>

ጅራፍ ራሱ ገርፎ እራሱ ሲጮህ የማናይባት አገር ታስፈልገናለች!  (ቬሮኒካ መላኩ)

ጅራፍ ራሱ ገርፎ እራሱ ሲጮህ የማናይባት አገር ታስፈልገናለች!
ቬሮኒካ መላኩ
 
1 . Amnesty International:  ትናንት ባወጣዉ መግለጫ በቡራዩዉ የዘር ፍጅት 58 ሰዎች በአሰቃቂ  ሁኔታ  እንደተገደሉ ገልጾ ሁሉም የተገደሉት በገጀራ ፤ በዱላና በድንጋይ እንደሆነ ገልጾ  ከተገደሉት 58 ሰዎች ዉስጥ አንዳቸዉም በጥይት እንዳልተገደሉ ገልጾል፤፤
2. ከቡራዩዉ አሰቃቂ የዘር ጭፍጨፋ የተረፉትና አዲስ አበባ ዉስጥ በየትምህርት ቤቱ  የተጠለሉት ለተለያየ ሚድያወች ቃል በቃል እንደገለጹት ጭፍጨፋዉን ያደረሱት ሰዎች ከአመት በፊት ጀምረዉ ያስፈራሯቸዉ እንደነበር ገልጸዉ  እነዚህም ጨፍጫፊዎች ራሳቸዉን ቄሮ በማለት የሚጠሩ እንደሆነ ፖሊስም አስተዳደሩም በደንብ እንደሚያዉቅ እየተናገሩ ነዉ፤፤
3.  የኦሮሚያ ከሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ነገሪ ሌንጮ ና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ይሄን በጥቁር ቀለም እንዳይለቅ ሆነ የተጻፈ አሰቃቂ ሽብር ለማድበስበስ የሚያደርጉት ሩጫ አስተዛዛቢም አስገራሚም ነዉ፤፤ ለነገሩ የክልሉ የፖሊስ አባል ቡራዩ ላይ ከቄሮ ጋር በአንደ ላይ በመሆን ድንጋይ ሲወረዉር የሚያሳይ ማስረጃ ቀድሞ ስለወጣ ኦሮሚያ ዉስጥ የመንግስተ መዋቅር እጅግ  በጽንፈና ሀይል የተበከለ እንደሆን  ማረጋገጥ ይቻላለ፤፤
..
የክልሉ መንግሥት ውጪያዊ ሰበብ መፈለጉን (externalization) እና በሌሎች ማላከኩን (Blame-shifting) ትቶ ራሱን ወደ ውስጥ እያየ መፈተሽ እንዳለበት መገንዘብ እንደሚገባው ማወቅ አለበት፡፡ፈረንጆች Denial የሚሉት ዓይነት፤ ያለውን ነገር እንደሌለ አድርገን መካድና መካካድ፤ የትም አያደርሰንም፡፡ መረጃ ባለመስጠትን ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ  አገር አናድንም፡፡ሰበብ ወይም ማምለጫ ዘዴ (Scapegoat) ለጊዜው እንጂ ለዘለቄታው አይበጅም፡፡ባዶ ኩነና (Vacant condemnation ) ምንም አይፈይደም ፤፤ጅራፍ ራሱ ገርፎ እራሱ ሲጮህ የማናይባት አገር ታስፈልገናለች! ራሱ ሰርቆ አፋልጉኝ ይላል እንደተባለው አይን-አውጣ፣ ሌባ እያየን ዝም የማንልባት አገር ታስፈልገናለች፤፤
Filed in: Amharic