>
5:13 pm - Tuesday April 20, 4483

አዲሱ ዘመነ ዐቢይ የመደመር የመከባበር ነፃነት የተበሰረበት አመት!!! (እስፋ ተድላ)

አዲሱ ዘመነ ዐቢይ የመደመር የመከባበር ነፃነት የተበሰረበት አመት !!!!!!
እስፋ ተድላ
ሁለት ሺ አስርን ማቆም ቢቻል ምንኛ  ጥሩ ነበር ። በተለይ ያለፉት ስድስት ወራቶች ላለፈው ሀያ ሰባት  ዐመት የተወገዘዉን ኢትዮጵያዊነት በለማ መገርሳ ቡድን በይፋ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ተብሎ በመነቃነቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኢህአዴግ መሪነቱ መደመርና መከባበርን በመስበክ እነሆ  ሁለትሺ አስራ አንድ ዋዜማ ላይ እንገኛለን ።
በአሜሪካ ቆይታቸው የለማ መገርሣ ቡድን የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ድጋፍና  ዕምነት አግኝተዋል ።
የዛ ውጤት የሆነው በውጭ ሲነቃነቅ የነበረው ግንቦት ሰባት አመራር አባሎች ዛሬ አዲስ አበባ ሲገቡ ከፍተኛ አቀባበል ከአውሮፕላን ማረፊያ በመንገዶችና በህዝብ በተሞላው የኳስሜዳ የኢትዮጵያ ን ሠንደቅ ዐላማ በማውለበለብ ኢትዮጵያዊነት ሱስ መሆኑን ዻግመኛ ተመስክሯል ።
በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ላለፉት ሀያ ሰባት  ዐመት በምንኖርበት ቦታ  ሁሉ  ባለማቆረጥ በዕርግጥም የሌሎች ሀገር ተወላጆች በሠልፍ ክብረወሰን መስበራችንን እስኪቀበሉ ድረስ ያደረግነውን ድምፅ ለሌለው ድምፅ መሆናችንን  ዛሬ በአዲስ አበባ ህዝቡ በነፃ ሲሰበሰብ ድምፁን ሲያሰማ በማየታችን እንደሰታለን።
ሀገራችን ዶክተር ብርሃኑ እንዳለው ትልቁ ስራ የማረጋጋት ስራ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት ሀያ ሰባት ዐመት በዕቅድ እንዳይደማመጥ በክልል የተወሰነ ህዝብ ነበር ።
ዐላማው ስልጣን ላይ የተቀመጡትን በሀብት አበልፅጎ ከሰባ በመቶ የሚሆነውን ወጣትበሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ  አድርጓል ።
ለዚህ ነው እንዳርጋቸው ፅጌ ጅቦች ላይመለሱ ወደ ዋሻዉ ገብቶአል ሲል ህዝቡ ይደገም ያለው ።
በመላው ዐለም የደረሰብንን ውርደት ለመሸሽ አንድም ቀን ኢትዮጵያዊ አይደለንም ሳንል በውጭ ያለን ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዐላማ በማውለብለብ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ግፍ በተለይ በዐረብ ሀገሮች ኤምባሲዎች ደጃፍ በማጋለጥ ያደረግነው ትግል ዛሬ እነዚህ ሀገራት ከኢትዮጵያውያን መጣላት ከፈጣሪ መጣላት መሆኑን እንዺገነዘቡ አስተምርዋል።
አሁን የኢትዮጵያ መጭው ረዥም  ጉዞ የቅርብ ስራው ዶክተር ብርሃኑ እንዳለው ማረጋጋት መከባበርን ይዞ ከጨዋው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መወያየትና ህዝብ ወኪሎቹን በነፃ እንዲመርጥ እንዲችል ተቋማትን ለመፍጠር ከዐቢይ አስተዳደር ጋር በጋራ መስራት ነው ።
ለዛሬው የአዲስ አበባ ነፃነት መደመር ቀን በ1997 በወያኔ ኢህአዴግ በግፍ ለተገደሉ ሁለት መቶ በላይ ዜጎች የዛሬ ስድስት ዐመት ድምፃችን ይሰማ የኢትዮጵያ እስልምና ዕምነት የጀመሩት ዕንቅስቃሴ የተከፈለው መስዋዕትነት በአዲስ አበባ ዙርያ መሬት ነጠቃን በመቃወም የቄሮ ዕንቅስቃሴ የተከፈለው መስዋዕትነት በባህርዳር ወሎ  የተነሳው የማንነት ትግል ና መስዋዕትነት ወደ ዘመነ ዐቢይ እንድንሻገር ማድረጉ አያከራክርም ።
የሁለት ሺህ አስራአንድ ዋዜማ ላይ ቆመን ያለፈው ዐመት ያበረከተልንን ደግ ደጉን በማባዛት እየደመርን ክፉዉን በመቀነስ አዺሱን የዐቢይ ዘመን የመከባበር እናድርገው ።
መልካም ሁለት ሺህ አስራአንድ !!!!!!
Filed in: Amharic