>

ወያኔ የሚለውን ታሪክና ስም - ህወሓት ከራያ አብዮት የሰረቀችው ነው!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ወያኔ የሚለውን ታሪክና ስም – 
ህወሓት ከራያ አብዮት የሰረቀችው ነው!!!
                   
 ዘመድኩን በቀለ 
 
~ በቀዳማዊ ወያኔና በሁለተኛው ወያኔ መካከል ምንም የታሪክ ግንኙነት የለም። ሁለተኛው ወያኔ አሁን ራዮች እያደረጉ ያሉት ትግል ነው። 
 
~ ራያ ከትግሬ ጋር በዘርም በባህል አይገናኝም “
 የትግራዩ ምሑር ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ
ህወሓት እንደ ድርጅትም ሆነ አባላቶቿ እንደ ግለሰብ የሚታወቁት በሌብነት ነው። የህወሓት ሌብነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ  ” ህወሓት ሌባ” የሚለው መፈክር ያልተሰማበት ሰላማዊ ሰልፍ የለም ( አሁን ደግሞ የቀን ጅብ)። የሚገርመው ግን “ወያኔ” የሚለው ስምና ታሪክ ራሱ ከራያ አብዮት የተሰረቀ መሆኑ ነው። ሕወሓት መስረቅ ባህሏ ስለሆነና ስለማያሳፍራት ሁለተኛ ወያኔ ብላ ሰየመችው እንጂ በመጀመርያውና ህወሓት ሁለተኛ ወያኔ ብላ በሰየመችው ህወሓት መካከል ምንም ዓይነት የታሪክ ሰንሰለት የለም። ዋቢ ልጥቀስ።
በኢህአፓነታቸው የሚታወቁትና አሁን አሁን ደግሞ  በመፍቀሬ ህወሓትነታቸው የሚታሙት የአክሱሙ ተወላጅ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ  እ ኤ አ በ 2009 The Ethiopian Revolution : war in the Horn of Africa የሚል መጽሓፍ አሳትመዋል።
በዚሁ መጽሓፋቸው ገጽ 81 ላይ ስለ ወያኔና ራያ እቅጭ እቅጩን ጽፈውታል። በሆባልትና ዊሊያም ስሚዝ ኮሌጅ የታሪክ መምህር የሆኑት ትውልደ አክሱሙ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ
” ራያ ትግሬ አይደለም። በራያና በትግሬ መካከል ቁልጭ ያለ የዘርና የባልህ ልዩነት አለ” በማለት ራያ ትግሬ አለመሆኑንና በራያና በትግሬ መካከል ግልጽ ያለ ልዩነት መኖሩን ገልጸው ” በቀዳማዊ ወያኔና ህወሓት “ሁለተኛ ወያኔ” ባለችው ትግል መካከል ምንም ዓይነት የታሪክም ሆነ የዓላማ ግንኑነት የለም። ወያኔ የሚለውን ስም ህወሓት ይሉኝታ የሌላት ሌባ ስለሆነች የተጠቀመችበት ነው ” ብለው ፍርጥ አድርገው አስቀምጠውታል።
★~ ፩፦ ራያ ከትግሬ ጋር በዘርም ሆነ በባህል አይገናኝም።
The Ethiopian Revolution : war in the Horn of Africa  page 81 paragraph 2
” Raya / Azebo and Wajerat , who instigated the revolt ( first weyane) , remained largely indifferent or hostile to the ” second weyane” ( kalaay weyane) , as the 1975 revolt is called by its makers. Part of the reason was their bitter memories of betrayal ; the other part was that the Raya/ Azebo are ETHNICALLY and CULTURALLY different from the dominant group ( Tigray) “
ምልስ አማርኛ ትርጉሙ እንዲህ ይነበባል ( ትርጉሙ ቃል በቃል አይደለም)
“ህወሓት ሁለተኛ ወያኔ ብላ የሰየመችው ትግል ሲጀመር እውነተኛውንና የመጀመርያውን ወያኔ በ1943 ዓ.ም ( እኤአ) የጀመሩት የነ ዋጀራት ራያ አዘቦ ሕዝብ ግን የህወሓትን ትግል አይደግፉትም ነበር።እንደውም የህወሓት ተቃዋሚና ቀንደኛ ጠላት ነበሩ። ራዮች እና ዋጀራቶች ለህወሓት ጠላት ወይም ስሜተ ቢስ የሆኑት በሁለት ምክንያት ነው። የመጀመርያው (በትግራይ) በደረሰባቸው መራራ የመከዳት ስሜት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እነ ራያ አዘቦ ዋጀራት ከትግራይ ጋር በዘርም በባህልም ልዩ ስለሆኑ ነበር። …”
ራያ – ከትግሬ በዘርም በባህልም ከተለየ ለምን ትግራይ ክልል ውስጥ እንዲሆን ተፈለገ? ቢያንስ ለምን ልዩ ዞን እስካሁን አልተፈቀደለትም? ለሌላው የተፈቀደው ማንነት ራያ ላይ ሲደርስ ለምን ቆመ? የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንድ ማንነት የሚወሰነው በቋንቋ፣ በዘር፣ በባህል፣ በስነ ልቦና እንደሆነ ይተነንናል። ራያ በዘር ትግሬ አይደለም። ባህሉም ከትግሬ አይመሳሰልም። ሕገ መንግሥቱ ራያ ላይ ሲደርስ ለምን ልምሾ ሆነ? ግልጽ ነው። ራያን መሬቱን እንጂ ሕዝቡ ስለማይፈለግ ነው።
★~ ፪፦ በቀዳማዊ ወያኔና  ህወሓት ሁለተኛ ( ካልአይ) ወያኔ በምትለው የወንበዴ ድርጅት መሃከል የታሪክ ግንኙነት የለም።
እኚሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁር ከላይ በተገለጸው መጽሐፋቸው ላይ ይሄንኑ ሀቅ አስቀምጠውታል The Ethiopian Revolution : war in the Horn of Africa  page 81 paragraph 2
” Another interesting aspect of the first and second weyane dialectic is that many , if-not most, of the leading elements of the armed struggle were the children and grand children of those who opposed  the 1943 revolt and took part in its brutal suppression or who stood aside until the winner was known. Where si the historical continuity of nationalist resistance ? It didnt matter. The TPLF was in search of a foundation myth and the  1943 uprising provided it”
ምልስ አማርኛ ትርጉሙ እንዲህ ይነበባል ( ቃል በቃል አልተተረጎመም)
“በመጀመርያውና በሁለተኛው ወያኔ ( ህወሀት) መካከልም የሚገርም ጉዳይ አለ። ይሄውም ብዙዎቹ የህወሓት መሪዎች – የመጀመርያውን የራያን ቀዳማይ ወያኔ ሲቃወሙ የነበሩና በኋላም የራያን ሰዎች ( አብዮት)በጭካኔ ያጠፉ ሰዎች ልጆችና የልጅ ልጆች መሆናቸው ነው። አባቶቻቸው እና አያቶቻቸው የመጀመርያውን የራያን የወያኔ አብዮት በጭካኔ አጠፉ የገዳዮቹ ልጆችና የልጅ ልጆች  ደግሞ ሁለተኛ ወያኔ ብለው ተነሱ። ስለዚህም  በመጀመርያውና በሁለተኛው ወያኔ መካከል ምንም የታሪክ ግንኙነትና ቀጣይነት ( ሰንሰለት) የለም። ያለው ታሪክ ያጥፊና ጠፊ ነው። ህወሓት ግን ከጅምሩ ይሉኝታና ነውር አልፈጠረባትምና የቀዳምዊ ወያኔን ስምና ታሪክ በመስረቅ ሁለተኛው ወያኔ ብላ አዲስ አፈ ታሪክ ደረሰች።”
የመጀመርያው ወያኔ የራያ አመጽ ነው። ያመጹትና የተዋጉት ራዮች ናቸው። አመጹንም ወያኔ ብለው ሰየሙት። ህወሓት 2ኛው ወያኔ ብላ የተሰረቀ ታሪክ ተቀጣይ ያደረገችው ግን በትግራይ ኤሊቶች የተጀመረ  ነው። አንዱ የራያ። አንዱ የትግሬ። የራያን የመጀመርያውን ወያኔ በጭካኔ ያጠፉት ሰዎች የልጅ ልጆች ሁለተኛ ወያኔ ብለው ሲነሱ ትንሽ እንኳ አላፈሩም። የመጀመርያውን የራያን ወያኔ አባቶቻቸውና አያቶቻቸው እንደጨፈጨፉት ያውቃሉ። የሁለቱም ትግል ዓላማ በሁሉም ነገር ልዩ እንደሆነም ያውቃሉ። ታሪኩ የአጥፊና ጠፊ – ገዳይና ተገዳይ እንደሆነም አሳምረው ያውቃሉ። ግን የመጀመርያው ወያኔ ትልቅ ስምና ዝና ስለነበረው በራያ የወያኔነት ታሪክ ለመድመቅ ስማቸውን ሁለተኛው ወያኔ ብለው ስየሙት።
ሁለተኛው ወያኔ ሊባል የሚገባው ግን አሁን ራዮች እያካሄዱት ያለው ትግል ነው። ታሪኩ ተገልብጦና ሙሉው ስለማይነገር እንጂ  የመጀመርያው የራያ ወያኔ መነሻና እርሾ – ራዮች የትግራይ መሳፍንቶች ላይ ያመጹበት የትግል ታሪክ ነው። ሁለተኛው ወያኔ ሊባል የሚገባውም አሁን  በዘመናችን ራዮች በዘመኑ የትግራይ መሳፍንቶች የሚደርስባቸውን በደል ለመቃወም የጀመሩት አብዮት ነው።
“A thief , be it at the highest power echelon or at lowest berth of life, is a creature with too cursed and super-lowly a mind to know what belongs to him and what doesn’t. That is why he takes everything he finds in his way. And for this reason a thief is said to be a mindless dishrag. Our country has been ruled for the last 27 years by a bevy of mindless dishrags.”
Borrowing Freedom
በነገራችን ላይ በመጀመርያው ወያኔ የ እንግሊዝ አውሮፕላንና የኢትዮጵያ መደበኛ ጦር የገባው ደጃዝማች ኃይለሥላሴ ጉግሳ  አማካኝነት ነው። የአጼ ዮሐንስ የልጅ ልጅ የሆነውና በኋላም ከድቶ ባንዳ በመሆን ለጣልያን ያደረው ኃይለሥላሴ ጉግሳ የራያን አመጽ ሲሰማ አስመራ ላይ ሆኖ ሌላ ፕሮፓጋንዳ ጀመረ። ( ጣልያን ትዕዛዝ ሰጥታው ስለመሆኑ ይነገራል)።
“የራያ ሕዝብ ውጊያው ጸረ እንግሊዝ መሆኑንና የጣልያንን መምጣት አበክሮ ይፈልጋል”  ብሎ ያልሆነ መግለጫ አስመራ ላይ በመስጠቱና ጣልያንም ይህን ግጭት በማስፋት እንግሊዘን አስወጥታ ኢትዮጵያን ለመያዝ ልቧ ስላልሞተ መሳርያ በድብቅ ማስገባት ጀምራ ነበር። በወቅቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት  ዋዜማ ጣልያንና እንግሊዝ ፍጥጫ ውስጥ ስለነበሩ – እንግሊዝ ይሄ እንቅስቃሴ ባጭሩ እንዲቀጭ ለማድረግ ኢትዮጵያ ባስቸኳይ ሠራዊቷን ልካ አመጹን እንድታስቆም ጠየቀች። አልፎ ተርፎም አውሮፕላን እስከመስጠት ደርሳለች በማለት ወንድማችን ዘ-አዲስ ጦማሩን ይቋጫል።
ሻሎም !  ሰላም !
Filed in: Amharic