>

ሁሌም ምስጢር ያዘለው የወሎ ህዝብ ሽልማት!! (ሔቨን ዮሀንስ)

ሁሌም ምስጢር ያዘለው የወሎ ህዝብ ሽልማት!!
ሔቨን ዮሀንስ
አማራየ ነይ ሙሽራየ ቅኔው ተመችቶኛል :: የፍየል ሽልማት ትክክለኛ ስጦታ ነው :: ብራቮ ያባቶች ልጅ መሆን እንድህ ነው :: የወሎ ባህል አንባው ሽልማት ትዝ አለኝ ሃሃሃሃሃሃ
የአማራ ህዝብ መሸለም ይችላል :: ለመንግስቱ ሀይለማርያም ጫማ ሸለሙት ባህል አንባ ሰው ግጥም ብሏል ጫማውን ለካው በእግሩ ልክክ አለ ::መንጌም የእግሬን ልክ እንደት አወቃችሁ አላቸው አስራ ሰባት አመት የረገጠንን እንደት እንርሳው አሉት ::
መለስ ዜናዊም ወደ ወሎ አቀና ባህል አንባ ኢህአደጎችን ሰብስቦ ማላዘኑን ቀጠለ ::የቦረና ህዝብ ጀግና ነው :: ውለታ ውሎልናል ስልጣን እንድንይዝ ምናምን ብሎ የአማራን ትግል ጨፍልቆ ገደል ከተተው ከተሰራው ስራ አንድ ማንኪ ተናገረ እሷም እያመመችው ነበር :: በመጨረሻም ጋቢ ሸልመው ላኩት :: ጋቢው የሰጡት ሸማግሌ ማለት የሸለሙት ሸማግሌ ለመንጌና ለአፄ ሀይለ ስላሴ እንድሸልሙ የተመረጡ ነበሩ::  ዛሬም እርስዎ ይስጡ ተብለው ተመረጡ እንድህ አሉ በወጣትነቴ ለተፈሪ ሸልሜ ሸኘሁ በጎልማሳነቴ መንግስቱን ሸልሜ ሸኘው ዛሬ በድካሜ በሽምግልናየ ለገሰን መለስን ሸልሜ ስሸኘው በፍፁም ደስታ ነው አሉ ::
ነገሩ ወድህ ነው ለአፄ ሀይለስላሴ ጋቢ ሸልመው ነበር ከፈን ሆነ የወሎ ህዝብ በተፈጥሮ መዛባት ርሀብ ሲጎዳው ዞሮው አላዩም ነበር ::ይሁንና ወሎ የረገመውም የመረቀውም ጠብ አይልም እሳቸውም ወሎን በረገጡና በተሸለሙ ሰሞን ደህናሁኝ አለም ብለው አረፋ :: መንግስቱም ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ የጀግንነቱን ያህል ጥፋቱ አይሎ ነበርና ጫማ ሸለሙት ጫውም ለጉዞ የተሰየመ ነው ከሀገር ወጣ ::መለስም ጋቢውን ተሸለመ ከፈኑን ከወሎ ተቀበለ ::ከወሎ በተመለሰ ሰሞን ወደ ውጭ ሀገር ወጣ መብረቅ እንደመታው የአበበ ገላው ድምፅ አኮማሸሸው በዛው ወደማይቀርበት ነጎደ ::
እንድህ እያሉ ከሱቄ በር ቆመው አንድ አዛውንት ሲነግሩኝ የማያቋርጥ ሳቅ እስቅ ነበር :: አይ ልጀ አንቺ ሮጠሽ አልጠገብሽም አይገባሽም ችግራችን ሳቂ እንጂ ያላየነው ያልሆነው የለም የሚያየን አጣን እንጂ አሉ :: እኛ አማራዎች በይሉኝታ ተተብትበን ተጎዳን ሰውም አጣን :: እንደ ትናንቱ አይነት ሰው ቢኖረን ወ/ሮ ስህን ያለው የቀለም ቀንድል ፈሶ ሲደርቅ ዝም ይባል ነበር :: በዚህ ባለፍኩ ቁጥር ተንገበገብሁ ስንት ሙህር እንዳልወጣበት የከብት ማጎሪያ ያስመስሉት አይ ;;እያሉ ንደታቸውን ሲያመጡት እኔም አብሬ ከንፈሬን እየነከስኩ ቁጭት ውስጥ ገባሁ ይሁና በይ ሰላም ዋይ ልጂት ሄቨን ብለው እያዘገሙ ሄዱ እኔም ዛሬ የጠሚዶ ሽልማት ተመችታኛለች ሰናይ ሌሊት ይሁንላችሁ ለማለት ነው :: ነገ ሌላ ቀን ነው ::
Filed in: Amharic