>

እቴጌ ጣይቱን በመሰረተቻት ከተማ ሀውልት ብትነፍጓትም ሚልዮኖች ልብ ውስጥ ተተክላለች!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

እቴጌ ጣይቱን በመሰረተቻት ከተማ ሀውልት ብትነፍጓትም ሚልዮኖች ልብ ውስጥ ተተክላለች!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ዛሬ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚንፈላሰስባት አዲስአበባ ከተማ የእቴጌ የጣይቱ ጥኑ የህልም ውጤት መሆኗ አለም የሚያውቀው ሀቅ ነው ። የተለያዩ የታሪክ ፀሃፊዎች ለእቴጌ ጣይቱ ” ብርሃን ዘኢትዮጵያ “የሚል ዘናጭ ሐረግ የቸሯት ለአገሯ ባደረገችው አስደናቂ  ገድል ነው ።
በዚህ ዘመን ኪቦርድ ጨብጠው ጀግናን ሲያንኳስሱ የሚውሉ Sick የኦሮሞ ብሄርተኞች ከበቀሉ ግማሽ ክፍለዘመን አስቆጠሩ ።
የእነዚህ ብሄርተኞች ተምሮ እንዳልተማረ እያደር የሚደነቁሩ እና እንደ ሽንቁር እንስራ የሚያፈሱ ናቸው  ።
 መስከረም ሲጠባ ፣ህዳር ሲታጠን ፣ የግንቦት ልደታ ሲመጣ ይሻላቸው ይሆናል እያልን ተስፋ እናደርጋለን እንጅ እነሱ እንደሆነ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ መጓዝ ዋነኛ አመላቸው ነው።
ታዋቂው ጀርመናዊ ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ ”A nation is a detour of nature to arrive at six or seven great men. —Yes, and then to get round them.
”  የኒቼ አባባል ግርድፍ ትርጉሙ ” አገር የምትመሰረተው በስድስት ወይም በሰባት ታላቅ ሰዎች ዙሪያ ነው ” ማለቱ ነው ።
ይሄ የኒቼ አባባል አለም የተቀበለው እውነታ ነው። ኒቼ ባስቀመጠው ሀቅ መሰረት ወደድንም ጠላንም ኢትዮጵያ  የምትባለው አገር እነ ይኩኖአምላክ ፣ቴዎድሮስ ፣ምኒልክ ፣ ጣይቱና ሌሎች ያልጠቀስኳቸው ጥቂት ታላላቅ ሰዎች አምጠው የወለዷት አገር ነች ።
ታዲያ እነዚህ ታላላቅ ሰዎች አምጠው የገነቧት አገር ላይ ሀውልት አይሰራም የሚል ዘነዘና ጭንቅላት ስመለከት ያቅረኛል።
 ይሄ መንግስትም  ሁሉን በእኩል አይን ማየት ሲገባው እነዚህን sick ብሄርተኞች  እሹሩሩ እያለ ሲያቀማጥል  ሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ግን  እንደ እንጀራ ልጅ  እየተመለከተ ነው።
በዚህ የሚያባብስ እንጅ የሚያሻሽል በሌለበት ሁኔታ ከገባንበት አዘቅት የመውጣትና አብሮ የመቀጠል  እድላችን የጠበበ ነው።
በዚህ በ22ኛው ሴንቸሪ ከአለም ጋር እንወዳደር ወይስ ማንም መንደሬ ውሃ ቀጠነ እያለ ባላዘነ  ባለ ቁጥር ጥቅማችንን አሳልፈን እየሰጠን በማያልቅ አዙሪት እንዘፈቅ ? መልሱን ለራሳችሁ የህሊና ፍርድ እተወዋለሁኝ።

ለሐውልት ሲጨንቅህ ልብህ ላይ ቆማለች!!!

ዲ/ን መ/ር  አባይነህ ካሴ
ጣይቱ አትጠልቅም 
ልትጠልቅ አልሠራትም
ተሠርታ ያለቀች በብርሃን ወጋግራ
በደስታ በሙሾ በነፃነት ፍልሚያ ምትኖር ተዘክራ
መጥለቂያ አድማስ የላት አለች ስታበራ
ጋት መሬት ለመንፈግ
ከንቱ ነው አትፈልግ
ለሐውልት ሲጨንቅህ ልብህ ላይ ቆማለች
የስንቱን ልብ መቅደስ ማደሪያ አርጋዋለች
ነፃነትን ሰብካ እሳት ለኩሳለች
አንገት አስደፍታ አንገት ቀና አርጋለች
ንግሥቲቱ ነግሣ ዙፋን የሠራችው ምድር ላይ ነው ብለህ
መሬት መሬት ስታይ 
ጣይቱ መለኛዋ ደምቃ ታበራለች በአፍሪካ ሰማይ ላይ 
ይነግርሃል እውነት ቀና በል እና እይ
ጣይቱ እሳትሽን አደራ እንዳትለቂው
ግንፍልፍሉ በርዶ ሲያውቅሽ እንድትሞቂው 
ጣይቱ ጦቢያዬ ናት አትጎትታትም
የዚህ የዚያ ብለህ አትከፋፍላትም
አንተ ብትወነክል ጣልያን እሺ አይልም
ቀምሶታል የጣይቱን ምሬቷን ጣሟንም
ለእኛ ብርሃን ስትኾን ለፋሺስት እሳቷ
አይጠረጠርም በዓለም ነው ሐውልቷ
ይነጋል አይቀርም ይነጋል ሌሊቷ
ጠሐይ ናት ጣይቷ፡፡ 
የአዲስ አበባ መስተዳድርን አጓጉል ውሣኔ በመቃወም ነሐሴ ፳፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.
Filed in: Amharic