>
5:14 pm - Monday April 20, 2787

ጋሽ በቄ ያም ሆኖ ዛሬም እወድዎታለሁ!!! (የኢሳት ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ) 

ጋሽ በቄ ያም ሆኖ ዛሬም እወድዎታለሁ!!!
የኢሳት ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ 
*የትግሬ ብሔርተኞች ኢሳትን “ፀረ ትግሬ” ይላሉ
*የአማራ ብሔርተኞችም ተመሳሳይ ቃላት ይጠቀማሉ
እርስዎ “የኦሮሞ ጠላት” አደረጉን 
እነዚህን ውድ ኢትዮጵያዊያን ከጠላን ታዲያ የኛ ሀገርና ሕዝብ ከወደየት ነው? እኛስ ማን ነን?
የሐሰት ክስዎት ለርስዎ ያለኝን ክብር አይቀንሰውም። በመጀመሪያው እስር ወቅት ሲሰቃዩ “ኦሮሞ ይጠላሉ” ብለው የሚከሱን እኛ ምን እንዳደረግን እንደእናት የማያቸው ባለቤትዎ ወይዘሮ ሀና ይንገርዎት።
ያኔ የዛሬ ዘር ነጋዴዎች ዞር ብለው በማያዩዎት ወቅት እኔ ልጅዎ ምን እንዳረግኩ ህሊናዎ ያውቃል።
ከዚያም ከእስር ተፈትተው አሜሪካ ሲመጡ እንዴት እንዳከበርንዎት፣ በግሌ እንዴት ዝቅ እንዳልኩልዎት የሚዘነጉ አይመስለኝም። በድጋሚ ሲታሰሩ በሐሳብ አብረን እንዴት እንደተሰቃየን ልጅዎ ቦንቱ ትንገርዎት።
እንደገና ከተፈቱ በኋላ ወደ ዲሲ ሲመጡ አብረን ባሳለፍናት ጥቂት ሰዓታት የተነጋገርነውና ያሉኝ ቃላት ከቶ እንዴት ይዘነጋዎታል?  ሕበረብሔራዊ ለሆነች ኢትዮጵያ እንደሚተጉ የገቡልኝ ቃልስ ከወዴት በነነ እርስዎ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንዲሁም የክብር አቀባበልን ሸሹ ተብለው ሲከሰሱ ሽንጤን ገትሬ የተከራከኩልዎት እኔስ የት ልግባ?
 በኦሮሞ ጥናት ማህበር ዓመታዊ ዝግጅት ላይ የተገኙ ዕለት አንድ የኦነግ አመራር ከርስዎ ጋር ፎቶ ለመነሳት ሲጠይቅ በፍጹም ያሉትን ያስታውሳሉ ኦነግ በገዢው ስሮእት በሽብርተኛ የተመደበ ድርጅት ስለሆነ ሕግን ለመከትልና የወያኔ ወጥመድ ውስጥ ላለመግባት ሲሉ በፎቶ አብሮ መታየቱን እንደማይፈልጉት ገልጸው ነበር።
ከሱ ቀን በፊት ኢሳት ቢሮ ኮከብ ከሌለው ባንዲራ ጎን መነሳት ችግር እንደሚያስከትል በመግለጽ ወደ ሌላ አቅጣጫ ዞረን የማስታወሻ ፎቶ ተነስተን ነበር። ሁለቱን ክስተቶች አጠገብዎ ሆኜ በማየቴ ጋሽ በቄ የመርኽ ሰው ናቸው የሚል የጸና እምነት ፈጥረውብኛል።
ታዲያ እኔ ከልቤ የማከብርዎት ወዳጅዎ ዛሬ ኢሳትን ኦሮሞ ጠል አድርገው ሲከሱ ለማመን ከብዶኛል።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እርዎነትዎ እየተቀየረ ቢመጣም አሁን ደንግጫለሁ። አጥብቀው የሚከተሉት ክርስትናዎ እንዲህ ያለ የሀሰት ውንጀላ ይፈቅዳል ወይ  ጋሽ በቄ ወደአዕምሮዎ ይመለሱ። እባክዎ የፖለቲካና የአስከሬን ንግድ ካሰከራቸው ጋር አብረው አይናውዙ።
እስኪ ይፍረዱን
*የትግሬ ብሔርተኞች ኢሳትን “ፀረ ትግሬ” ይላሉ *የአማራ ብሔርተኞችም ተመሳሳይ ቃላት ይጠቀማሉ
እርስዎ “የኦሮሞ ጠላት” አደረጉን እነዚህን ውድ ኢትዮጵያዊያን ከጠላን ታዲያ የኛ ሀገርና ሕዝብ ከወደየት ነው? እኛስ ማን ነን?
እባክዎ ይንገሩን , አደራ ዋቃ! ሁሉም ጠምዝዞ የራሱ በቀቀን ካላደረገን እኛ ኢሳቶች “ፀረ —” እንባላለን
ኦቦ በቄ አሁን እንደትላንቱ ወድዎታለሁ::የምወድዎት እንደ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የከፈሉትን መስዋዕትነት ስለማከብር ነው። ሕዝብን ማሸነፍ የሚቻለው እውነት ብቻ ይዞ ነው! “
Filed in: Amharic