>

የወልቃይት ጠገዴና ራያ ጥያቄን ከዶ/ር አብይ ጫናነት እንቀንስ (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

የወልቃይት ጠገዴና ራያ ጥያቄን ከደ/ር አብይ ጫናነት በመቀነስ ሀገራችን ኢትዮጵያን ወደ ልማት በማሰገባት ለውጣችን እናስቀጥል

ከሁሉ በፊት ከዚህ ኃሳብ ጋር የሚመጣ ተጠያቂነትም ሆነ ኃላፊነት የምወክለውን ድርጅት ቤተሰቤን ሆነ ጓደኞቸን የማይመለከት የኔና እራሴ ብቻ መሆኑን አረጋግጣለሁ።
መንገሻ ዘውዱ ተፈራ
ራያ (ራያ ስል ራያ አዘቦንና ራያ ቆቦ በማጠቃለል አንደሆነ ታወቆ አንዲነበብ አሳስባለሁ) በቅድሚያ ህገ ውጥ ዝርፊያን በህግ ማስከበርና ማስተካከል ሲገባ ከማንነት ጋር ማያያዝ የተሳሳት ማምታቻና ጊዜ መስጫ ላይ የጋራ ግንዛቤ ማግኘት አለብን።
ማንነት ማለት በአካባቢው ያልነበር፣ የለለና፣ መከሰቱ፣ እንግዳ፣ የሆነ በድንገት ሲከሰት ምንድን ነው፣ ማን ነው፣ከየት መጣ ወይም መጣች ተብሎ የሚጠየቅ ለአዲስ መጤ የሚሰጥ እንጅ ለተወላጅ የአካባቢው ባለቤት አይደለም።
በስፋት ሊቀርቡ የሚችሉ በርካታ ምሳሌዎች ማቅረብ ይህን ፁፍ ያረዝሙትና አነባቢዎች በመሰላቸት ሳታነቡትና ሳትረዱት አንዳትቀሩ ስለ ወልቃይት ጠገዴና ራያ አጭር ምሳሌ በማቅረብ ለማሳየት ልሞክር።
“በአንድ ሕግና መንግስት ባለበት ሐገር በሚኖሩ ቤተሰብ ቤት አንድ አጉራ ዘለል ጉልበተኛ በመምጣት ቤቶች ሲል አንኳኳ። ባለቤቶቹም ከላይ በገልፅኩት በትክክለኛው አጠያየቅ ከውጭ ድምፁ የሚሰማውን እንግዳ ማነህ በማለት ማንነቱን ለማረጋገጥና ምክንያቱን በመረዳት ለመርዳት ጠየቁት። “ባለቤቱዋን ያመንች በግ ላቷዋን ደጅ ታሳድራለች አንደሚባለው” የጀርባ አይዞህ ባይ ላኪዎቹን የተማመነው ይህ አጉራ ዘለል ጉልበተኛ ስለማንነቴ መጠየቅ አትችሉም ከዚህ ቤት ውጡ ብሎ ቤታቸውን ተቆጣጠረው። እነዚህ ሴራውን ያልተጠራጠሩ ከቤት የተባረሩ ቤተሰቦችም ሕግና መንግስት አለ በሚል እምነት በአካባቢው ላለው የመንግስት ተወካይ ነኝ ተብየ ማንነቱን ስለ አላወቁት ሰው ድርጊትና ሰለገጠማቸው ችግር አቤት አሉ።”
ይህ አቤቱታ የቀረበለት በመንግስት ስም የማፋናቀሉና ዘር ማጥፋቱ ዋና ፈፃሚና መሪ በሉ የማናውቀው የእናንተን ማንነት አንጅ የእሱን ማንነት እናንት ባታውቁ እኛ ስለምናወቀው ቤታችሁን መቆጣጠሩ አግባብ ነው ለቃችሁ ሂዱ ብሎአቸው አረፍ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ከ27 ዓመታት በላይ አሁንም ማንነታቸው የታወቁት ማንነት ጠያቂ ማንነታቸው ያላታወቀው ዘራፊ ወንበዴዎች የማነነት ባለቤት ሆነው ይኖራሉ።
የወልቃይት ጠገዴና የራያ ጉዳይም በዚህ መልኩ በህወሀት መንግሰት የማጭበርበሪያ የማንነት ጥያቄ ሰም የአማራ ክልልን መሬት ወርው የሚኖሩበት አይን ያወጣ ማን አለብኝነት ተግባር አንጅ ከማንነት ጋር የማይያያዝ ጥያቄአችን የማንነት ሳይሆን ከቤታችን የገባ ሌባን የማሰወጣት መሆኑን ልናምን ይገባል።
ህወሀት ይህን የሚያደርገው ከፍልፍል ጋሻ ጃግሬዎቹ አንዱ የሆነውን የድሮው ብአዴን የአሁኑ አዴፓን በመጠቀም ነው። የድሮው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ሁሉጊዜ ከህወሀት ፈጣሪው ተሰፍሮ በሚሰጠው የማስፈፀሚያ መርሃ ግብር ትዕዛዝ መሰረት ይህንን ወረራና መስፋፈት የማንነት ጥያቄ የሚል ማጭበረበሪያ በመጠቀም ሲችል በማስፈራራት ሳይችል በማታለል ከወለቃይት ጠገዴና ራያ ጀምሮ የአማራ ክልል ህዝብን እያስጨረሰ እጅግ በጣም አሰዛኝ አሳፋሪ አንገት አስደፊ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ሲፈፅም ቆይቶአል።
አሁን በቅርብ ግን ከኢትዮጵያ ህዝብ በደረሰበት ጫና “የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ብንሽሸው ብንሽሸው የማናመልጠው የእራሳችን ጉዳይ ነው“ በማለት በአንደበቱ ማረጋገጡ ይታወሳል። በዚህም መሰረት ተስፋን የሰነቁ ተሳዳጅ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች ለአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስትና አዴፓ (የአንድ ሳንቲም ዘውድና ጎፈር) ባቀረቡት ጥሪ መስረት የአማራ ክልል መንግሥትም ጥያቄአቸውን በመስማት የመፍትሔ ሃሳብ ለመስጠት ልዑኮች ሲልክ በወጣቶቹ የቀረቡት ጥያቄዎች፦
እኛ ተሳዳጅ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች በማንነት ጥያቄ መልስ ይገኝ አይገኝ ሳይሆን በአማራነታችን በአዲስ የተከፈተብን አፋጣኝ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በገለልተኛ ፀጥታ አሰከባሪ  ዋስትን እንዲቆምልንና አንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተወልደን ባደግንበት ቦታችን ተመልሰን እየሰራን እየተማርን ለመኖር የሚያስችል መፍትሔ ይሰጠን።
ይህ የማይቻል ከሆነ የህወሀት መንግሰት አሁን የእኛን ዘር በማጥፋት የአማራን ህዝብ በመውጋት በወራራና ዝርፊያ የያዘውን የሱ ያልሆነውን የወልቃይት ጠገዴና ራያ የአማራ ክልለ መሬት ለማስከበር እያደረገ ያለውን የሚሊሽያ ሰልጠና ምሽግ ቁፋሮ ትጠቅ በማስጠጋት ላይ ይገኛሉ። ይህንን ተግባር እናንትም ዝም ብላችሁ አትቀበሉትም ብለን እናምናለን። በመሆኑም የዚህ አብሪተኛ ተግባር የቁጭት ስሜት አሳድሮባችሁ ከቢጫ ዛፍ ሆነን ቢጫ ወፍ የመምታት ባህል ላለን ለእኛ ለወልቃይት ጠገዴ ጎንደሬና በሞይዘር ታምር ሰሪው ባለ ታሪክ የራያ ህዝብ ከጎናቸን በመሆን ትጥቅ ብቻ በማቅረብ እንድትረዱንና መሬታችን በአጭር ቀን በማስከብር ሰለማዊ ኑሮአችን አንድናረጋገጥ።
ነገር ግን አሁንም በሀገሪቱ በቁጠር ሁለተኛ የሆነው ሰፊ ህዝብ ወኪል የመንግሰት ባለቤት መሆናችሁን መቀበል ካልፈለጋችሁና ድሮ እንደነበራችሁት ለህወሀት በአሽከርነታችሁ መቀጠል ከመርጣችሁ አልቻልንም የሚል መልስ ስጡንና ከመሃል ውጡልን። ብሶታችን ለክልላችን ህዝብ በሎም ሁልጊዜም ከጎናችን ለመቆም ዝግጁ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ነፃነታችን እንድናስከብር ለእራሳቸን ተውት ናቸው።
የአማራ ብሔራዊ ክልልላዊ መንግስት ለነዚህ ግልፅና በጊዜ የተገደበ አጭር መልስ ፈላጊ ጥያቄዎች በጊዜው የሚሰጡት መልስ አንደልነበራቸው ብንረዳም ከዚያ ተመልሰው በ13/01/2011 የምንጠብቀው ጠንካራ መግለጫ መስጠት ቢሆንም የፈራ ተባ መግለጫ ሰጥተዋል። ይህንን መግለጫ ይሰጣሉ ብለን ያልጠበቅነው አሰይ አስይ ለጄ ቆመች ልጀ ቆመ በማለት የልጠበቅን ደግሞ ደካማ ፈሪዎች እያልን ተከታዩን በተስፋ ስንጠበቅ ነበር። ሆኖም ግን  ከስድሰት ወር በፊትና የ27 ዓመታት የአማራ ክልል መንግሥት ስውር ጌታ አብሪተኛው የህወሀት መንግሥት ንቀት በተሞላበት አዋቂ ለህፃን በሚጠቀምበት  አባባል የማልሰማ መሰለህ አንዲህ አይነት ድፍረት ለእኔ? በል አሁን ይህች “የተፋሁዋት ምራቅ ሳትደርቅ“ ይህችን መግለጫህን የሚሽርና ይቅርታ የሚጠይቅ መግለጫ እንዳታወጣ። ይህን አውጥተህ ባልሰማ ግን እኔ አንተን አያደረገኝ የሚል የዛቻ ትዕዛዝ አሰተላልፎአል።
ስለዚህ የአማራ ክልል መንገሥትም ለዚህ የህወሃትን በእብሪት ለተሞላ መግለጫ በሳልና የብስለታችን ልዩነት የሚያሳይ በስዓታት የተገደብ ጠንካራ መግለጫ በማውጣት ለተግባረዊነቱ ዝግጁ መሆን። እኛም መላው የአማራ ክልል ህዝብ ከኢትዮጵያዊያ ወገናችን ጋር በመሆን በአለፉት የሶስት ዓመት ትግል ተሞክሮአችን በመጠቀም ለወልቃይት ጠገዴና ራያ ጥያቄ ከጎናቸው በመቆም ህወሀትን ከትግራይ ህዝብ የሚነጥል ትግል በማድረግ ትግራይንም ጥቅም ካሰከራቸው ትንሽ ቁጥር ነቀርሳ የህወሀት ጥቅመኞች በማገላገል ለደ/ር አብይ ጫናን በመቀነስ ሀገራችን ኢትዮጵያን ወደ ልማት በማሰገባት ለውጣችን ለማስቀጠል እንነቃቃ አንታገል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
Filed in: Amharic