>

በተንኮል ፖለቲካ ተለንቅጦ የተሰራው ኢህአዴግ!!  (መስከረም አበራ)

በተንኮል ፖለቲካ ተለንቅጦ የተሰራው ኢህአዴግ!!
መስከረም አበራ

ሞንጆሪኖ ካልተሾመች ሃገር የማይቆም ከሆነ እንኳን ተጋዳሊት ስለነበረች መከላከያ ሚኒስትር ብትሆን ይሻል ነበር፡፡ እንጅ የህወሃትን ሰው የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ማድረጉ ኢፈርት የለመደውን እንዳያጣ ከመርዳት በቀር ለእኛ ምን ሊረባን?   ፡፡ከሃያ ሚኒስትር ግማሹ ሴት እንዲሆን ይሁን ሞንጆሪኖ ከዶ/ር አምባቸው የተሻለ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትርነት እውቀት ኖሯት ይሁን እዛ ቦታ ላይ የተቀመጠችው የኢህዴግ አምላክ ያውቃል! በሰላም ሚኒስትር ውስጥ የታመቁ (የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት፣የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣የፋይናንስ መረጃ ደህንነት ኤጀንሲ፣የፌደራል ፖሊስ፣ የፌደራል እና የአርብቶ አደር ሚኒስትር (ይሄ በተለይ በጣም የሚገርም ዘው ማለት ነው) መስሪያ ቤቶች  ብዛት እና ይሄን ሁሉ መስሪያ ቤት  በአንድ ሰው ስር ማድረግ ለወ/ሮ ሙፈሪያት ጠጠር ማለቱ አይቀርም፡፡

በዚህ ላይ ሙፈሪያት በደህንነት መስሪያ ቤቶች ልምድ እንዳላት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ የወ/ሮ ዳግማዊት ሹመት ከአዲስአበባ ምክትል ከንቲባነት መንደር ራቅ ለማድረግ ነው ወይስ እንደተባለው የሴት ሚኒስትሮችን እኩል በእኩል ለማድረግ? በተንኮል ፖለቲካ ተለንቅጦ የተሰራው ኢህአዴግ ነገረ ስራው ወደቀደመ “ኢ-አማኒነቴ” ሊመልሰኝ እየፈተነኝ ነው! የዳግማዊትን ቦታ የሚይዘው ሌላ የአዲስ አበባ ሰው ካልሆነ የጨዋታው አካሄድ ለታከለ ብቻ ጥሩ የሚሆን ይሆናል፡፡ በታከለ ውስጥ አብይ እንዳሉም ያስጠረጥራል……

Filed in: Amharic