>

የፒያሳ አካባቢ የግንቦት ሰባት አስተባባሪዎች የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው (ጌታቸው ሽፈራው)

የፒያሳ አካባቢ የግንቦት ሰባት አስተባባሪዎች የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው
ጌታቸው ሽፈራው
እንዳልካቸው ማረባ እና ይግረም ጫመታ የተባሉ የፒያሳ አስተባባሪዎች ያሳለፍነው ሰኞ  ለፕሮግራሙ የሰቀሉትን ሰንደቃላማ ፓሊስ እየቀደደ ሲያወርድው ለምን ባንዲራ ትቀዳላችሁ በማለታቸው ከሰኞ ጀምረው በእስር ላይ ይገኛሉ
ዛሬ በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው መርማሪ ፓሊሱ ምርመራዬን አልጨረስኩም በሚል ሰበብ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የጠየቀው ቀን ተፈቅዶለታል ።
“ጨለማ እና ቀዝቃዛ ቤት ነው ያለነው”
እየሩሳሌም አስፋው
ይህንን የተናገሩት መርማሪዎቻቸው ፊት ነው ተዘግቷል የተባለው ጨለማ ቤት ዛሬ ኢትዮጵያዊነትን በዘመሩ ልጆች ዳግም ተከፍቷል  ከተያዙ 50 ሰዓት አልፏቸዋል ችሎት አልቀረቡም ልደታ ፍ/ቤት እነሱም ከአሳሪዎቻቸው ጋር መኪና ውስጥ እኛም በርቀት እነሱን እያየን ቁጭ ብለናል ምሳ እንዳናቀርብላቸው ተከልክለናል።
እኔም የአርበኞች ግንቦት 7 የሀገር ውስጥ አቀባበል ኮሚቴ አባል ነኝ። አብረውኝ የኮሚቴው አባል የነበሩት ብርሃኑ ተክለያሬድ እና መኮንን ለገሰ አቀባበሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ትልቁ ኃላፊነት የነሱ ነበር፤ በሚገባም ተወጥተውታል።
የብርሃኑ፣ የመኮንን እና ሌሎች አቀባበሉን በማስተባበር ሥራ ላይ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን እስር ያልተገባ ነው! የዜጎች በነፃነት የመደራጀት እና ማንኛውንም የፓለቲካ አመለካከት በነፃነት የመያዝ እና የማራመድ መብት ላይ የተሰነዘረ ግልፅ ጥቃት ነው።
የታሰሩበት ምክንያት አግባብ አይደለምና በአስቸኳይ ይፈቱ ካልሆነ እኔንም ከጓደኞቼ ጋር እሰሩኝ
Filed in: Amharic