>

በዛሬው እለት በራያ አላማጣ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል!! (ደጀኔ አሰፋ)

በዛሬው እለት በራያ አላማጣ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል!!
ደጀኔ አሰፋ
* “ስብሰባው የሚመለከተው እኛን ነው ፡ የራያ ህዝብ ማንነት በትግሬዎች ውክልና አይወሰንም” በማለት ወደ አዳራሽ ለመግባት ቢሞክርም እጅግ ቁጥሩ የበዛ ልዩ ሃይልና የከተማው ፖሊስ በወጣቶቹ ላይ ባወረደው ከባድ ድብደባና ማሳደድ ሳቢያ ተቋርጧል! 
__
ትህነግ በትላንትናው እለት ከትግራይ በአበል ያመጣቸውን ሰዎች ገሚሱን በስብሰባ አዳራሽ አብዛሃኞቹን ደግሞ በአላማጣ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክፍሎች በቡድን በመከፋፈል የራያ ህዝብ ትግሬ እንደሆነና የማንነት ጥያቄ እንደለለው እያስተማሩ ሲውሉ በተጓዳኝ የራያ ህዝብ በልዩ ዞንነት በትህነግ የትግራይ ክልል ስር እንዲሆን እንደጠየቁ ተደርጎ እንዲያቀርቡ ሲሰብኩ ውለዋል።
ሆኖም ግን እውነተኛው የራያ ህዝብ እና የህዝቡ መከታ የሆነው የራያ ስበር በወሰደው የተቃውሞ እርምጃ እና የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ በሰብሳቢዎቹም ይሁን በተሰብሳቢዎቹ ላይ ከባድ መደናገጥን ፈጥሯል።
ከዚህም መዳናገጥ የተነሣ ስብሰባውን ሲያስተባብሩ የዋሉት ባለስልጣናት ከምሽቱ 1:30 በልዩ ሃይሉ ታጅበው ማይጨው ሄደው ለማደር የተገደዱ ሲሆን ከትግራይ የመጡት ተሰብሳቢዎችም ለህይወታችን ስለምንሰጋ ከዚህ አንወጣም በማለት በከባድ ጥበቃ ሲማሩበት ከዋሉት የአላማጣ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ማደራቸው ተሰምቷል!!!
የትህነግ ተላላኪዎቹ የሁለት ቀኑ ስብሰባ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን ትህነግ የስብሰባውን አካሄድ በመቀየር ሁሉም ከትግሬ የመጡትን ተሰብሳቢዎች (የራያ ማንነት ሰልጣኝ ደቀ መዛሙርት) ወደ አላማጣ ከተማ ትልቁ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመውሰድ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛል ።
ይህንን የትህነግ ሸፍጥ መሸከም ያልቻለው የራያ ስበር በዛሬው ዕለት “ስብሰባው የሚመለከተው እኛን ነው ፡ የራያ ህዝብ ማንነት በትግሬዎች ውክልና አይወሰንም” በማለት ወደ አዳራሽ ለመግባት ቢሞክርም እጅግ ቁጥሩ የበዛ ልዩ ሃይልና የከተማው ፖሊስ በወጣቶቹ ላይ ባወረደው ከባድ ድብደባና ማሳደድ ሳቢያ ተቋርጧል።
የከተማዋ ዋና መንገድ በተለይም አዳራሹ በሚገኝበት (ከራያ ሆቴል እስከ ሆሣዕና ሆቴል) ያለው መንገድ ለተሽከርካሪ ዝግ የተደረገ ሲሆን ከተማዋ በዚህ ሰዓት የዜጎች መኖሪያ ሳይሆን የልዩ ሃይል ማሰልጠኛ ካምፕ ትመስላለች።
#የፌደራል መንግስት እየሰማን ስላልሆነ ወገናችን የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን እንድትቆሙ እንጠይቃለን!!!
#የራያ ህዝብ የፍትህ ያለህ እያለ ይጮሃል !!!
Filed in: Amharic