>

ገለልተኛ አጣሪ አሁኑኑ !!! (መስከረም አበራ)

ገለልተኛ አጣሪ አሁኑኑ !!!
መስከረም አበራ
የቡራዩው አሰቃቂ ግድያ ወዴት ወዴት ዘመም እያልን እንደሆን ማሳያ ነው፨ ይህ ነገር ተለባብሶ ማለፍ የለበትም፨ በሃገራችን ለሃቅ ግዴለሹ እየበዛ ነው ፣ እኔ ላይ ቢደርስስ ብሎ የሚያስበው ትቂት ነው፨ ሁሉም ለፖለቲካ ትርፍ ይሮጣል፣ የዘር ማንዘሩ ስም እንዳይጠፋ፣ የዘመዱ ስልጣን እንዳይናጋ የቻለውን ሁሉ ያደርጋል፨
እኛ የዛሬ ቋሚዎች ነገ እንደማንሞት ሆነን በሰው ህይወት ላይ የፖለቲካ ቁማር እንቆምራለን፤ ዘር ማንዘራችን ስሙ በክፉ እንዳይነሳ ለመሸፋፈን እንጋጋጣለን፨ ወቀሳው ከሰፈራችን ሰው እንዲርቅ  ማመካኛ ሊሆን ይችላል ወዳልነው ሁሉ ጣት እነቀስራለን፣ የራሳችንን “እውነት” እንፈጥራለን፣ ውሸት አያሳፍረንም ፣ትዝብት አንፈራም፣ ክፉኛ ዘቅጠናል!
በዚህ መሃል የንፁሃን ደም ይጮሃል፨ እውነተኛ ገዳያቸው ፣የጥፋቱ ባለቤት በውል ታውቆ ሲጠየቅ ከሞት ባይነሱም ቢያንስ ሁለተኛ ሞት አይሆንም፨ እናም ፍትህ ያሻቸዋል፨
የሃገራችን ተቋማት ላይ እምነታችን እስከዚህም ስለሆነ እንደ “Amnesty International, Genocide Watch, Human Rights Watch” አይነት ገለልተኛ አጣሪ ነገ ዛሬ ሳይል መግባት አለበት፨ በበኩሌ ዘይኑ ጀማልን እና የአዲሱ ገ/ እገግዚአብሄር የሚያጣሩት እውነት ሌላ ሞት  የይመስለኛል፨ እውነት ብናገር የእንትን ዘር ይነሳብኛል ሳይል  እውነትን መፈለግን ብቻ አንግቦ የሚመጣ አካል ያስፈልጋል፨
Filed in: Amharic