>

የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባርና ኦሮሚያ  (ኤርሚያስ ቶኩማ)

የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባርና ኦሮሚያ 
ኤርሚያስ ቶኩማ
==> ከ25 አመታት በዃላ ነገ ወደሃገራቸው የሚገቡት አብዛኞቹ የኦነግ አመራሮች ከሃገራቸው የተሰደዱት በትግራይ ነፃ አውጪ መሪዎች ሴራ ነው።
==> የኦነግ አባላት ባሌ ጫካ ውስጥ ተደብቀዋል በማለት ደኑን በሙሉ በእሳት በማያያዝ በርካታ ሺህ የኦነግ ወታደሮችን የገደሉት የትግራይ ነፃ አውጪ አመራሮች ናቸው
==> በሚያዝያ 1983 አመተ ምህረት የአምቦ ህዝብ የደርግ ደጋፊ ነው በማለት ህዝቡን በቦንብ የጨፈጨፉት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር አመራሮች ናቸው
==> ለሶማሌ ልዩ ሃይል መሣሪያ በማስታጠቅ በሐረርጌ የሚገኙ ንፁሃን ኦሮሞዎችን ያስጨፈጨፉት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር መሪዎች ናቸው።
==> ባለፉት 25 አመታት በርካታ ሺህ ንፁሃን ኦሮሞዎች በየእሥር ቤቱ ተጥለው ኢሰብአዊ ድርጊት እንዲፈፀምባቸው ትእዛዝ የሰጡት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር አመራሮች ናቸው።
==> የኢሬቻ ክብረ በአል ላይ የተገኙ ንፁሃን ዜጎችን በጥይት የጨፈጨፉት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር አመራሮች ናቸው።
==> ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ የተነሣውን የህዝብ ጥያቄ ለማፈን አደባባይ ላይ በሺህዎች የሚቆጠር ወጣቶችን ያስጨፈጨፉት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር አመራሮች ናቸው።
ይህ ሁሉ ሀጢያት በትከሻቸው ላይ ያለው የትግራይ ባለሥልጣናት ኦነግ ሠራዊት አቀባበል እናደርጋለን ማለታቸው ምን ያህል ወስላታዎችእንደሆኑ እና የሚሰማቸው ቢያገኙ ” እኛነን ወዳጆቻችሁ” የምትል አሳፋሪ  ድራማ ለመስራትእየሞከሩ እንደሆኑ የሚያሳይ ነው። የኦሮሚያ ወጣት ማን እንደገደለው በደንብ ጠንቅቆ ያውቃል። ጊዜው ሲመጣ ሁሉ የእጁን ያገኛል።
Filed in: Amharic