>

ሊፈቱ ነው የሚለው ዜና እና የፖለቲካው ቁማር !!  (ሃብታሙ አያሌው)

ሊፈቱ ነው የሚለው ዜና እና የፖለቲካው ቁማር !!
 ሃብታሙ አያሌው
“የአዲስ አበባን ወጣት ጦላይ እያሰለጠንን ነው
አላሰርንም”
ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል
ሃፍረተ ቢስ የሆነው የፌደራል ፖሊስ የለመደውን ነውር ዛሬም እየደገመው ነው። ጦላይ በረሃ ወስዶ ከቤተሰብ ነጥሎ ያሰቃያቸውን የአዲስ አበባ ወጣቶች በካሜራ እያስቀረፀ ፤
* በሰራነው ወንጀል ተፀፅተናል
* ስልጠናው በጣም ጥሩ እና ጠቃሚ ነበር
* እስፖርት በመስራት ጤናችንን ከመጠበቅ በቀር ዱላ
የለም
* በስሜት ተነሳስተን የጥቂት ፀረ ሰላም ሃይሎች
መጠቀሚያ ሆነናል
* አይደገምም !!
ምናልባት እንደ ወታደሮቹ እራት ግብዣ እና ፑሽ አፕም ልናይ እንችላለን።
ኮሚሽነር ዘይኑ ይሄ ድራማ ተነቅቷል ሌላ ሞክሩ !!
የአዲስ አበባ ወጣት የታሰረበት እውነተኛ ምክንያት
1. ኢትዮዽያ ኢትዮዽያ አንደነት ማለቱ
2. አዲስ አበባ የነዋሪዎቿና የሁሉም ኢትዮዽያዊ ከተማ ናት ማለቱ
3. አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሠንደቅ ዓላማን ከፍ አድርጎ ማክበሩ
4. ለግንቦት 7 መሪዎች ደማቅ አቀባበል ማድረጉ
5. ቡራዩ ላይ ብሔርን ኢላማ አድርጎ የተፈጸመውን ጥቃት ማውገዙ ነው።
እነዚህ ነገሮች በአክራሪ የኦህዴድና ተቃዋሚ በሆኑ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጥርስ እንዲነከስበት፣ ታፍሶ እንዲታሰርና ወደ ጦላይ ተግዞ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንዲፈጸምበት አድርጎታል። በዚህ ሕገ ወጥ ድርጊት የተነሳ በርካታ ወጣቶች ከስራቸው፣ ከትምህርታቸው፣ ከወላጆቻቸው. . . ተለይተው አስከፊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው ነው። ቤተሰቦቻቸውም ለስቃይና እንግልት ተዳርገዋል።
በእስሩ ላይ ከዶር አብይ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የኦህዴድ አመራሮች ተሳታፊዎች ናቸው።
የዶር አብይ መንግስት የቃላት ጨዋታውን አቁሞ በሕገ ወጥ መንገድ ያሰራቸውን ወጣቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፍታ።
ፍትህ በእንግድነት ተቀብሎ ያለውን ባጎረሰ
እጁን ለተነከሰ የአዲስ አበባ ወጣት !!
Filed in: Amharic