>

ልክ እንደ ጋሞ ኢትዮጵያዊ ስትሆን እየሞትክም ቢሆን ገዳይህን ትታደጋለህ!! 

ልክ እንደ ጋሞ ኢትዮጵያዊ ስትሆን         
  እየሞትክም ቢሆን ገዳይህን ትታደጋለህ!! 
  ዜድ – ከራየን ወንዝ ዳር
*  ” ጋሞነቴ እና ኢትዮጵያዊነቴ ተጣልተውብኝ ላስታርቃቸው ቁጭ ያልኩበት ጊዜ ትዝ አይለኝም” ነበር ያለው ጋሽ አሰፋ ጫቦ። 
ጋሽ አሰፋ ጫቦ ግን እንኳን የዛሬውን የጋሞዎች መከራና ስቃይ ስደትንም ያላየ። እንኳንም በጊዜ ወደ አምላኩ ተጠራ።
ይህ ዛሬ ከኦሮሚያ ክልል በግድ እንዲወጣ የተደረገው የጋሞጎፋ ህዝብ ነው ጃኖ ፣ ኩታ፣ ጋቢ፣ ቡልኮ ነጠላ እያመረተ ኦሮሞን በእጅ ጥበቡ ጥበብ የሆነ አልባሳት እየሠራ የሚያስውበው፣ የሚያደምቀው።
ጋሞዎች ከሥራ በቀር ለወሬ እንኳን ጊዜ የሌላቸው ናቸው። የሽመና ጉድጓድ ውስጥ ተተክለው ሌት ተቀን በትጋት ኑሮን ለማሸነፍ የሚተጉ ነገዶች ናቸው። ተጫዋቾች ፣ የእረፍት ቀናቸው በሆነችው [ የዶርዜ ማርያም ] በሚሏት በዕለተ ሰኞ በፕላን የሚዝናኑ፣ በሞታቸው ጊዜ እንኳ በትርኢት ሟችን የሚሸኙ የዋሕ ህዝቦች ናቸው።
ዶርዜዎች ሀገር ወዳዶችም ናቸው። አሁን ለመፈናቀላቸው፣ ለመገደላቸው፣ ለመሰደዳቸው በእነ ጃዋር የጥፋት ሠራዊትም ጥርስ የተነከሰባቸው ልክ እንደ ዐማራው ከአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራ ጋር ሙጥኝ ማለታቸው ብቻ ነው። ሌላ ጣጣ ፣ ሌላ ምክንያትም የለም። የዲሞግራፊ መለወጡ ዘመቻ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።
ይሄ ሁሉ ጥፋት ሲፈፀምባቸው ያዩ የጋሞዎቹ ነገድ አባላት ዛሬ በጋሙጎፋ አርባምንጭ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር። ህዝቡ ባየው፣ በሰማው ነገር በእጅጉ መቆጣቱ የሚጠበቅ ተፈጥሮአዊም ነበር። የበቀል እርምጃም ይወስዳሉ የሚል ስጋትም በመንግሥትም በህዝብም ተገምቶም ነበር። ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ስትሆን በቀልህን ለእግዚአብሔር ነው የምትሰጠው። ሶማሌ ላይ ወገኔ ተገደለ ብለህ አወዳይ ላይ ምስኪን ሶማሌ በሜንጫ አንገቱን ድፋው የሚል ስብከት አትሰብክም። ኢትዮጵያውያን በቀልን ተምረው አላደጉም። ለበቀል ለበቀል ፈሪሀ እግዚአብሔር ባይኖረው ኖሮ ዐማራው በነገዱ ላይ እንደደረሰበት በደል ቢሆን ኢትዮጵያን ባወደመ ነበር። ነገር ግን ዐማራው ለምጣዱ ሲባል ዐይጧን ሲያሳልፍ ነው የኖረው።
አርባምንጭ በተቆጡ ወጣቶች ተጥለቀለቀች። የኦሮሞ ንብረት ናቸው ብለው ወዳሰቡዋቸው የንግድ ድርጅቶችም ማምራት ጀመሩ። ይሄን ያዩ የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቶቹን ቀድመው በኦሮሞ ንብረት ዙሪያ ሰፈሩ። ለምለም ሳርና ቅጠል በእጃቸው ነጭተው ይዘው። በሽምግልና እድሜያቸው መሬት ላይ ተንበርክከው ወጣቶቹን ለመኗቸው። አሰከኗቸው። አበረዷቸው። በቀል የእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ይበቀል፣ ፍርዱን ለእሱ እንተው። በእነሱ የጥፋት መንገድ አንሂድ በማለት አግባቡዋቸው።
ሽማግሌዎቹ የሀገረ ስብከቱን ሊቀጳጳስ በልጠው ተገኙ። የእስልምና ኡስታዝና ሼኪዊችን በልጠው ተገኙ። ለወትሮው በአርባምንጭ እንደ አሸን በመርመስመስ ይህን ምስኪን ህዝብ የሃይላንድ ውኃ የተቀባ የጌታ ውኃ ነው እያሉ መቶ መቶ ብር ይቸበችቡ የነበሩ ” የቁጩ ነብያትና ሐዋርያት፣ ፓስተሮችንም በለጡ። ቀደሙ። እኛንም አኮሩን።
ወጣቶቹም የአባቶቻቸውን ምክር ሰሙ። በሰልፉ ላይ ሞተውም፣ ተገድለውና ቆስለውም። የሽማግሌ ምክር ሰምተው ወደየቤታቸው ገቡ። የጋሽ አሰፋ ጫቦ ልጆች እንዲህ አኮሩን።
አባገዳዎች ሰምታችኋል አይደል። አይታችኋል አይደል። እዩ፣ ተመልከቱም። ከእናንተ ወገን አንድም ይህን አይነት ተግባት የፈፀመ ሰው አላየሁም። ኦሮሞ ሽማግሌ ያከብር ይሰማ እንደነበር አውቃለሁ። አሁን ኦሮሞ ሽማግሌ መስማት ትቷል። ሐጂ ጀዋርን ነው የሚሰማው፣ ፀጋዬ አራርሳን ነው የሚሰማው። ፕሮፌሰር ልዝቅኤልን ነው የሚሰማው። ጂጂኪያንና ምስራቅን ነው የሚሰማው። ፕሬዘዳንት ማሜማሜ ነው የሚሰማው። መፈክሩም ” ኢትዮጵያ አውትኦፍ ኦሮሚያ ” ሲል ነው ውሎ የሚያድረው። ህልሙም “የሚንሊክ ሰፋሪ” ነው የሚለውን ህዝብ ማፈናቀል፣ ማስወጣት፣ ማሰደድ ነው።
አባ ገዳዎች፣ አቦቲን ቢያ፣ ማንጉዶታ ጉርጉዶን አቦ ኤሳሴንተን፣ ማሎ ኡመኒ ኢትዮጵያ ዬሮ ኡመታ ኦሮሞ ወጂን አከአዳንጪቱ ዮጉ ጎደሙ ኢሲኒ ማል ኤግዱ?  ኢጆሌ ኬሰኒፍ ማሊፍ ዋኤንኩን ሃማዳ ጄተኒ ኢቲንሂምተን። ማሊፍ ጨሊስተኒ ዱቢከነ ላልተን?  ኤኙ ሶዳቱ?  ዋቀ ሞ ነመ ሶዳቱ?  ሜ ላላ ወራ ጋሞ፣ አቦቲ ጋሞ፣ ማንጉዶታ ጋሞ። ሜኢሳኒራ ዱቢ በረዳ።
ቦሩ ገሩ የሮ ኦሮሞን ጉባፊ ጀላን ኡመታ ሁዳን ወጂን አከ ዲናቲት ፣ አከ ነመ ቢየዲጉት ላለሜ ሶማሌ ወጂን፣ ዐማራ ወጂን፣ ትግሬ ወጂን፣ አመሞ ጋሞጎፋ ስልጤፊ ጉራጌ ወጂን ዲገ ወልዲበቴ ታኡን ሳ ባዬ ዋን ኢስነረኪሱ ነቲ ፈካታ። አመ ደፋቲ ከአ። ኡመተ ከነ ከኢጆሌን ኬ ረኮ ኢቲፊዴ ሁንዳ ዴማቲ ዲፈማ ጋፈዳ፣ ዳካ ባዳቲ ጂልበ ኬሰኒን ፎቀቃቲ ዲፈማ ጋፈዳ። [ ከበጀምቶተኮ አፉን ኬሰን አፋን ኦሮሞ አከ ጋሪቲ ኢንዱበኔ ኢስኒት ፈካቴ ዲፈተ ነጎዳ ]
ብራቮ !  ጋሙጎፋ፣ ብራቮ የጋሽ አሴ ልጆች። አሁንም ልክ እንደ ጋሽ አሴ ” ጋሞነታችሁ እና ኢትዮጵያዊነታችሁ አይጣላባችሁ።”
Filed in: Amharic