>

እሾህን በሾህ !!! (ቬሮኒካ መላኩ)

እሾህን በሾህ !!!
ቬሮኒካ መላኩ
1ኛ~ ኦዴፓ በሚያስተዳድረው  ክልሉ የፈለገውን ሰው በሾመ ቁጥር  Trauma (የስጋት ልክፍት)  ውስጥ መግባትና ፓኒክ ማድረግ ተገቢ አይደለም። ይሄን ጉዳይ ብዙ ሰዎች  ላይ ስላስተዋልኩኝ ነው። እንደ እኔ አመለካከት ኦዴፓ በፌደራል ላይ የሚመድበውን ሰው በጥንቃቄ መከታተል ያስፈልጋል እንጅ  በክልሉ  እንኳን ጀነራል ከማል ገልቹን ይቅርና  ካዋጣው የ6ወር ህፃን ልጅ  መመደብ ይችላል።
2ኛ~ ኦዴፓ ከ6ቱ የኦነግ ድርጅቶች የአንዱ መሪ የነበረውን ጀኔራል ከማል ገልቹን የክልሉ የፀጥታ ሀላፊ  ሲያደርግ  ” እሾህን  በእሾህ”  እንደሚባለው  ክልሉ ላይ እያገነገነ የመጣውን ዳውድ ኢብሳን  በከማል ገልቹ  ለመጠራረግ ይመስላል።
3ኛ~ እንደሚታወቀው ከማል ገልቹና ዳውድ ኢብሳ እሳትና ጭድ ናቸው።  ጀኔራል ከማል ገልቹን ከአስመራ  እንደ ኳስ በካልቾ ጠልዞ ኡጋንዳ ካምፓላ ያሳረፈው ዳውድ ኢብሳ እንደሆነ ይታወቃል ። አሁን በተራው የክልሉን መንግስት  መሳሪያና  ወታደር የሚያገኘው ከማል ገልቹም ብድሩን ዳውድ ኢብሳን  በመጠለዝ ይመልሳል ። ለማ መገርሳና አቢይ አህመድም  ቅዤት ከሆነባቸው ኦነግ እረፍት ያገኛሉ።
4ኛ-  ሌሎቻችን ምን አይነት ስትራቴጅ መከተል አለብን?   ዘመኑ የአእምሮ ትግል ወቅት ነውና አእምሮህን አስላ። እቅድህን አጥራ። ስትራቴጅህን በጥንቃቄ ቀንብብ ። የፖለቲካ ተወዳዳሪህን አእምሮ ፈርጅ (Wave length) በልጦ መገኘት  ጊዜው የሚጠይቀው ሃቅ ነው።
ኦዴፓ ናፖሊዮን ቦናፓርትን ከመቃብር ቆፍሮ ከሾመ እኛ ደሞ ከናፖሊዮን በአስር እጥፍ በጦር መሪነትና በፖለቲካ የሚበልጠውን ታላቁ  እስክንድርን ከመቃብር ቆፍረህ ቁጭ ታደርጋለህ።  ለማንኛውም ኮሌኔል ደመቀ ዜውዴ  ለበለጠ ሃላፊነት ራሱን ቢያዘጋጅ ጥሩ ነው።
Filed in: Amharic