>
5:13 pm - Tuesday April 19, 9121

ፖሊስ  የአዲስ አበባውን ወጣት አስፋው ጭበሮን አይን በአፈሙዝ አጠፋ! (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

ፖሊስ  የአዲስ አበባውን ወጣት አስፋው ጭበሮን አይን በአፈሙዝ አጠፋ!
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
መርህ አልባ ስልት ሃገር አያረጋጋም
ውጤቱም የጥፋት አዙሪት ነው!!
የዶ/ር አብይ አስተዳደር ዋናውን ችግር ፈጣሪ አደብ ከማስገዛት ይልቅ በጥፋት ሃይሎች አረመኔያዊ ተግባርና የዘረኝነት ቅስቀሳ የተቆጣውንና ድርጊቱን እንዲያስቆም መንግስትን ሊጠይቁ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸውን  የአዲስአበባ ወጣቶች በአፈሳ ማሰር ቀጥሉዋል።ለሚያደርጉት ቅጥ ያጣ ተግባር  ለህዝብ ማብራሪያ መስጠት ሲያቅታቸው ህዝብን ለማደናገር ሲሎ በደጋፊወቻቸው በኩል የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ምናምን የሚል ማጭበርበሪያ ማሰራጨት ጀምረዋል።
የአክራሪ ጎሰኞችን ፕሮፖጋንዳ ለተመለከተ ሰው የሚፈልጉትን ነገር ለማስፈፀም ሲሉ ምንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለሱ ግልፅ ማሳያ ነው።ዶ/ር ብርሃኑና አቶ አንዳርጋቸው የቡራዩ ጭፍጨፋ ተጎጅወችን ከጎበኙ በሁዋላ ለጋዜጠኞች የሰጡትን መግለጫ ሰምቸዋለሁ።ዶ/ር ብርሃኑ እየሆነ ያለው ነገር በጣም ስላስጨነቀው በምንም ነገር ላይ እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር ሲቸገር አይቸዋለሁ። አቶ አንዳርጋቸውም ሰላም ከሌለ በሃገር ላይ ምንም ማድረግ እንደማይቻልና መንግስት ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጥ ጠይቀው ሰላምን ለማስከበር ከመንግስት ጎን ሁነው ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ሲገልፁ ሰምቻለሁ።አክራሪ ጎሰኞች ዶ/ር ብርሃኑንና አቶ አንዳርጋቸውን አሁን ባለው የሃገራችን ሁኔታ በመንግስት ግልበጣና ሁከት በመቀሰቀስ ለመፈረጅ ሲጣጣሩ ማየት ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት አክራሪ ጎሰኞች ፍላጎታቸውን ለማስፈፅም ምንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለሱ ግልፅ ማሳያ ነው። የዶ/ር አብይ መንግስት በመርህ አልባ ስልት ዙሪያ ጥምጥም መዳከሩን አቁሞ ለራሱም ለሃገርም ሲባል አክራሪ ጎሰኞችን አንድ ይበልልን።
ከዚሁ የጅምላ አፈሳና እስር ጋር በተያያዘ ህግ አስከባሪ ተብዬዎቹ አሰቃቂ ወንጀሎችን በአደባባይ እየፈጸሙ እንደሆነ በስልክ ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል ነገሩ እንዲህ ነው:-
ሽሮሜዳ አካባቢ ወጣት መአከል ለተጠለሉ  የቡራዩ ተፈናቃዮችን ምግብና ውሀ በማቅረብ ሲያስተናግድ ውሎ ማታ ወደ ቤቱ ሲገባ ጠብቀው ደብድበው በመኪና ጭነው ወደ መነን ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱት በሁዋላ ከመኪና ጎትተው በማውረድ በጠመንጃ አፈሙዝ አይኑን  አፍስሰውታል ።
ተጎጂው በስልክ እንደነገረኝ ሃሙስ መስከረም 10 በምኒልክ ሆስፒታል ተመርምሮ የቀኝ አይኑ ሙሉበሙሉ መጥፋቱን ተነግሮታል።
ሌላም ደግነት አስፋው የተባለ ወጣት በፖሊስ ድብደባ ሁለት ጥርሱ ወልቆ ወደ ሰንዳፋ ተጭኖ መወሰዱን ነግረውኛል። አስፋው ጭብሮ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የሚኖር የሶስት ልጆች አባት መሆኑንም ገልፆልኛል።
Filed in: Amharic