>
5:13 pm - Tuesday April 19, 3566

ዘገምተኛው ጮሌ ጋንግሪን ነው ተቆርጦ መጣል አለበት!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ዘገምተኛው ጮሌ ጋንግሪን ነው ተቆርጦ መጣል አለበት!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ወያኔ የአማራ ህዝብ ማንነትን ለማጥፋት፣ የአማራ ህዝብን ስነልቡናዊ ጥንካሬ ለመስለብ እና የአማራን አንገት ለማስደፋት እንደ መሳሪያ ከተጠቀመባቸው መርዝ ሰዎች አንዱ አለምነው መኮንን ይባላል ።
አለምነው መኮንን የአማራ ህዝብን ” አማራ ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው ፣ ትምክህተኝነትን ያልተወ ፣በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር…  ይሄ የትምክህት ልጋግ መራገፍ አለበት ። ” በማለት ድፍን የአማራ ህዝብን የተሳደበ ወራዳ አረም ነው።
ይሄ ወራዳ ሰው ዛሬ ደሞ አይኑን በጨው አጥቦ  ፍርፋሪ በሚወረውርላቸው አሽከሮቹ አማካኝነት ብቅ እያለ ነው።
 የአለምነው  ቅልብ ካድሬዎች የኢጣሊያን የሮማውያን ዘመን የከፋፍለህ ግዛ ” Devide et Impera “ስልት በጎጥ  መልኩ ይዘው መጥተዋል።
“አለምነው የፕሮፓጋንዳ ሰለባ የሆነው ወሎዬ ስለሆነ ነው  ” የሚል እጅግ  አስቂኝና የወረደ ከአለምነው ከራሱ ተቀብለው እያስተጋቡ ነው።
ይሄን ምክንያት ስሰማ የአለምነው ዘገምተኛ ጮሌነትና  የአሽከሮቹ ደሞ ሆዳምነት ብብቴ ውስጥ ገብተው እንደኮረኮሩኝ አስቆኛል። ለመሆኑ ድፍን የአማራ ህዝብ የሚያደንቃቸው ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው  የወሎ አማራ አይደሉም ወይ?
ይሄ ጋንግሪን የሆነ ሰው ድፍን አማራ መሳደቡ ሳይበቃው ዛሬ ደሞ በጎጥ ሊከፋፍለን የህልም ሩጫ ጨምሯል።
 አለምነውና አሽከሮቹ  የአማራ ልጆች የአማራ ብሄርተኝነት የመጀመሪያው የቤት ስራ  የነበረውን ጎጠኝነትን አከርካሪውን ሰብረው ከቀበሩ በኋላ በመቃብሩ ላይ የአማራ ብሄርተኝነት እንድያብብ ማድረጋቸውን ገና የሰሙ አልመሰለኝም ።
ዛሬ በአማራ ምድር ጎጠኝነት ተቀብሮ በስብሶ በብስባሹ ላይ አማራዊነት የሚል  መንፈስ በቅሏል።
አለምነው መኮንን የመዘዘው ካርድ ለሰከንድ እንኳን የማያጫውተው መሆኑን አሽከሮቹ ልትገነዘቡ ይገባል ።
አለምነው አማራ ላይ የበቀለ ጋንግሪን ነውና ይሄ በሽታ መቁረጥና የመርዙን ሰንኮፍ መንቀል ግደታ ነው።
ብአዴን የሚባለው በለውጥ ላይ ያለው ፓርቲ እስካሁን ስደግፍ ቆይቻለሁኝ አሁንም ይሄ ፓርቲ የአማራ ህዝብ ነኝ የሚል ከሆነ  አለምነው መኮንንና መሰሎቹን  ቆርጦ ካልጣለ በአንድ እግሩ ሌላኛውን እግሩን ጠልፎ የመጣል ያህል ድርጊት እየፈፀመ መሆኑን መረዳት አለበት።
Filed in: Amharic