>
5:13 pm - Sunday April 19, 0905

ምኞት ባይከለልከም አዝሎት የሚመጣው እልቂት ግን ያሰጋል!! (ውብሸት ሙላት)

ምኞት ባይከለልከም አዝሎት የሚመጣው እልቂት ግን ያሰጋል!!
ውብሸት ሙላት
 
* 16ኛው ክ/ዘመን እስኪገባደድ አይደለም አዲስ አበባ ፈጣጋር የሚባለዉ (በከፊል ምስራቅ ሸዋ) ይኖሩ የነበሩት ኦሮሞዎች አልነበሩም። አማራም አይደለም።
የኦሮሞ ድርጅቶች ( ፖለቲካ ፓርቲዎች) አዲስ አበባ የኦሮሞ እንደሆነች መግለጫ አዉጥተዋል። ያዉ ገዥ ፓርቲዎች ስላልሆኑ የፈለጉትን መግለጽም መመኘትም ይችላሉ። ፍላጎትንም ምኞትንም መከልከል አይቻልም።
አንድን አካባቢ ወይም ቦታ ለስንት አመት ሲኖርበት ነው የእንቶኔ ብሔር መሬት ነዉ የሚባለዉ? የአሁኑ አዲስ አበባ የሚባለዉ አካባቢ እስከ 16ኛዉ ክፍለ ዘመን ድረስ ይኖሩ የነበሩት ኦሮሞዎች ሳይሆኑ ሌሎች ነበሩ። 16ኛው ክ/ዘ ከገባ በኋላ የነበሩት አጼ ልብነ ድንግል ዋና ከተማቸዉ  እዚሁ አካባቢ ነበር። እንደውም የአጼ ልብነ ድንግል ልጅ ገላዉዲወስ የተወለደዉ አዳማ (ናዝሬት) ነዉ። ግራኝን ካሸነፈ በኋላ መቀመጫውን (ከተማዉን) ዳዋሮ (ከናዝሬት በስተምሥራቅ?) ነበር። በዚያን ወቅት አይደለም አዲስ አበባ ፈጣጋር የሚባለዉ (በከፊል ምስራቅ ሸዋ) ይኖሩ የነበሩት ኦሮሞዎች አልነበሩም። አማራም አይደለም።
ታሪክን መሰረት አድርገን ከጠየቅን እስከ 16ኛው ክ/ዘመን እስኪገባደድ በአካባቢው በስፋት ይኖሩ የነበሩት ኦሮሞዎች አልነበሩም። ከዚያ በኋላ ነው ይህን አካባቢ ቁጥሩ በዛ ያለ ኦሮሞ የሰፈረበት።
ከዚያ ደግሞ አጼ ምኒልክ ዋና ከተማቸዉን አዲስ አበባ ካደረጉ (ከተቆረቆረች) 130 ዓመት አልፏል። የአካባቢውም የሕዝብ ስብጥር ያዉ እንደምናየው ሆኗል።
አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ለማለት መነሻው ከ17ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ እስከ 1879 ዓ.ም.  ያለውን ጊዜ መነሻ በማድረግ ከሆነ በየትኛው ሥነ አመክንዮ ነው አንድም ከ17ኛው ክፍለ ዘመን በፊት ያለው አንድም ከ1879 በኋላ ያለው የሚዘለለው? በሌላ አገላለጽ ከ17ኛው ክ/ዘ በፊት ያሉትስ የእኛ ነው የማይሉበት ምን ምክንያት አለ? ከ1879 ዓ.ም. በኋላ በተፈጠረው ሁኔታ አሁን ያለው ያለው ሕዝብ የእኔ ነው የማይሉበት ምን ምክንያት ይከለክላቸልዋ?
 እና ምን ለማለት ነው? አድስ አበባ የአድስ አበቤዎች ናት። ዘመን እየቆጠርን በዚህን ጊዜ የእንትና በዚያን ዘመን የእንናን ብንል ማቆሚያ የሌለው ጣጣ ውስጥ ይከተናል።
ምኞት ባይከለልከም አዝሎት የሚመጣው የእልቂት ግን ያሰጋል!!
Filed in: Amharic