>

" ወጣቶች ባዶ እጃቸውን ወጥተው ታንክ ፊት ቆመው ሲታገሉ የኦነግ ሰራዊት የት ነበረ ?! " (አቶ ሌንጮ ለታ)

” ወጣቶች ባዶ እጃቸውን ወጥተው ታንክ ፊት ቆመው ሲታገሉ የኦነግ ሰራዊት የት ነበረ ?! “
አቶ ሌንጮ ለታ
ኦነግ ትጥቅ አልፈታም በማለት ለተጀመረው ስላማዊ የፖለቲካ ሂደት እንቅፋት መሆን የለበትም መንግስትም በጉዳዩ ላይ ግልፅ መረጃ ማቅረብ አለበት ሲሉ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ተናገሩ። አዲስ አበባ በሚገኘው አሐዱ በተባለው ሬድዮ ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር እንግዳ ሆነው የቀረቡት አቶ ሌንጮ ለታ በሀገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ሁሉን አካታችና የማይቀለበስ እንዲሆን ሁሉም አካል በሀላፊነት መንቀሳቀስ አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከኦነግ ጋር የደረሰበትን ስምምነት ይፋ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ሌንጮ ለታ የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምን ተነስተው ትጥቅ አንፈታም እንዳሉ መረዳት ይቸግረኛል ብለዋል። ” ወጣቶች ባዶ እጃቸውን ወጥተው ታንክ ፊት ቆመው ሲታገሉ የኦነግ ሰራዊት የት ነበረ? አሁንስ ትጥቅ አልፈታም ማለት ማንን ለመውጋት ነው?”  ሲሉ ጠይቀዋል። የትጥቅ ትግል የትም እንደማያደርስና ስላማዊና ህዝባዊ እምቢተኝነት የተሻለ የትግል ስልት መሆኑን ከተገነዘብኩ ብዙ አመታት ተቆጥረዋል፣ አሁን የሚያስፈልገን በስላምና በመግባባት ላይ የተመሰረተ የዴሞክራሲ ሽግግር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

Filed in: Amharic