>
5:14 pm - Tuesday April 20, 5379

በራያ ዛሬም በህወሀት ልዩ ሀይል የንጹሀን ደም እየፈሰሰ ነው!!! (ደጀኔ አሰፋ)

በራያ ዛሬም በህወሀት ልዩ ሀይል የንጹሀን ደም እየፈሰሰ ነው!!!
ደጀኔ አሰፋ
 
ከሆስፒታል በደረሰን መረጃ ሰባት ወጣቶች በልዩ ሃይሉ ተገድለዋል
= ሁለት ወጣቶች በሞት አፋፍ ይገኛሉ (Critical)
= በጥይት የቆሰሉ በርካቶች ሲሆኑ ከተለያየ የከተማዋ አቅጣጫ ወደ ሆስፒታል እና ክሊኒኮች እየገቡ ይገኛል
– – – – – –
ሰሚ ያጣው የራያ ሕዝብ ሰቆቃ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት ማምራቱ እጅግ ያሳዝናል። በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት የፈጸሙ የመንግስት ኃይሎች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል!
 በራያ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ በነበሩ ዜጎች ላይ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰደው የኃይል እርምጃ ለሰባት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ምክንያት መሆኑን ተሰምቷል። ዛሬም የትግራይ ልዩ ኃይሎች ለሰልፍ በወጡ ንጹሃን ዜጎች ላይ ይህ አይንት የጭካኔ እርምጃ መውሰዳቸው እጅግ አሳዛኝ ነው።
በራያ ያለው ውጥረት እና ግጭት ወደዚህ አቅጣጫ ሊያመራ እንደሚችል ብዙ ምልክቶች መታየት ከጀመሩ ውሎ አድሯል። ሁለቱ ክልሎች እና የፌደራል መንግስቱ ችግሩን ዘላቂ መፍትሔ እስኪያገኝ ድረስ አካባቢው በፌዴራል የጸጥታ ኃይል እንዲጠበቅ ማድረግ አለመቻላቸው የዛሬውን የንጹሃን ዜጎች እልቂት አስከትሏል። አሁንም ራያን ጨምሮ ግጭት በተነሳባቸው እና ሊነሳባቸው ይችላሉ ተብለው በሚሰጉ ሥፍራዎች ላይ መከላከያ እና የፌደራል የጸጥታ ኃይል ማስፈር የግድ ይላል።
የትግራይ ልዩ ሀይል ከተማዋን በጭስ አፍኗቷል ፣ልዩ ሀይሉ ወደ ህዝብ በመተኮስ ላይ ይገኛል ፣ የፌደራል መንግስት በራያ ህዝብ ላይ በወንበዴው የህውሓት መንግስት እየተደረገ ያለውን አፈና ሊያስቆም ይገቧል ገለልተኛ የሆነ የፀጥታ ሀይል በቦታው በማስፈር የክልሉን ልዩ ሀይል አኳባቢውን ለቆ እንዲወጣ ቢያደርግ ህዝቡ ላይ ሊደርስ የሚችለውን መከራ መቀነስ ይችሏል ። የፌደራል መንግስት ህውሓትን ማባበል አቁሞ ዝምቷውን ሰብሮ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ያስጠብቅ ።
ዛሬ በራያ የትግራይ ልዩ ሀይል ፖሊሶች ባደረጉት ጭፍጨፋ ልጆቻቸው የተገደሉባቸው እናቶች አደባባይ በመውጣት እያለቀሱና የመንግስት ያልህ እያሉ ነው።
በንጽሁሃን ዜጎች ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ ትዛዝ የሰጡና ነፍስ ያጠፉ የትግራይ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በህግ ሊጠየቁ ይገባል።
የራያ ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ “ለማንነት መከበር እስከ መስዋዕትነት” በሚል መፈክር በቆራጥነት እየታገለ ይገኛል!!! ከዚህ በሗላ ባርነት በቃን! መታሰር በቃን! መሞት በቃን! መረገጥ በቃን ብሏል!!! ማንነቴን ወይም ሞቴን ብሎ ቆርጦም ተነስቷል።
ለሟች ቤተሰቦች መጽናናት ይስጣቸው!
መከላከያ ሰራዊቱ ሲገባም “መከላከያ የእኛ” እያለ ህዝቡ የተቀበለው ሲሆን በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ ያለው ሰፈር አንፃራዊ መረጋጋት ቢኖርም 01 ቀበሌና ወደ ላይ ያለው ሰፈር ግን አንዳች እንቅስቃሴ የሚባል የለም!!!

Filed in: Amharic