>

የአቶ ለማ መገርሳ አስተዳደር ፈተና ውስጥ ወድቋል!!! (ሀብታሙ አያሌው)

የአቶ ለማ መገርሳ አስተዳደር ፈተና ውስጥ ወድቋል!!!
ሀብታሙ አያሌው
* በቀጠለው ውጊያ አንድ የመንግስት ታንክ መቃጠሉ ተሰምቷል
በወለጋ አካባቢ የመከላከያ ሰራዊት ከኦነግ ታጣቂዎች ጋር እያደረገ ያለውን ውጊያ አስመልክቶ ከቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ጥያቄ የቀረበላቸው የመንግስት ሹመኛ ሲመልሱ ቀጥሎ የተመለከተውን ብለዋል።
“አሁን ትልቅ ችግር እያደረሰ ያለው የኦነግ ሰራዊት ሳይሆን የመንግስት ሰራዊት ነው!”
በቀለም ወላጋ ዞን በግዳም ከተማ የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ምትኩ ታከለ
የኦዴፓ መዋቅር በፅንፈኛ እና አክራሪ ብሔርተኞች እየተጠለፈ መሆኑን መከራከር ከጀመርን ሰንብተናል።
ማስታወሻ
ከ ሦስት ሳምንታት በፊት የኦነግ ሰራዊት በወለጋ እና ባሌ አካባቢ ወታደር መልምሎ እያሰለጠነ መሆኑን፤ ምሽግ ቁፋሮ መጀመሩን፤ ከነዋሪ ዜጎች መሳሪያ በግድ እያስፈታ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቄ ነበር።
በርካታ የኦሮሞ አክቲቪስት ነን የሚሉ አካላት መረጃውን ውሸት ነው ብለው ከማጣጣል አልፈው “የኦሮሞ ጠላትነት ማሳያነው፤  ለውጡን ለመቀልበስ ነው ” በሚል ተራ መከራከሪያ ጉዳዩን ለመሸፋፈን ሲጥሩ ነበር።
 ዛሬ በውጊያው ከመንግስትም ከኦነግ ታጣቂዎችም የሰው ህይወት እየጠፋ ንብረት እየወደመ ሲሆን በመንግስት በኩል አንድ ታንክ መቃጠሉም ተሰምቷል።  ነዋሪው አካባቢውን ለቆ እየሸሸ መሆኑን የአካባቢው ህዝብና አመራሮች ለሚዲያ እየገለፁ ነው።
ለዚህም ማሳያ ኢሳት በጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ያቀረበውን ዜና ይመልከቱ) 
በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በምስራቅ ጉጂ የኦነግ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት እርምጃ በመወሰድ ላይ ነው!!!
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ካለፈው አርብ ጀምሮ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ላይ የመንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ በብዙ ታጣቂዎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሷል። የኦነግ ወታደሮችን ትጥቅ መፍታት የተቃወሙ ወጣቶች በየአካባቢው የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያደርጉ ሰንብተዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውጥረቱ ዛሬም ድረስ መቀጠሉን ያነጋጋርናቸው የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ እና ዱጋ ዳዋ ወረዳዎች የኦነግ ደጋፊ ቄሮዎችና የመንግስት ወታደሮች የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውንና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኦነግ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን እንዲሁም ከመከላከያም የተጎዱ ወታደሮች እንዳሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
 ሁኔታው ያሳዘናቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ የወጣቶች ድርጊት በጣም እንዳሳዘናቸው፣ ወጣቶቹ የመረጡት የትግል ስልት ስህተት መሆኑንና ጫካ የገቡ ወጣቶች እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የክልሉ ምክትል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ እንደሚሉት ትጥቃቸውን ያልፈቱ የኦነግ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የተጀመረው እንቅስቃሴ መቀጠሉን ገልጸው፣ ከዚህ ውጭ ግን በክልሉ ከኦነግ ሰራዊት ጋር ጦርነት እየተካሄደ እንደሆነ የሚዘገበው ትክክል አይደለም
ብለዋል።
Filed in: Amharic