>

የአምስቱ የኦሮሞ ድርጅቶች መግለጫ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው) 

የአምስቱ የኦሮሞ ድርጅቶች መግለጫ!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 
በኦሮሞ ስም የተደራጁ አምስት ጅርጅቶች የሰጡት መግለጫ ብዙ ትርጉም ሊሰጠው የሚችል ነው። አምስት በትልልቅ ሰዎች የሚመሩ ፓርቲዎች ተሰብስበው የሚጽፉት መግለጫ ድምጸት እና በዚህ ወቅት የሚያንጸባርቁት አቋም ይህ መሆኑ ያስዝነኛል።
ትልቅነት አላየሁበትም።
 አርቆ አሳቢነት አልሰማሁበትም።
ሆደ ሰፊነት አላሸተትኩበትም።
በተቃራኒው፤ የአሸናፊነት፣ የድል አድራጊነት ስሜት አይበታለሁ። ለመሞትም ለመግደለም ዝግጁ ነን የሚል ዛቻ እሰማበታለሁ። እልህ ሲተናነቃቸው እታዘባለሁ። ጊዜው የእኛ ነው የሚል ድምጽ ይጮሃል።  ተሳስቼ ሊሆን ይችላል፤ ግን አልመሰለኝም።
ታሪክ የምጸት ሳቅ ሲስቅ ይታየኛል። በማን ላይ እንደሚስቅ ነው ያላወቅሁት። ከዚህ ስሜት በመነሳት የራሴ ድምዳሜ ላይ ስደርስ:-
* ሰዎቹ ያልሠለጠኑና ፈጽሞ ሊሠለጥኑ የማይችሉ የጉድ ፍጥረቶች መሆናቸውን፣
* በፍትሕ በአመክንዮና በተጨባጭ ታሪካዊ እውነታ ፈጽሞ የማያምኑና በእነሱም መዳኘትና መገዛት ፈጽሞ የማይፈልጉ።
* ለዝርፊያና ለውንብድና ብቻ ታጥቀው የተነሡ ወንበዴዎች መሆናቸውን ነው በዐሥር ጣታቸው ፈርመው ያረጋገጡልን፡፡
በፍትሕ፣ በአመክንዮና በተጨባጭ ታሪካዊ እውነታ ፈጽሞ የማያምኑና በእነሱም መዳኘትና መገዛት ፈጽሞ የማይፈልጉ የሆኑበት ምክንያትም ጥቅማቸው የተመሠረተው በዝርፊያ፣ በወረራ፣ በንጥቂያ፣ በውንብድና በመሆኑና ፍትሕ፣ አመክንዮና ተጨባጭ ታሪካዊ እውነታ ያላቸውንና ያለአግባብ “ይገባኛል!” የሚሉበትን ሁሉ የሚያሳጣቸው ስለሆነ፣ ጠባብ ብሔርተኝነታቸውን መሠረት ስለሚያሳጣባቸውና አየር ላይ ስለሚያንሳፍፋቸው ነው፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ፣ የነዐቢይን እና የኢትዮጵያን እጣ ፋንታ ለመረዳት እሞክራለሁ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic