>

ህዳሴ ግድብና ሜቴክ!! (ደረጄ ገረፋ ቱሉ)

ህዳሴ ግድብና ሜቴክ!!
ደረጄ ገረፋ ቱሉ
ሳሊኒ የያዘው የሲቪል ስራ 75% ሲጠናቀቅ ሜቴክ የያዘው የ ኤሌክትሮ ሜካንካል ስራ የተጠናቀቀው  ከ25 እስከ 30 % ብቻ ነው ።
ሜቴክ ለዚህ እንዲከፈለው የተዋወለው በ26 ቢለየን ብር አካባቢ ሲሆን እስካ አሁን 16 ቢለየን ብር  አከባቢ ወስዷል።
ሌላው ሜቴክ የወሰደው ስራ የደን ምንጣሮ ሲሆን የውል መጠኑ 5.2 ቢለየን ብር ነው።የሰራው የስራ መጠን 37% ሲሆን የተከፈለው ክፍያ ደግሞ ግማሽ (2.6 ቢለየን ብር) ያህል  ነው።
በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ምክንያት ሳሊኒ 3.2 ቢለየን ብር እና 338 ሚለየን ዩሮ  አካባቢ ካሳ ጠይቋል።
ካሳውን አስመልክቶ አለመክፈል ይቻላል ወይ ተብለው የተጠየቁት ባለስልጣን አለመክፈል በፍጹም አይቻልም ብለዋል።
ግድቡ ይጠናቀቃል ተብሎ የታቀደው በ5 ዓመት ሲሆን አሁን ከተጀመረ 7 ዓመት ሆኖታል።
ስለዚህ  የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ካለፈ ሁለት ዓመት ቢሞላውም ሜቴክ ማጠናቀቅ የቻለው  ከ30% በታች ነው።የተከፈላቸው ክፍያ ደግሞ 65% አከባቢ ነው።

Filed in: Amharic