>

<< ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ማገዝ አለብን!!! >> ዶ/ር መረራ ጉዲና 

<< ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ማገዝ አለብን!!! >>  
የዶ/ር መረራ ጉዲና ጥሪ !!
የተሻለ ታሪክ የሚሠራው የጋራ አጀንዳ ቀርጾ በብሔራዊ መግባባት ላይ የመድረስ የሁላችንም የቤትሥራ እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ግን መግፋቱ ማናችንንም የማትጠቅም ኢትዮጵያ የመፍጠር ሁኔታ ይመጣል!!!
“…የመጣውን ለውጥ ሁሉም በአግባቡ እንዲይዝ አደራ እላለሁ፡፡ ሥልጣን የለቀቀውም፣ ከእሥር ቤት የተፈታነውም፣ በተለያየ መንገድ አገር ቤት የገቡ በጥንቃቄ እደግመዋለሁ በጥንቃቄ መያዝ ያለብን እድል ነው፡፡
ይህንን እድል በማይሆን መንገድ አበላሽተን አገሪቷን ለሌላ ተጨማሪ ዓመታት የደም ጎርፍ እንዲፈስባት ማድረግ የለብንም፡፡ በተለይም እኛን እዚህ ያደረሱንን ወጣቶችን፣ ተቃዋሚዎችን ጭምር ያስከበሩ ወጣቶችን ደም ዝም ብለን አጉል እንዲፈስ ከፈቀድን ታሪክ ምንጊዜም ይቅር የማይለን ሰዎች ሆነን እናልፈዋለን፡፡
 የተሻለ ታሪክ የሚሠራው የጋራ አጀንዳ ቀርጾ በብሔራዊ መግባባት ላይ የመድረስ የሁላችንም የቤትሥራ እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ግን መግፋቱ ማናችንንም የማትጠቅም ኢትዮጵያ የመፍጠር ሁኔታ ይመጣል፡፡ ሁላችንም በማይሆን መንገድ የመክሰር ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል፡፡
ሁላችንም ተባብረን ከሕወሐት መሪዎች ጭምር አገሪቷን ከመጠፋፋት እና አጥፍቶ ከመጥፋት ፖለቲካ እንጠብቅ፡፡ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ማገዝን አሁንም ደግሜ አደራ እላለሁ።”
ከዶ/ር መረራ ጉዲና  ስዩም ተሾመ Source: Amen Media & Communication
Filed in: Amharic