነ ድንጋዩ ይያያዝበታል፡፡ ከዚያ በኋላ ንቅንቅ የለም፡፡ደጃዝማች ውቤ እንዴት ባለ ልዩ ውበት እንዳሠሯት አንደኛውን የዐፄ ቴዎድሮስ ዜና መዋዕል የጻፈው ወልደ ማርያም «ከባሕር ወዲህ እንደ እርሷ ድንቅ ተብሎ የሚነገር ሥራ የለም»ብ ሏታል፡፡
የደረስጌ ካህናት በአንድ ነገር ይመሰገናሉ፡፡ ደጃች ውቤ ከሰጡት ቅርስ እና ንዋያተ ቅድሳት መካከል አንድም እስካሁን አልጠፋም፡፡ በጣልያን ዘመን እንኳን ቤተ ክርስቲያንዋን ለመዝረፍ የመጣውን ጣልያን ቀጥታ ከዚህ በኋላ አልደርስም እነዲል አድርጋዋለች፡፡ በ1928 ዓም መጋቢት ሦስት ቀን ጣልያን በደብርዋ ላይ ያዘነበው የአውሮፕላን ቦንብ እንኳን እሳቱ ጢሱ አልነካትም፡፡የወርቅ አክሊል
የደረስጌ ቅርስ ተሠፍሮ ተቆጥሮ በሚገባ የተመዘገበ ነው፡፡በየዓመቱ ቆጠራ ይደረጋል፡፡ የሚገርመው ግን ቅርሱን ለመቁጠር ሁለት ወር ከአሥራ አምስት ቀን መፍጀቱ ነው፡፡ የአካባቢው ገበሬ ለቅርሱ ከፍተኛ ጥበቃ ነውየሚያደርገው፡፡ ዕቃ ቤቷ እና የያዘችው ዕቃ ሲተያዩ ወርቅን በቀዳዳ ኪስ እንደ ማስቀመጥ ነው፡፡ ከኖራ እና ከድንጋይ ተሠርታለች፡፡ ቅርሱ በቅርስ ላይ ተነባብሮ ተቀምጦባታል፡፡
ደጃዝማች ውቤ ደረስጌ ማርያምን ሲሠሩ አንድ ምኞት ነበራቸው፡፡ ዘመነ መሳፍንትን አክትመው በደረስጌ ማርያም መንገሥ፡፡ ለዚህም አቡነ ሰላማን ከግብጽ አስመጥተው ነበር፡፡ እናም የተሟላ ንዋያተ ቅድሳት ለደብሯ አበርክተዋል፡፡
=>የብር እና የወርቅ ከበሮ፤ 
=>ከፋርስ እና ከግብጽ የመጡ ምንጣፎች፤ 
=>ከብር እና ከወርቅ የተሠሩ የፈረስ ኮርቻዎች፤ 
=>70 ሳንቲ ሜትር ርዝመት ያላቸው ከጎሽ ቀንድ የተሠሩ ዋንጫዎች፤ ለደብሯ ሰጥተ ዋታል።
ደጃዝማች ውቤ እና ደጃዝማች ካሣ የካቲት ሦስት ቀን 1845 ዓም ቧሂት ላይ ጦርነት አደረጉ፡፡ ደጃዝማች ውቤም ተማረኩ፡፡ ቤቴል በሚባለው አምባ ላይም ያስቀመጡት ዕቃ ሁሉ ተማረከ፡፡ ዳጃዝማች ካሣም በአቡነ ሰላማ እጅ ተቀብተው በዚህችው በደረስጌ ማርያም የካቲት አምስት ቀን 1845ዓም ዐፄ ቴዎድሮስ ተብለው ነገሡ ፡፡
የዐፄ ቴዎድሮስ ዜና መዋዕል ጸሐፊ ደብተራ ዘነብ « ከአምባው ውስጥ የተገኘ የወርቅ እና የብር ዕቃ ለቁጥር አስቸገረ፤ ብርጭቆ እና ብርሌ ታናናሹ ዕቃ እንደ ሣር እንደ ሣር ቅጠል ሆነ፡፡ ሁለት መድፍ ነፍጡ ለሸክም አስቸገረ፤ ብሩም ለሠራዊትዎ ሁሉ ለመኳንንቱም ለአንዱ ሺ፣ነገሡ ላንዱ መቶ፣ ላንዱ ሃምሳ፣ ለአንዱ ሃያ፣ ላንዱም አሥራ አምስት፣ ላንዱም አሥር እየሰጡለት ለምጧትም እየሰጡለት እስከ ሸዋ ድረስ ሳያልቅ ነበር» በማለት ይገልጠዋል፡፡
ታሪክ ጸሐፊው ወልደ ማርያምም «ከአምባው የተቀመጠ ገንዘብ ተራዛሚው ነፍጥ ብቻ 500 ተቆጠረ፤አረቄ መርፌም ሁለት ጋን ተገኘ ይባላል» ይላል፡፡
ደጃዝማች ውቤ ሲማረኩ ዐፄ ቴዎድሮስ ሀብትዎን ያምጡ አሏቸው፡፡ ደጃች ውቤም «ይህንን ሁሉ ገንዘቤን ለእግዝትነ ማርያም መስጠቴ የምድር እና የሰማይ መከራ እንዳታሳየኝ ነበር፤ አሁን እንዴት ላድርግ ከእርሷ ይቀበሉ እንጂ፡፡» አሏቸው፡፡ የደጃች ውቤ ሠራዊትም እየሸሸ ደረስጌ ገብቶ ደወለ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም «ስለ እግዝትነ ማርያም ብዬ ምሬዋለሁ» ብለው ዐዋጅ ነገሩ፡፡
ምንም እንኳን ደጃች ውቤ በዚያ የመከራ ሰዓት አላዳነችኝም ብለው ቢፀፀቱም፤ ዐጽማቸውን አክብራ፣ታሪካቸውን አኑራ ትውልድ እንዲያስታውሳቸው ያደረገች፣ እስከ ዛሬም በጸሎተ ቅዳሴ እንዲታሰቡ ያደረገች ይህችው የደከሙላት ደረስጌ ማርያም ናት፡፡
ከዕቃ ቤቱ  በግራ በኩል አንድ ጥንታዊ ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃ በዚህ ቦታ ይገኛል፡፡ ወደ ሕንፃው በደረጃ በኩል ትወጣላችሁ፡፡ ከከዚያም በደረጃ ወደ መጀመርያው ፎቅ ስትወጡ በፊት ለፊቱ በኩል በረንዳ ታገኛላችሁ፡፡ ወደ በረንዳው ዝለቁ፡፡እነሆ አሁን የኢትዮጵያን ታሪክ በቀየረ አንድ ታሪካዊ ቦታ ላይ ቆማችኋል ማለት ነው፡፡ እዚህ ሠገነት ላይ ቆመው ነበር ዐፄ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት መሆናቸውን ያወጁት፡፡ የዘመነ መሳፍንት ማብቂያ እና ኢትዮጵያ ወደ አዲሱ ዘመን መሸጋገርዋ የታወጀው እዚህ ቦታ ላይ ነበር፡፡ ዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው ከዚህ ሠገነት ላይ ነው፡፡
ዐፄ ቴዎድሮስ ንግሥናቸውን ያወጁበት ሠገነት ከአናቱ በተያያዘ ከባድ እና ረዥም ብረት የታሠሩ ሁለት ደወሎች አሉ፡፡ ትልቁ ደወል አሥራ አምስት የፈረስ ጉልበት አለው ይባላል፡፡ ይህንን ደወል ከጀርመን ያመጡት ዶክተር ዊልሔለም ሺምበር ናቸው፡፡ ደወሉ በአሁኑ ጊዜ በዓመት ሦስት ጊዜ ብቻ ይደወላል፡፡ ለኅዳር 21፣ ለኅዳር 25 ለመርቆሬዎስ በዓል እና ለጥር 21 ቀናት፡፡ በጥንት ዘመን ደወሉ ሲደወል ከደረስጌ በግምት 200 ኪሎ ሜትር እስከሚርቀው ወገራ ድረስ ይሰማ ነበር ይባላል፥በትልቁ ደወል ላይ ” Aloysij Lucenti Funde Romae  የሚል ጽሁፍ አለ፤፤
በትንሹ ደወል ዙርያ እንዲህ የሚል ጽሑፍ ይነበባል፦
louis Del A Strasbourg L’an 1848 faite par”
የደወሉ ውፍረት ወደ ሃያ ሳንቲ ሜትር ይጠጋል፡፡ ከአግዳሚው ጋር በሚገባ በብረት ታሥሯል፡፡ አግዳሚው ደግሞ ከግድግዳው ጋር ፡፡
ጽሑፉ እንዲህ ይላል ፦
In Honorem Dei AC Beatae Marae birginis Anno Domini MDCCXLIII
ቤተ ክርስቲያንዋን የሚጠብቃት ኃይለ እግዚአብሔር ነው፡፡ ኢጣልያ ኢትዮጵያን እንደ ወረረ በ1928 ዓም መጋቢት 3 ቀን ለሦስት ሰዓታት ያህል በደረስጌ ማርያም ላይ የቦንብ ናዳ ከአውሮፕላን አወረደባት፡፡እንደ ሠለስቱ ደቂቅ ጢሱ እንኳን አልነካትም እነኳን እሳቱ፡፡
በዓመቱ የቦንብ ናዳውን ያዘዘው የጣልያን ተጎዳኝቷል ጦር አዛዥ ወደ አካባቢው ሲመጣ በቤተ ክርስቲያንዋ ላይ ምንም እንዳልተከሰተ ያያል፡፡
«እኔ ዬስ ጉግሳ ቤተ መንግሥት መስሎኝ እንጂ እንዲህ ያለች ባለ ተአምር ቤተ ክርስቲያን መሆንዋን መቼ ዐወቅኩ» ብሎ ተፀፀተ ይባላል፡፡
ይህ ባለ ሥልጣን ከቤተ ክርስቲያንዋ ዐጸድ ለባንዴራ ማንጠልጠያ የሞሆን እንጨት ሊያስቆርጥ ሲነሣ ካህናቱ «ተው መቅሰፍት ይወር ድብሃል፤ እንኳን ዛፏን ቆርጠው በአጠገቧ በበቅሎ አታሳልፍም» ይሉታል፡፡ እርሱ ግን የሚመጣውን አየዋለሁ ብሎ ማስቆረጥ ይጀም ራል፡፡ወዲያው በግቢው ውስጥ በበቅሎ ሲያልፍ ከበቅሎው ወድቆ ተሰበረ፡፡ አጃቢዎቹ ወዲያው አፋፍሰው ወደ አንምድ ጥግ ሲወስዱት ሞተ፡፡
1930 ዓም ደግሞ ሌላው የጣልያን ጦር አዛዥ ለሞቱበት ወታደሮች በግቢው መቃብር ሊያስቆፍር ሲነሣ የደብሩ አለቃ እና ሽማግሌዎች ከለከሉት፡፡ በዚህ ተናድዶ ሕዝቡን እፈጃለሁ ብሎ ሲነሣ መብረቅ ሐምሌ 21 ቀን ወርዶ እርሱን እና ባንዴራውን ለይቶ መታው፡፡
Filed in: Amharic