>

ዶ/ር  አብይ ታሪክን እየጠቀሱ አንድነታችንን ከመናገር ራሳቸው ጋር ያለውን እውነት ቢነግሩን ምናለ?!? (ቬሮኒካ መላኩ)

ዶ/ር  አብይ ታሪክን እየጠቀሱ አንድነታችንን ከመናገር ራሳቸው ጋር ያለውን እውነት ቢነግሩን ምናለ?!?
ቬሮኒካ መላኩ
ጎንደር ከ 500 አመታት በላይ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣ የአፍሪካ የፖለቲካና ኢኮኖሚ መጋገሪያ መዲና ከመሆኗ አንፃር  እንኳን 85 የኢትዮጵያ ብሄር ይቅርና የአለም ነገዶች ሁሉ ከስካንዲኒቪያን አገሮች ጭምር እየመጡ የሚተራመሱባትና የተዋለዱባት ከተማ ነበረች።
ጄምስ ብሩስ ከስኮትላንድ የአባይን  ምንጭ ለማጥናት መጥቶ  በአስቴር ፍቅር ለመነደፍ 2 ቀን አልፈጀበትም። አስቴርን አፈቀረ አገባ ወለደ ተዋለደ ። ይሄ ለምሳሌ ያክል የጠቀስኩት ነው። ፈረንሳዩ ፖንሴንትም እንደዛው ነው ።
የዚህ አይነት ብዙ ታሪክ አለ። ጎንደር በዛን ወቅት ከአዲስአበባ የምትበልጥ ከለንደን ጋር የምትወዳደር ሜትሮፖሊተንት ከተማ ነበረች።
የፈረንሳዩ ፀሃዩ ንጉስ Louis XVI (14ኛ)  ለታላቁ ኢያሱ አዲያም ሰገድ ደብዳቤ ሲፅፍ አፄ ኢያሱን  ” ጌታዬ ” እያለ በመጥራት ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ስለ አፄ ሱሲኒዮስ የተናገሩት እውነት ነው ። ስለአፄ ፋሲል የተናገሩት ግን ውሸት ነው። የአፄ ሱሲኒዮስ እናት ሱሲኒዮስን ስታረግዝ ሀይለኛ የፓወር ስትረግል ስለነበር  ከጎጃም ወደ ግንደበረት ሄዳ ኦሮሞዎች ጋር መግባቷ ፣ መውለዷና ሱሲኒዮስም ከኦሮሞወች ጋር እንደ ልኡል ተንቀባሮ ማደጉ በጣም ትክክል ነው። ኦሮሞዎች ሱሲኒዮስ በደንብ አሳድገውታል ። ተዋግተውለታልም። በዚህም የሸዋ ኦሮሞዎችን ሁሌ  አደንቃለሁኝ ።
በተረፈ አፄ ፋሲል በአባቱም በእናቱም አማራ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ከመውጣታቸው በፊት ጀምሮ ” አማራና ኦሮሞ ላይለያይ የተሰፋ ህዝብ ነው።” በማለት በጣም ያምናሉ ። የሁለቱ ህዝቦች አንድነት ማረጋገጥ እጅግ የሚያረካው መሪ ነው። ይሄ መቼም ደግ ነው ።  በተረፈ ዶ/ር  ታሪክን እየጠቀሱ አንድነታችንን ከመናገር ራሳቸው በእናታቸው አማራ መሆናቸውን ደፍረው ቢናገሩና ልጆቻቸው ከ75% በላይ የአማራ ዘር እንዳለባቸው ቢመሰክሩና ለኦሮሞ እንደሚሰሩት ሁሉ  ለአማራመ  በተግባር  ቢሰሩ አንድነታችን የት በደረሰ ኖሮ እላለሁኝ።
Filed in: Amharic