>

በፖለቲካው ዜሮ ፍላጎት ላለው የጋሞ ልጅም አዲስ አበባ ከኦሮሞው እኩል ከተማው ነች!!!! (ደግፌ አስረስ)

በፖለቲካው ዜሮ ፍላጎት ላለው የጋሞ ልጅም አዲስ አበባ ከኦሮሞው እኩል ከተማው ነች!!!!
ደግፌ አስረስ
አገራችን ውስጥ ቁጥር አንድና ጉልህ ውሸት አማራው ሌሎችን አፈናቅሎ ሲገፋና ሲገዛ ኑሯል የሚለው ነው። ይሄ ውሸት አማራን ብቻ የሚመለከት ቢመስለንም ከወያኔ ርኩስ መሪዎች በስተቀር፣ ፀጋየ አራርሳን ከመሰሉ የተማሩ ደንቆሮዎች ሌላ፣ ጅዋር መሀመድን ከመሰሉ ከፋፋዮች ውጭ ሁሉንም የሚመልከትና የሚጎዳ ነው። ይህን ውሸት በጋራ እስካላመከነው ድረስ ኢትዮጵያን ካጣን በኋላ በየተራ ራሳችንን እናጣለን!
ጅዋር መሀመድ አዲስ አበባ ጥግ ለተከሰተው አሳፋሪ ተግባር ሲመልስ “ከኛ በላይ የተገፉ መሬታቸውን የተነጠቁ የጋሞ ብሄሮች ላይ እንዴት እንዲህ እናደርጋለን?” ብሎ ነው የመለሰው። በጅዋር ዲክሽነሪ ይሄ ማለት አማራው ጋሞውን መሬቱን ነጥቆ ጨቁኖታል ተብሎ ነው የሚፈታው። ጋሼ ጅዋር ጋሞ መሬቱን ባማራ አልተነጠቀም ወይም በወልቃይቶችና በጅሩዎች አልተጨቆነም።
፲፲ ጋሞ ጅዋር በምትለው መልኩ የብሄር መስተጋብርን የሚያይበት አይን የለውም! ሰላማዊውን የራሱን ቢጤ አማራ ጨቋኝ ማለት ጎሜ ነው። ስለ ጎሜ ለማወቅ አሰፋ ጨቦን አንበው። ውሸት ጎሜ ነው። ጋሞዎች ታዲያ ለምን አዲስ አበባ ወይም ቡራዩ መጡ ካልክ አንድ አገራቸው ስለሆነ! ሁለትም አገራቸው ስለሆነ! ሶስተኛ ምክንያትም ከፈለክ አገራቸው ስለሆነ! አንተ ባህር ተሻግረህ አሜሪካ ዝንብህ እሽ ሳይባል ኑረህ መሄድህን አትዘንጋ! የአገር ፍቺው ሳይገባህ አገራዊ አጅንዳ ባትሸከም ግሩም ነው!
አዲስ አበባ የኦሮሞ አደለችም ባልተባለበት “አዲስ አበባ የኦሮሞ ነች” በማለት አውስትራልያ ሆኖ ሰው ማጋደል ጊዜውን ጠብቆ በአውስትራልያ መንግስት ማስጠየቁ አይቀርም። አምስት ሚሊየን ህዝብ ላይ በከበባ እልቂት ለመፈፀም መቀስቀስ በማንኛውም መመዘኛ ሽብር ነው። አንድም ሀይል አዲስ አበባ የኦሮሞ አይደለችም ብሎ አያውቅም! ሊልም አይችልም! አዲሳባ የታላቁ ኦሮሞ የሆነችውን ያክል ሁሉ፣ በእኩልነት ሽሮሜዳ የሰፈሩ ጋሞዎችም ነች! አንድ ድውር የሚያዳውር በፖለቲካ ዜሮ ፍላጎት ላለው የጋሞ ልጅ አዲስ አበባ ከተማው ነች! የነፀጋየ አራርሳና የነጅዋር መሀመድ የተሰቃየች ነብስ ይህን ደዋሪ የማንን ያክል ድርሻ አለህ ብላ ትጠየቀው ይሆናል። ይሄ ደዋሪ ባዲስ አበባ ላይ ፀጋየ ያንተን ያክል ድርሻ አለው። የጠቅላ ሚንስትሩን ዐብይ ያክል ድርሻ አለው! ያ ካልሆነ አፖርታይድን በአዋጅ አቋቁሙ!
ጋሞዎቹ መጤም ሰፋሪም አይደሉም! ዜጋ! ዜጋ ናቸው! በአማራው ላይ የተሰነዘረው የውሸትና የማረድ ሜንጫ ተራ እየጠበቀ ሁሉም ጋ ይደርሳል የሚባለው ለዚህ ነው። ዙሩ በዚህ ካልተገታ የመጨረሻው ማረፊያ የሚሆነው ኦሮሞው ላይ ነው። የዘር ፖለቲካ እስከቤተሰብ እንደሚወርድ በተራ ጋብቻ አይተንዋል፣ አርሲ ወለጋ እስከመባባል እንደሚዘልቅ የሳቸው ዘር ሳንሆን ያመንናቸው፣ የሳቸው ቋንቋ ተናጋሪ ሳንሆን የወደድናቸው ዐብይ ነግረውናል። ለጊዜው እሳቸውን ከፀጋየና ከጅዋር በተሻለ እናምናቸዋለን!!
ትልቁን ውሸት ከናድን አገራችንን እንገነባለን! “አማራ አፈናቃይም ገዥም ጨቋኝም አልነበረም! አደለም!!
Filed in: Amharic