>

መግለጫ አምላኪ የሆነ "የወንበዴ" ቡድን ! (ቹቹ አለባቸው)

መግለጫ አምላኪ የሆነ “የወንበዴ” ቡድን !
ቹቹ አለባቸው
1. መግቢያ፡-
አዴፓ፤ ለህወሀት መንግስት እጅግ እየከበደው እንደመጣ፤ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ህወሀት፤አየዴፓ አመራር በአዳዲስ ወጣት የአማራ ልጆች መያዙ፤ላብ ላብ ብሏታል፡፡ እንደነ ደሴ ጥላሁንና ንጉሱ ጥላሁን የመሳሰሉት፤የአዲሱ ትውልድ አመራሮች፤የአዴፓን ነገር ሊዘይሩት እድሉን ማግኘታቸው፤ በህወሀት ዘንድ እጅግ ፍርሀትን አንግሷል፡፡ የክልሉ መንግስትም፤ዛሬ ላይ አማራ ክልል ያለው መንግስት፤ብአዴን የሚመራው መንግስት ሳይሆን፤አዴፓ የሚመራው መንግስት መሆኑን ማስመስከር ጀምሯል፤ብቻ ወቅቱ ለህወሀት በአማራ ክልል ውስጥ የለመደውን ነገር ሁሉ ለመከወን፤ እጅግ ከባድ ሆኖበታል፡፡ ስለሆነም ህወሀት፤በአሁኑ ወቅት፤ የአዴፓን ተወንጫፊ ሚሳየሎች መቋቋም ተስኖት፤ የሚይዘውንና የሚጨብጠውን ነገር አጥቷል፤ ገናም ያጣል፡፡ለዚህ አባባሌ፤ጥሩ ማሳያ የሚሆነው ፤ሰሞኑን በወልቃይትና ራያ፤አካባዎች የተከሰቱት መፈናቀሎችና ግድያዎች፤እንዲቆሙ፤ ይሄን ችግር ለመፍታት፤ የትግራይ ክልል መንግስት የቻለውን ሁሉእንዲሰራ፤ለዚህ በጎ ስራውም የአማራ ክልላዊ መንግስት ከትግራይ መንግስት ጎን እንደሚቆም፤አዴፓና የክልላችን መንግስት ያወጡትን በጎ መግለጫ ተከትሎ፤ከህወሀት በኩል የተሰነዘረው፤በጎ ያልሆነ ምላሽ ነው፡፡ሁላችንም፤እንደምናስተውሰው፤አዴፓም ሆነ የክልሉ መንግስት ያወጡት መግለጫ፤ለስለስ ያለ፤ማንንም ወገን የማያስቆጣ፤ህገ-መንግስትን መሰረት ያደረገ እንዲሁም፤ለወዳጅነት በር የሚከፍት ነበር፡፡ነገር ግን፤ለዚህ የአዴፓና የክልላችን መንግስት፤በጎ መግለጫ፤ ከ”ወንበዴው” ቡድን የተሰጠውን መግለጫ ይዘት ስንመለከት፤ህወሀት እጅግ ግራ የተጋባው፤ይይዘው ይጨብጠው ያጣ ቡድን እየሆነ መምጣቱን እንገነዘባለን፡፡
 
2. የ”ወንበዴው”ሕወሀት መግለጫ ዋና ዋና ይዘቶችና የኔ እይታ፤-
 
ከትላልቱ፤ የህወሀት መግለጫ፤የተገነዘብኩት አጠቃላይ ነገር ቢኖር፤የመግለጫው ዋነኛ ይዘት፤ ፤አዴፓና የክልሉ መንግስት፤ በሰላምና በመረጋገት ውስጥ ያለችውን፤ትግራይን እየረበሹ ነው፤ የሚል መልእክት ያለው ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ድርጊቱም፤ህገ-መንግስቱን የጣሰ፤ስለሆነ፤አዴፓና የክልሉ መንግስት ለዚህ ድርጊታቸውም፤ይቅርታ ይጠይቁ የሚል መንፈስ ያለው መግለጫ ነው፡፡ገራሚ ነገር ነው፡፡ አሁን አዴፓና የአማራ ክልል መንግስት በዚህ ደረጃ የሚታሙ ናቸው? ይልቁንስ ብአዴንና /አዴፓ እንዲሁም፤የክልሉ መንግስት፤የህወሀት ተላላኪ ናቸው ሲባሉ የከረሙ አይደሉንም? ይሄንን እውነታስ  “ወንበዴው” ህውሀት ሳይቀር የሚያውቀው እውነታ አይደለንም?
 ሕወሀት ግራ ተጋብታለች
አንዱን ነገር ለማብረድ ስትማስን፤ በሌላው በኩል ይፈርስባታል፡፡ ሕወሀት የእነዚህን ችግሮች እውነተኛ ምክንያት ፈትሻ፤አስተማማኝ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ፤ሰበቡን ከሌሎች ጋር ለማያያዝ ትሞክራለች፡፡ ሰሞኑን ደግሞ፤ በአዴፓ ላይ ያላትን ስሜት፤ በነ አቶ አብረሀ ደስታ ስታስነግር ሰንብታ፤አሁን ደግሞ በራሷ አንደበት፤በግልጽ ችግር እየፈጠረብኝ ያለው አዴፓ ነው ብላ መጥታለች፡፡ ይሄ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በተለይም እንደኔ ህወሀትና አዴፓ ምንም የሚያዛምዳቸው ነገር ስለሌለ፤ቶሎ መፋታት አለባቸው ብሎ ሲከራከር ለኖረ፤አንድ የብአዴን ታጋይ ደስታ ይሰጠዋል ብየ አምናለሁ፡፡ የትላንቱ የህወሀት መግለጫ የሚነግረን እውነታ ቢኖር፤እውነትም በአዴፓና በህወሀት መካከል አንዳች አብሮ የሚያኖር መሰረት የሌለ ስለመሆኑ በቂ ማሳያ ነው ብየ አምናለሁ፡፡
3. ግን ለምን ሕወሀት እንዲህ ወደ መወራጨት ገባች ?
ሁላችንም፤እንደምናውቀው፤ላለፉት 27 አመታት የአማራን ክልል፤ የነ አቶ በረከት ሥምኦንን እጅ በመጠቀም፤ በቀጥታ ሲያስተዳደር የኖረው፤ህወሀት ነው፡፡ የብአዴን ነገርና ክራሞት፤ክድን ብሎ ይብሰል ፡፡ ስለሆነም፤ሕወሀት እንደልቡ ሲዳክርበት የኖረውን የአማራ ክልለ፤ዛሬ ላይ ደርሰህ፤በቃህ ስትለው፤ ከባድ መረበሽ መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ሕወሀት፤የአማራ ህዝብ እና ብአዴን/አዴፓ ይሄንን ያክል ጠንክረውና ጉልበት አግኝተው፤ ባንዴ በዚህ ደረጃ ሕወሀትን ይዳፈራሉ፤ለህወሀት ፈተና ይሆናሉ፤ብሎ  አልጠበቀም ነበር፡፡ ግን ሆነ፡፡ ይሄ ሁኔታ ህወሀትን ይይዘው ይጨብጠው አስጠፋው፤ምክንያቱም ፤የአዴፓ ውሳኔ መብረቃዊ ሆነ፡፡ይሄ ሁኔታ ለህወሀት፤እንዲሁ በቀላሉ የሚዋጥለት አልሆነም፤ግራ መጋባት፤መደናገጥ፤ፍርሀት ወዘተ… በህወሀት ቤት ተፈጠረ፡፡
ለህወሀት ከባድፈተና ሆነው፤የአዴፓ እምቢተኝነት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ፤ ይሄንን ሁኔታ፤በአዴፓ ውስጥ ሆኖ፤ ሁኔታውን ለመቀየር የሚሰራ የእነ በረከታዊያን አይነት ሰዎች፤ አዴፓ ውስጥ ከነጭራሹ መጥፋታቸው ነው፡፡ ለሕወሀት ከባድ ፈተና የሆነባት ዋነኛው ነገር ይሄ ነው፡፡ ዛሬ ላይ፤አዴፓ ውስጥ ሆኖ አይደለም፤ለህወሀት መሰለልና ጥብቅና መቆም፤ በአዴፓ መድረክ ውስጥ፤ስለ ህወሀትየሆነች በጎ ነገር ማንሳት እንኳን ከባድ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ በእኔ እምነት፤ከዚህ በላይ ለሕወሀት ከባድ ጊዜ ያለ /የሚመጣ አይመስለኝም፡፡ ስለሆነም፤ በአሁኑ ወቅት፤ህወሀት እንዲህ ብትቃዥ፤ወዳ አይደለም፤ስሯ፤ አዴፓ ውስጥ ንቅል ብሎ በመውደቁ ነው፤ ትርፍራፊ ካለም፤ገና እንነቅለዋለን፤ያኔ ህወሀት ጨርቋን አውልቃ፤በጎዳና ላይ ወጥታ ስትሮጥና  ስታብድ፤ቆመን እናጨበጭብላታለን፡፡
4. መፍትሄው ምንድን ነው? ወጥር አዴፓ!
በአሁኑ ወቅት፤ከሕወሀት ጋር ለገባንበት ሰጣ ገባ፤ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታ ካስፈለገ፤ትልቁ መፍትሄና ጉልበት የሚገኘው፤ የአዴፓ ንቁ ሆኖ የመገኘትና ያለመገኘት ጉዳይ ነው፡፡ አዴፓ፤ ከፍርሀት፤ይሉኝታና መሽኮርመም ወጥቶ፤በድፍረት፤ ሁሉንም ሰላማዊና ህጋዊ አማራጮች፤ ወደ መጠቀም ካዘነበለ፤ እመኑኝ፤ አዴፓ ህውሀትን በዝረራ አሸንፎ የአማራን ህዝብ ጥቅም ያስከብራል፡፡ ነገር ግን እንደተለመደውና ብአዴን እንደመጣበት መንገድ፤አዴፓም በመለሳለስና በይሉኝታ፤የህወሀትን ነገር ከተመለከተው፤ መግለጫ ስንለዋወጥ መኖራችን ነው፡፡ ሕወሀት አቅሟ ሞቷል፤አሁን ያላት ብቸኛ አቅም፤አንድም ወደ ጦርነት መግባት ነው፤ያለበለዝያም አቅሟን አውቃ፤ወደ ጦርነት እንዳንገባ ማድረግ ነው፤ሌላ አቅም የላትም፤ጨርሳለች፡፡ ስለሆነም፤ወቅቱ ከመቸውም ጊዜ በላይ፤ለአዴፓ የተመቸ ሁኖ ይሰማኛል፡፡ ከዚህ ተሰነስቸ፤አዴፓ የሚከተሉትን እርምጃዎች እንዲወስድ አመክራለሁ፡-
1.የሕወሀትን፤የእሽርሩ አያያዝ፤በግልጽ ማስወገድ፡፡ አዴፓ የአማራ ህዝብ ወኪል እንጅ፤የህወሀት ጉዳይ አስፈጻሚ እንዳልሆነ በአማርኛ ቋንቋ መናገር አለበት፡፡ ዛሬም እደግመዋለሁ፤አዴፓ ከህሀት ጋር፤አብሮ ለመጓዝ እስከ ወሰነ ድረስ፤አማራ ህዝብ ችግር አይፈታም፡፡
2.ወልቃይትና እራያ አካባቢዎች የሚደረጉ መፈናቀሎችና ግድያዎች፤መነሻቸው፤ከአማራዊ ማንነት ጋር የተያያዘ ስለሆነ፤ በነዚህ አካባቢዎች በሚገኙ አማራዎች ላይ የሚከሰተው በደል፤ ለአዴፓ፤ በደሉ በሰብአዊነት ላይ ደረሰ በደል ብቻ ሳይሆን፤ ከአማራዊ ማንነት መጠቃት ጋር አስተሳስሮ እንደሚመለከተው፤ በግልጽ ቅንቋ ለህወሀት ማሳወቅ አለበት፤
3.አዴፓ፤ሕወሀትን በግልጽ የሚቃወሙትን ወጣት፤አመራሮች ወደፊት ማውጣት አለበት( ለምሳሌ እንደነ ደሴ እና ንጉሱ ያሉትን) ፤በአንጻሩ ደግሞ ዛሬም በአዴፓ ውስጥ ተወሽቆ የህወሀት አሸርጋጅ ሆኖ ለመቀጠል የሚውተረተር አመራር ካለ ገለል ማድረግ አለበት፤
4.የፌደራሉ መንግሰት፤በጉዳዩ ላይ የያዘውን የዝምታ አካሂያድ እንዲሰብርና ወደ ተጨባጭ ስራ እንዲገባ፤ከመግለጫ በዘለለ፤ ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ፤በጥብቅ መጠየቅ፡፡ በኃላ ነገር ከተበላሸ በኃላ፤መሯሯጡ ጠቃሚ አይደለምና፤የፌደራል መንግስት ስራውን እንዲጀምር ግፊት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
5.በመጨረሻም፤ አሁንም፤ከህወሀት ጋር አብሮ አውሎ የሚያሳድር አጀንዳ የለንምና፤አዴፓ ከህወሀት ጋር ፍች የሚፈጽምበትን ፕሮሰስ ፤ ከወዲሁ እንዲጀምር ስል እመክራለሁ፡፡
ከሕወሀት ጋር ያለንን ግንኙነት በመበጠስ፤የአማራን ህዝብ የመከራ ጊዜ እናሳጥር!

Filed in: Amharic