>

የሶስት ከተሞች ወግ አዱስ አበባ፣ መቀሌና አስመራ (ፍጹም አለሙ) 

የሶስት ከተሞች ወግ:- አዱስ አበባ፣ መቀሌና አስመራ
ፍጹም አለሙ 
* ኢሱ ከአስመራ አዲሳባ ያለውን 700 ኪሎ ሜትር የወሀ መንገድ አድርጎታል።ቀን ቀን እየሳቀ ከተማ ይጎበኛል፣ ማታ ማታ በዝግ ችሎት እንዴት አድርጎ  27 ዓመት ጨፍልቆ እንደገዛ ያስረዳል፣የጨፍልቀህ- ግዛው -ፖለቲካ 101 ለዓቢይና ቅርብ ረዳቶች ያስተምራል
* እነ ዳውድንም “ዳውን!ዳውን! ሄይ የምን ትጥቅ አልፈታም ነው?እንዴ ?! ምን ነበር አስመራ የተባባልነው ?”እያለ ወደ “ልቦናቸው”እንዲመለሱና ዓቡይም እንዲያጠናክሩ ይመክራል!
አዱስ አበባ የወታደር አመጽና እገታ ደርሶባት ተደናብራላች።አንዴ ፑሽ አፕ አሰርታ ፎቶ ትንሳለች።ከዛ ሕዝብን ለማረጋጋት ይሁን ለማደናበር በጋዜጣዉ መግለጫ ሚዱያውም ታጨናንቃለች።
ግን የሚዱያ ነጻነትና በግንድ ቆርቋሪ ጋዜጠኛ(investigative journalist) ስለሌለና እንዳይኖር ስላደረገ 27 ዓመት የቆየው ሥርዓት እውነቱን ለማወቅ ተስኖናል።አዲስ አባ ሰላማዉ ልጆቿ ጦላይ ታስረውባት “እበትናለሁ፣በሜንጫ ነው የምለው፣መጤ ፣ሰፋሪ፣ኮሪደር ከፍተን።እናስወጣለን፣መሣሪያ አናወርድም “ወዘተ የሚል ፎካሪና ዘረኛ ግን እንደፈለገ ይፈነጭባታል።
መቀሌ ውስጥ የሽፍታው ጌታቸው አሰፋ ጀሌዌች አነ ስብሀት ነጋ፣በረከት ስምዖን…ጀነራል ክንፈ፣ጃነራል ኳርተር፣ ዳንኤል አሰፋና ህላዉ ዮሴፍ ይዝናኑባታል።ከ አክሱም ሆቴል ወደ ፕላኔት ከዛ ሚላኖ ሆቴል ከዛ ደግሞ ካሌብ ሆቴል  አሁን ደግሞ አክሱም ተመልሰው በግ እያስጠበሱ ውስኪ አየተራጩ፣ መዙቃና ሴት እየቀየያየሩ ባጠቃላይ እየተዝናኑ የዓቡይ መንግስት  የሚወድቅበትን ሴናሪዮ ይወያያሉ። ያ ደግሞ አዱስ አበባን ራስ ምታት ፈጥሮባታል።
አዱስ አበባ ጌታቸው አሰፋ ሱዳን ሄዶ ከዛ ወደቻይና ይሄዳል ሲባል ያወጣችውን የመያዣ ትዕዛዝ እንኳን ማሳፈጸም አልቻለችም።የላከችው አንቶኖቭና ፓሊስ ባዶውን አዱስ ተመልሷል።
ደብረ ጽዬን አዱስ አበባና አዋሳ ሲመጣ ይደመራል፤ትግራይ ሲሄድ ይቀነሳል።
ለውጡን ይደግፋል ተብሎ የነበረው ሳሞራ ለሱዳን መንግስት አማካሪ ከሆነና ድልብ ዶላር ክፍያ ካገኘ በኃላ ኑሮውን ወደ መቀሌ ያዞረ ይመሰላል። “የትግራይን ሕዝብ ለአማራና ለኣሮሞ ጅቦች አሳልፎ ሰጠ፣ካደን” እያሉ እን ስብሀት፣ ጌታቸው አሰፋና አለም ገብረዋህድ “ያጠፉትን ስም”ለማደስ ነውን? ወይስ እሱም ቀስ ብሎ ተንሸራቶ ሊቀነስንና የሚጠላው የጌታቸው አሰፋ አጋዥ ሊሆን ነው?ምን ጥቅም ሊያገኝ?አይታወቅም። ግን የሕውሀት ስብስባ ላይ ደግሞ ይገኛል።
ስብሀት” የወስጥና የውጭ አይጦች መጥተዋል ስለዚህ ትግራይ ያገኘችውን ድል እንዳትነጠቅ ጠንቅቃችሁ ጠብቁ” እያለ ይሰብካል።ያው በኮድ  ጦር ይስብቃል ማለት ነው።ከውጭ የሚገቡ ተቃዋሚ የትግራይ ተወላጆችን ሆቴላቸው ድረስ እየሄድ ያዋክባል፣”ከቄሮና ከአማራጋ ሆናችሁ ምን እንደምታረጉን እናያለን” እያለ ይዝታል፣ ያስፈራራል።እሱም 27 ዓመት ከፈነጨበት አዱሳባ ከነልጁ ሎሌዋቹ መቀሌ ከትሟል።
 የዕርዳታ ልብስ እያለበሰና ውሎ አበል እያስከፈለ ዓቡይን ተቃውሙ ብሎ ሰብኮ ምስኪኑን የትግራይን ገበሬ ሲያሰወጣ የነበረው የጌታቸው ቡድን  ምክንያት ሲየልቅበት ፓለቲካና ተንኮልን፣ እኩይን ተግባርና ኮንስፓይራሲን፣ መገደልና ማሰገደልን፣ የተካኑትን እንደነ በረከት ስምዖን  አይነቶችን ትግራይ ጠቅልሎ ሰብስቦ ያው ከላይ እንደተባለው በየሆቴሉ እያበላ፣እያጠጣ፣ እያዝናና ዓቡይን ለመጣል፤ ሀገርን ለመበጥበጥ መላ ይፈጥራል፤ይወጥናል፤ካልሆነ አስፈራርቶ ጥሩ ዲል ለማግኘት ይጥራል። እሳት የላሱ ነባርና አዱስ ፕሮፖጋንዱስቴች  ቀጥሮ “-ትግራይ ሊበሉህ ነው ” እያሉ  እንዲሸውዱና ሕዝቡ የለውጡ ተቋዳሽ እንዳይሆን ያግታል።
በተጨማሪም ይህ ባለ 5 ፖስፖርቱና   በርሜል ሙሉ ብር ላይ የሚያዘው ገዳይ አስገዳይ ጌታቸው መቀሌ ሆኖ ሕዝብና ህዝብን ለማጋጨት፣ በአየርም ሆነ በመኪና ከእስመራም ሆነ ከሌላ ቦታ የገቡትን ማኖ ለማስነካት ብሎም በለመደው ሙያ እንሱ እንዳሉበት አርጎ ግጭት ለመፍጠር ፓርቲዋችኑም ሆነ መሪዋቻቸውን ከሕዝብና ከመንግስትጋ ለማጣላት ሌት ተቀን ይሰራል።ግጭትና ግርግር ሲፈጠር ደም ሲፈስ ለሌባ ስለሚመች የዘረፈውን ይዞ ለመቀየስ እንቅልፍ አጥቶ ያድራል።
በረከት በበኩሉ “አዬ …ገዱና ደመቀ ናቸው ፖለቲካ የሚያውቁት “እያለ ያፌዛል።”እንሳያቸዋለን!” እያለ ይዝታል።ከሌሌች ድርጅቶች አጋሮችም ያፈላልጋል።አንዳንድ ጎብኝዎችም መቀሌ ብቀ ብለው ነበር ይባላል።
ደብረጽዬን ግራ ገብቶታል፤”ሲታሰር ወድ እኔ ሲፈታ ወድ እሱ “ዓይነት ሆኗል ።
ዓቡይ መቀሌ ሰዋቹን ልኮ ቢያቅተው አዱስ አበባ ሆኖ ስልካቸውን እንዳያዳምጥ ጅቦች የተባሉት የዱባይ የሕንድና የሌላ ሀገር በሳተላይት የሚሰራ ስልክ ነው የሚጠቀሙት።
ዓቡይ ነጭ ለባሽ እንዳይልክ ጽጉረ ልውጥ ሰለሚሆኑ ክልሉ ሊያስራቸው ይችላል።ያ ደግሜ ሌላ ችግር ነው።
ሆቴሉ ውስጥ ካሜራም ሆነ ማድመጫ እንዳይተክል ባላቤቶቹም ሆነ ክልሉ አይፈቅዱም።
እዱስ አበባ ግራ ገብቷታል።መቀልም እንደዚያው።
አስመራ ሕዝቡ ምን እንደሚልና እንደሚያስብ አይታወቅም።ታፍኗል።ዛሬ ኢሳያስ የምናምን ነጻ አውጪ፣ንቅናቄ፤ግንባር፣እግር-እጅ ገለመሌ የሚባሉትን ትላልቁን በአውሮፕላን ትናንሹን በካሚዮን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ የአሰመራን ካፌዋቹ፣ሆቴሌችና ቡና ቤቶቹን ባዶ አድርጎ ከአዱስ አበባ ለሚመጡ ሌሎች ቱሪስቶች ተራቸውን እንዲለቁ እድርጓል።
ኢሳያስ የትግል አጋሩ የነበሩትን እንጦርጦስ አውርዶ፣ገሎ አስገድሎ ፣በድሮ አጋሮቹ ወየኔዋችጋ ቂሙንና ጥላቸውን እንደስንቅ ይዞ የዓቢይ መንግስት ጭንቅ ውስጥ በገባ ቁጥር  ስራውን ትቶ ከአስመራ ከች ይላል።ከአስመራ አዲሳባ ያለውን 700 ኪሎ ሜትር የወሀ መንገድ አድርጎታል።ቀን ቀን እየሳቀ ከተማ ይጎበኛል፣ማታ ማታ በዝግ ችሎት እንዴት አድርጎ  27 ዓመት ጨፍልቆ እንደገዛ ያስረዳል፣የጨፍልቀህ- ግዛው -ፖለቲካ 101 ለዓቢይና ቅርብ ረዳቶች ያስተምራል፤ እነ ዳውድንም “ዳውን!ዳውን! ሄይ የምን ትጥቅ አልፈታም ነው?እንዴ ?!ምን ነበር አስመራ የተባባልነው ?”እያለ ወደ “ልቦናቸው”እንዱመለሱና ዓቡይም እንዱጠናከር ይረዳል።
አስመራ ግን ለውጥን በተስፋ ትጠብቃለች።መጠበቅ ያልቻለው ወይም ወገንና ብር ያለው በተከፈተ ቦርደር ወደ መቀሌና አዲስ  ይሾልካል።
መሳሪያ የሌላቸውና ከተማችን ውስጥ መብታችን ይከበር ያሉት ልጄቿ ጦላይ የታጎሩባት  አዱስ አበባ የዓቡይ መንግስት ላይ ዘመቻ ጀምራለች።ዓቡይ ደግሞ “ኮፈያ የማያረግ ፣ጸጉሩን የማያጨፈርር፣ስቆ የሚያስቅ ግን የማይስርቅ፣ምንጣፍ የሆነ  ወንድ ሚኒስትር ብቻ ሳይሆን ሽክ ያለች ግን ስራ መስራት የምትችል እንስት ሱሬና እስኪቡርቶ  አስታጥቆ እያላከ ነው በ10 ሚኒስተር መስሪያ ቤት።
ሶስቱም ከተሞች የራሳቸው ወግ ብቻ እንዱሰማ ይፈልጋሉ።
እኛም እናወጋለን።
እናርጅ እንውጋ።
Filed in: Amharic