>

የፌዴራል ፖሊስ ልምጭ እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ፍቅራቸው የታደሠ ይመስላል¡ (ዐቢይ ሠለሞን)

የፌዴራል ፖሊስ ልምጭ እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ፍቅራቸው የታደሠ ይመስላል¡

ዐቢይ ሠለሞን

በቡራዮ የተፈፀመውን ዝርፊያና ግድያን ለማውገዝ ሰኞ ዕለት ማለዳ ነበር የአዲስ አበባ ወጣቶች ወደ አደባባይ መውጣት የጀመሩት የፌዴራል ፖሊስም
“አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” እንደሚለው ተረት መሣሪያ ሊነጥቁ ነበር በሚል አምስት ሠዎችን ገደለ።

“እንደመር እንፋቀር ብለን ተገደልን
ህገ-መንግሥት ይከበር  መንግሥት እሹሩሩውን ያቁም” የሚሉ መፈክሮች አሠምቷል። መሞት የሰለቻቸው ወጣቶች። ነገር ግን  በመጎዳታቸው ብቻም አላበቃም።

 ትላንት ማክሰኞ እና ዛሬ በሰፊው የአዲስ አበባ ወጣቶች እየታፈሱ ይገኛል።

የፌዴራል ፖሊስ እንደለመደው ጡንቻውን ማሳየት ከ አዲስ አበባ ወጣቶች ጀምሯል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘይኑ ጀማልም በ ሰኞው መግለጫቸው በዘጠና ሠባት ላይ የ አዲስ አበባ ወጣቶች ተሸልመው የነበረውን አደገኛ ቦዘኔ የሚለውን የፍቅር¡ ስም ከሞተበት መቃብር ቀስቅሰው ሲያስነሱት ሰምተናል።

እናም ከዓመታት በኋላ የ አዲስ አበባ ነዋሪዎች እና የፌዴራል ፖሊስ መሣሪያ የአደባባይ ፍቅራቸውን በዚህ መንገድ ዛሬ አድሰዋል። “አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ” የአዲስ አበባ ወጣቶች ጉዳይ።

Filed in: Amharic