>
5:13 pm - Thursday April 18, 1563

ሻማውን ከማጥፋታችንና ግድቡን ከማፍረሳችን በፊት....!! (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

ሻማውን ከማጥፋታችንና ግድቡን ከማፍረሳችን በፊት . . . .!!
ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
.
እንዴት ጤነኛ ሰው በድቅድቅ ጭለማ፣ መቅረዝ እንኳ ሳያዘጋጅ፣ የብርሀኑን ብቸኛ ምንጭ. . . .  የተለኮሰ ሻማውን፣ ‹‹እፍፍፍፍ . . . .›› ብሎ ሊያጠፋ አፉን ያሞጠሙጣል? እንዴት ጤነኛ ሰው ከትልቅ ግድብ ስር . . . ያውም ፊት ለፊት ቆሞ፣ ከግድቡ ድንጋይ ይፈነቅላል?  የሀገሬ አክቲቪስቶችና አብዛኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስራቸው ያንን ይመስላል፤ ጎሰኝነት ባከረፋው ትንፋሽ የሀገርን ሻማ ሊያጠፉ ይጣደፋሉ፤ በራስወዳድነትና በስልጣን ፍላጎት በተሞረደ ምላሳቸው የግድቡን ድንጋይ ይሰረስራሉ፡፡
.
ከዚያስ?! ሻማው ቢጠፋ የሚውጠን ጭለማ፣ ግድቡ ቢናድ የሚያጥለቀልቀን ጎርፍና የምንወርድበት መቀመቅ አያስጨንቃቸውም፡፡ ሻማውን ከማጥፋታችን በፊት ቢያንስ ቀን የሚያወጣ መቅረዝ፣ ግድቡን ካማፍረሳችን በፊት ቢያንስ ከጎርፍ የሚያስጥለን ጀልባ ልናዘጋጅ ይገባል!
.
ለጊዜው ኢትዮጵያና ኢትዮጵየውያን ከጠ/ሚ አብይና በርሳቸው ከሚመራው መንግስት ውጭ፣ (መረረም ጣፈጠም) ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ መቅረዝ በእጃችን፣ ጀልባ በደጃችን ሲኖረን . . . ያኔ አስፈላጊ ከሆነ ሻማውን ስለማጥፋትና ግድቡን ስለመናድ ልንነጋገር እንችላለን፡፡
Filed in: Amharic