>

ባንዲራ ሽፋን እንጂ መነሻ አይደለም!!! ከአዲስ አበባ ግጭቱ ጀርባ (ታዬ ደንደአ)

ባንዲራ ሽፋን እንጂ መነሻ አይደለም!!!
ታዬ ደንደአ
 
ከአዲስ አበባ ግጭቱ ጀርባ
በከተማዋ የሚታየዉ የፀጥታ ችግር በቀን ጅቦች ስፖንሰርነት ቅጥረኞች ያነሱት መሆኑ ታዉቋል። አለማዉ ህዝቡን በማባላት ወደ ሥልጣን መመለስ ነዉ። ቅጥረኞች ሰልጥነዉ የተሰማሩ ከመሆናቸዉም በላይ በሞተር ሳይክል፣ በቤት መኪና እና በፕካፕ ገንዘብ እየተበተነላቸዉ መሆኑን የአይን እማኞች ገልፇል። ረብሻኞቹ ከሌላ ቦታ ተመልምሎ የመጡ ሲሆን የአዲስ አበባ ወጣት የለበትም። በብዙ ቦታዎች ደግሞ የአዲስ አበባ ህዝብ ግጭት እንዳይፈጠር ሲከላከል እንደ ነበር ታዉቋ። የግጭት ፕሮጄክቱ ሙሉ በሙሉ የፀረ-ለዉጥ ኃይሉ መሆኑ በተጨባጭ ማስረጃ ተረጋግጧል! ባንዲራ ሽፋን እንጂ መነሻ አይደለም። ሁለቱንም ባንዲራ የማይወዱ ሰዎች አንዱን ደግፎ ሌላዉን የተቃወሙ ያስመስላል።
ማስታወሻ
1. የረብሻኞቹ ፎቶ እና ቪዲዮ ይቀረፅ
2. የመኪኖቹ ታርጋ ይመዝገብ
3. ማስረጃ ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ አድርሱ።
Oduu Ammee
Jeequmsi Finfinnee waraabeyyii guyyaatiin kan qindeeffame ta’uu barameera. Jeeqxoti bakka biraatii filatamanii leenjifamuun bobbaafaman. Makiinaan maallaqa hiraa akka jiranis barameera.
Bakka jeequmsi jirutti suuraa fi viidiyoo jeeqxotaa waraabuu fi taargaa konkolaataa qabuu hin dagatinaa!
ይህችን የእጃዙር ወንጀል ከልምድ እናዉቃታለን!!!
 ታዬ ደንደዓ
 
ከ200 በላይ ቅጥረኞቹ ተይዘዋል።  ማን እንደላካቸዉም እየዘረዘሩ ነዉ።  ለያንዳንዳቸዉ 5000 ብር ተከፍሏቸዉ የተሰማሩ መሆናቸዉም ታዉቋል።
 
የኦሮሞ እስረኞች ከሶስት ጊዜ በላይ በቃሊቲ በዱሪዬ ተደብድቧል። ያስደበደባቸዉን በደንብ እናዉቃለን። ያስደበድብህና በኀላ አዛኝ ሆኖ ይመጣል። ዛሬም በተመሳሳይ ዱሪዬ አደራጅቶ ቄሮ ላይ ያዘመተዉ የተለመደዉ አዉሬ እንደሆነ ይታወቃል። አዲስ አበባ ላይ ቄሮን እያስመታ ሌላ ቦታ ደግሞ በኦሮሞ ፍቅር መቃጠሉን ይናገራል። እንደምናዉቀዉ አያዉቅም መሰለኝ። እስከአሁን ከ200 በላይ ቅጥረኞቹ ተይዟል።  ማን እንደላካቸዉም እየዘረዘሩ ነዉ። አንድም የአዲስ አበባ እና የአማራ ወጣት የለበትም። ምንም ትምህርት የሌላቸዉ ሰዉ እስከመዉጋት ስልጠና የተሰጠቸዉ እና ለያንዳንዳቸዉ 5000 ብር ተከፍሏቸዉ የተሰማሩ መሆናቸዉ ታዉቋል።
ፕሮጀክቱ ኦሮማራን ለማፍረስ የታቀደ እንደሆነ ግልፅ ሆኗል። ሁለቱን ታላላቅ ብሔሮች በማጋጨት ኢትዮጵያን ለማተራመስ አስበዉ ነዉ።
ክቡር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከOBN ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ
“በአዲስ አበባ የተፈጠረዉ ግጭት ፈፅሞ አማራን እና ኦሮሞን አይመለከትም። ሁለቱ ህዝቦች ከመቸዉም ጊዜ በላይ አሁን አንድ ሆኗል። ይህን አንድነት ለማላላት የሚፈልጉ ቡድኖች ኦሮሞ መስለዉ አማራን ወይም አማራ መስለዉ ኦሮሞን ሊሳደቡ ይችላሉ። ቄሮና ፋኖ አንድነታቸዉን አጠናክረዉ እነዝህን ወንጀለኞች ለፖሊስ መጠቆም አለባቸዉ። የነገዉን ታላቅ መድረክም በጋራ ሆነዉ ማድመቅ አለባቸዉ! ወጣቶቻችን የታገሉት ለወረዳቸዉ ወይም ለብሔራቸዉ ብቻ ሳይሆን ለመላዉ ኢትዮጵያዉያን ነፃነት ነዉ! ተባብረዉ አለማቸዉን ከግብ ማድረስ አለባቸዉ!”ብሏል።
አሁን ምርመራዉ እየቀጠለ ነዉ። ለደረሰዉ ጉዳት ሁሉ ድንጋይ የወረወረዉ ሳይሆን ያስወረወረዉ ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ መታወቅ አለበት
Filed in: Amharic