>

የመዐዛን ሹመት በሰማሁ ጊዜ !! (ሀብታሙ አያሌው)

የመዐዛን ሹመት በሰማሁ ጊዜ !!
ሀብታሙ አያሌው
እግዚአብሔር ምንኛ ቃሉን አጠፈ ?  በቀናት ሁሉ መጫረሻ ለእረፍቱ ለሰባተኛው ቀን (ለዕለተ ለቅዳሜ)  አንድ ቀን ሲቀረው በስድስተኛው ቀን በዕለተ አርብ አዳምን የስራው ሁሉ መጨረሻ አድርጎ ፈጥሮ ነበር።
ግን ግን  እግዚአብሔር ምንኛ ቃሉን አጠፈ ?  ማሟጠጫው የመሰለውን ሰው አዳምን ጥሳ፣ የስራ ቀኖቹን ተላልፋ ሔዋን (በ8ኛ ቀን) ትፈጠር ዘንድ ግድ ሆነ። ሴት ባቋራጭ የመጣች የእግዚአብሔር የማሟጠጫ ልጅ ናት። እናም…ወላጅ ወረተኛው እንዲሉ …የፈጣሪ ልብ ወደዚች ጨቅላ አደላ። አዳምን ጨምሮ ለእርሷ የተፈጠረ ሆነ። በመሆኑም ለወንድ ከተሰጠው የገሃድ ቃል በስተጀርባ ሴት እርሱን ጨምራ ትገዛ ዘንድ ከስውር ፍቅር የተበጀ ስውር እጅ ሰጣት…ወንድ ከዚያች እለት አንስቶ ምስኪንነቱን የማያውቅ ምስኪን ሆነ።
ወንድ በስውር ከተሻረበት የገሃድ ቃል በመነሳት ዓለምን ለመጠቅለል ባጅቷል። የሞንጎሎ መሪ ጃንጂስ ከሐን የዓለምን አንድ ሶስተኛ ምድር ጠቅልሏል። ግዛቴም ብሎታል። የሮማው ታላቁ አሌክሳንደርም እንዲሁ አድርጓል። ይህ ሁሉ ግን ለበላይዋ ሴት ቀለብ የተደረገ የዝና ክምችት ነበር። እያንዳንዱ ጦረኛ በልቡ የሚታጠቀው ተጨማሪ የጦሮ እቃ አለው። ያ የጦር ዕቃ ሴት ናት !!
 የአለማየሁ ገላጋይ ወርቃማ ቃላት ባይኖሩ ምን እል ነበር !!
                       አቦ ተባረክ
             በወ/ሮ መዓዛ ተስፋ አለኝ
 “ሴት ስለሆንን ሳይሆን ስለምንችል ነው”  በማለት መጀመሯ ልቤን አሙቆታል።  የኔም እምነት ይሄው ነው።
ከሕገ አራዊት ወዴት?
ሀይለገብርኤል አያሌው
የሕግ ልዕልና ፍትህ የማግኘት መብት ከሃገራችን ሰማይ እርቆ ቆይቷል :: ፍርድ ቤት የሰው ማረጃ ቄራ አቃቤ ሕጉ ጭራቅ :  ዳኞቹ አራዊት ሆነው ሕዝቡን ሲበድሉ ሕግ ሲያጣምሙና ፍርድ ሲገለብጡ ቆይተዋል :: የሃገራችን የፍትሕ ተቋም በዘመነ ወያኔ ደንብና ስርዐት : እውቀትና ሞራል : ሙያዊ ስነምግባርና ሰብዐዊነት የራቀው ተቋም ሆኖ በመገኘቱ የካንጋሮ ፍርድ ቤት የአራዊት ሸንጎ የሚል መጠሪያ መታወቂያው ሆኗል::
ሕወሃት በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የሕግ ልዕልናን ደፍጥጦና የመበቀያ ተቋም አድርጎ የፈጸመው ነውር ከሃጢያቱ ሁሉ ስርየት የማይገኝለት ነው::
ያ አስፈሪና አሳፋሪ የፍትህ መንበር አንዲት ውብና አዋቂ ሴት መሾሟን ሰምተናል:: መቼም ለአዲሷ ተሿሚ ሕሊና መጸለይ ይኖርብናል:: እኛ ያልሰማንው መንግስትም ያላወቀው እጅግ ብዙ ነውር የተሸከመ ግፍ የነገሰበት መስሪያ ቤት ከፖለቲካው ሰፈር ላልነበረ ለልጆች እናትና እንስት ለሆነች ተሿሚ ከባድ ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም::
ከመከራችን ሁሉ አስከፊ ከውርደታችን ሁሉ ነውር የሆነው :የመኖር ተስፋችንን ያጨለመው : የሃገር ባለቤት የመሆናችንን እውነት የገፈፈው : ሰው ሆነን ተፈጥረን ከሰው በታች ያወረደን የፍትህ ማጣት ነው::  እህታችን ወሮ ማዐዛ አሸናፊ ይህን ሁሉ ቀንበር ከላያችን እንደምታወርጂው ተስፋ እናደርጋለን:: ምሳሌና አርዐያም ሆነሽ ታሪክ ትሰሪያለሽ ከሕገ አራዊት ወደ ሕግ ልዕልና ታሸጋግሪናለሽ ብለን ተስፋ እናደርጋለን::
ዶር አብይ እስከዛሬ ካደረጉት ሹመት ሁሉ የላቀ ይህኛው ይመስለኛል:: የፓርቲ አባል ያልሆነች : ለቦታው የሚመጥን እውቀት ያላት : መልካምና የወገን ተቆርቋሪ የሆነች የጭቁኖች ተሟጋች ሴት
ለቦታው የምትመጥን ናት:: ጠሚ. በነካ እጃቸው የሚንስትሮችና የስራ ሃላፊዎችን ሹመት የካድሬነትና የፓርቲ መመዘኛ ማድረጉን ትተው ብቃትን ልምድንና እውቀትን እንዲያደርጉ እንመክራለን::
ተሿሚቷ ወሮ መዐዛ በሃቅ ለመስራት ፈጣሪ ይርዳሽ!
Filed in: Amharic