>
5:13 pm - Thursday April 19, 1123

እንዴት ሰው ህወሀት የሰራለትን የውሸት ካርታ ይዞ ልገንጠል ይላል?!? (ዶክተር መረራ)

”እንዴት ሰው ህወሀት የሰራለትን የውሸት ካርታ ይዞ ልገንጠል ይላል?!?” 
ዶክተር መረራ ጉዲና
መንግስት ደሞ ተቃዋሚውን እንዲቃወሙ ራሱ የፈለፈላቸው የፖለቲካ ሀይሎች አሉ ለነዚህ ቀለብ መስፈር ያቁም።  
“…የመጣውን ለውጥ ሁሉም በአግባቡ እንዲይዝ አደራ እላለሁ፡፡ ሥልጣን የለቀቀውም ፣ ከእሥር ቤት የተፈታነውም ፣በተለያየ መንገድ አገር ቤት የገቡ በጥንቃቄ እደግመዋለሁ በጥንቃቄ መያዝ ያለብን እድል ነው፡፡ ይህንን እድል በማይሆን መንገድ አበላሽተን አገሪቷን ለሌላ ተጨማሪ ዓመታት የደም ጎርፍ እንዲፈስባት ማድረግ የለብንም፡፡ በተለይም እኛን እዚህ ያደረሱንን ወጣቶችን ፣ተቃዋሚዎችን ጭምር ያስከበሩ ወጣቶችን ደም ዝም ብለን አጉል እንዲፈስ ከፈቀድን ታሪክ ምንጊዜም ይቅር የማይለን ሰዎች ሆነን እናልፈዋለን፡፡
የተሻለ ታሪክ የሚሠራው የጋራ አጀንዳ ቀርጾ በብሔራዊ መግባባት ላይ የመድረስ የሁላችንም የቤትሥራ እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ግን መግፋቱ ማናችንንም የማትጠቅም ኢትዮጵያ የመፍጠር ሁኔታ ይመጣል፡፡ ሁላችንም በማይሆን መንገድ የመክሰር ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ሁላችንም ተባብረን ከሕወሐት መሪዎች ጭምር አገሪቷን ከመጠፋፋት እና አጥፍቶ ከመጥፋት ፖለቲካ እንጠብቅ፡፡ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ማገዝን አሁንም ደግሜ አደራ እላለሁ፡፡
—-
ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ተቃዋሚ አለ መንግስትን የሚቃወም (ፖለቲካ ስርአቱን)የሚቃወም የተደራጁ ሀይሎች አሉ ።
 መንግስት ደሞ ተቃዋሚውን እንዲቃወሙ ራሱ የፈለፈላቸው የፖለቲካ ሀይሎች አሉ መንግስት ለነዚህ ቀለብ መስፈር ያቁም።
መንግስት ለነዚ ቀለብ መስፈር  ቢያቆም የ 24 ሰአት እድሜ አይኖራቸውም ።
 ኢህአዴግ ለእነዚህ ቀለብ መስፈሩን አቁሞ  ወደሱ የሰበሰባቸው።
ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው ያለቸው መንግስትና  ህዝብ ተባብሮ ወደ አንድነት ማምጣት አለበት ።
—-
የማንም ሀይል እየተነሳ ኦሮምያ ትገንጠል ይላል History አያውቁ Geography አያውቁ T.P.LF የሰራልህን Artificial. Border. ይዘህ ነው የምትገነጠለው?
የደቡብ ህዝብ እሺ ይላል?
አማራውስ እሺ ይላል? 5ሚልዮን የአ.አበባን ህዝብስ ቀቅለህ ልትበላው ነው?!?
ሁሴን ከድር
Filed in: Amharic