>

አርቲስት ታማኝ በየነ 150 ግራም ወርቅና መኪና  ተበረከተለት!!! (በሀይሉ ማሞ)

አርቲስት ታማኝ በየነ 150 ግራም ወርቅና መኪና  ተበረከተለት!!!
በሀይሉ ማሞ
* የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና አርቲስት ታማኝ በየነ 150 ግራም የወርቅ ሀብል ከነ መስቀሉ ተበርክቶለታል፡፡
* ከእንጅባራ ከተማ የለውጥ ደጋፊ ወጣቶችም እንዲሁ ስጦታ ተበርክቶለታል
 
በአቫንቲ ብሉናይ ሪዞርትና ስፓ በተካሄደው የእራት ግብዣ የባሕር ዳር ነዋሪዎች በአቶ ንጉሱ ጥላሁን አማካይነት ባማረ ፍሬም የተንቆጠቆጠ የራሱን ምስልና የወርቅ ስጦታውን አበርክተውለታል፡፡
እንዲሁም ዶክተር አንባቸው ለእዚህ ጀግና ይገባዋል ያሉትን በጋይንት ህዝብ ስም የመኪና ስጦታ አበርክተውለታል።
ሽልማቱ በጋይንት እንደቀጠለነው፦ 
ለጀግናው ልጃችን መኪና ያንሰዋል ያለው የጋይንት ህዝብ ፈረስ፣ በሬ፣ ጋሻ እና  ጦር እንዲሁም  ለእርሱና ለባለቤቱ ፋንትሽ በቀለ ካባ ሸልመዋቸዋል።
የእንጅባራ ከተማ የለውጥ ደጋፊ ወጣቶች ደግሞ የአጼ ቴዎድሮስን ምስል፣ በስሙ የተሰራ ጭራ አበርክተውለታል፡፡ለባለቤቱ አርቲስት ፋንትሽ በቀለም የአካባቢውን ባህል የሚገልጽ ድርብ ኩታ ተበርክቶላታል፡፡
Filed in: Amharic