>

ከተማዋ ስጋት አንዣቦባታል!!! (ጃዋር መሀመድ)

ከተማዋ ስጋት አንዣቦባታል!!!
ጃዋር መሀመድ
ይህ የባንዲራ ጭቅጭቅ ወደ ግጭት እንዳያመራ በመስጋት የዛሬ 3 ወረ ገደማ ገና የድሮው ባንዲራ ባህ ዳር ላይ በብዛት ታይቶ ከሌሎች ተቃውሞን ሲቀሰቅስ  ምክረ ሀሳብ አቅርቤ ነበር። ይሄውም
1) ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን የፈለገውን ባንዲራ የማውለብለም መብቱ እንዲከበር
2) በህግ ከተደነገጉት ይፈዴራል እና የክልል ባንዲራዎች በስተቀር ማንኛውም ባንዲራ በመንግስት መስሪያ ቤት እና በህዝብ አደባባዮች እንዳይሰቀል
3) የሚወዱትን ባንዲራ መጠቀም መብት ሆኖ ሳለ የሌሎችን ባንዲራ ማንቋሸሽ፤ ማቃጣል እና መቅደድ ትክክል እናዳልሆነ እና ግጭትን መጋበዝ ስለሆነ ከንደዚህ አይነት ድርጊት እንድንቆጠብ
ሰሚ ግን አልተገኘም። ባለፉት ሳምንታት የድሮው  ባንዲራ በፊንፊኔ የህዝብ አደባባዮች እና መንገዶች ላይ ተሰቅሎ እና ተቀብቶ ለቀናት ቆየ። ፖሊስም ሆነ የከተማዋ አስተዳደር ምንም አላሉም።  ይህ ትዝብትን ብቻ ሳይሆን የፉክክር መንፈስንም መቀቀሱ አልቀረም። ትላንት የኦሮሞ ወጣቶች የኦነግን አመራር ለመቀበል እያደረጉ ባሉት ዝግጅት  የትግል አርማ የሆነውን ባንዲራ መስቀል ሲጀምሩ  ጥቃት ደረሰባቸው። ፖልስም ባንዲራ ማስወረድ  ጀመረ። በግብግቡም ሰዎች ተጎድተዋል፤ ከተማዋ ስጋት አንዣቦባታል። ይህ ጉዳይ በፍጥነት ሊረግብ ይገባል። ይህ እንዲሆን ደግሞ፡
– ማንኛውም ሰው የፈለገውን አይነት ባንዲራ እና አርማ የማውለብለብ መብቱ በሌሎች ዜጎች/ ቡድኖችም  በመንግስትም ሊከበር ይገባል
– አንዱ  ኦፊሴላዊ ያልሆነ ባንዲራ በህዝብ አደባብይ እንዲሰቀል ከተፈቀደ ሌላውም ሊፈቀድ ይገባል
– የፖሊቲካ ድርጅቶች ደጋፊዎቻቸውን በማረጋጋት መብታቸውም በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲያራምዱ ማድረግ አለባቸው።
– ቅዳሜ ለሚደረገው የኦነግ አመራር አቀባበል አስር ሺዎች ወደ አብዮት አደባባይ ይተማሉ። ይህ አቀባበል በሰላም እንዲፈጸም ሁሉም ወገን ሀልፊነት አለበት።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሰሞኑን በዚህች ከተማ ጸረ-ኦሮሞ አመለካካትን ለመቀስቀስ እየተሞከረ እንደሆነ ይታያል። ይህ አካሄድ ለከተማዋ ከፍተኛ አደጋ አለው።  በከታማዋ ላይ ያለው ጥያቄ የከትማዋ ወኪሎች እና የኦሮሚያ ክልል መንግስት በህገመንግስቱ መሰረት በሚያደርጉት ውይይት እና ድርድር በሰላም መፍታት ነው የሚሻው። ይህን ሰላማዊ እና ህጋዊ አክሄድ ትቶ የጥላቻ ዘመቻ ምክፈት ነገሮችን የባሰ ያወሳስባል፤ ከተማውንም ለምህበራዊ ግጭት እና ኢኮኖሚያዊ ውድቀት ያጋልጣል ። እናም በጥንቃቄ፤ በመወያት እና በሰላምዊ መንፈስ እንጓዝ እላለሁ።
Filed in: Amharic